የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)
ሽማግሌዎቹ እስሚዝና ላፍቦሮ
አሁን በሕይወት ያሉትን የመጀመሪያዎቹን መልእክት ተሸካሚዎች በቀላሉ መቁጠር እንችላለን (1902)፡፡ ሽማግሌው ዩሪያ እስሚዝ ከእኛ ጋር ግንኙነት የነበረው በሕትመት ሥራ ጅምር ላይ ነበር፡፡ እርሱ ከባለቤቴ ጋር አብሮ ሰርቷል፡፡ ሁልጊዜ በሪቪውና ሄራልድ አዘጋጆች ዝርዝር ውስጥ ለማየት ተስፋ እናደርጋለን፤ መሆን ያለበትም እንዲህ ነው፡፡ ሥራውን የጀመሩ ሰዎች፣ ጦርነቱ በጠነከረ ጊዜ በጀግንነት የተዋጉት፣ የያዙትን መልቀቅ የለባቸውም፡፡ እነርሱ ከባዱን ችግር ተሸክመው ካለፉ በኋላ ወደ ሥራው በገቡት ሰዎች መከበር ይኖርባቸዋል፡፡ Amh2SM 225.2
ለሽማግሌው እስሚዝ በጣም ርኅራኄ ይሰማኛል፡፡ በሕትመት ሥራ የሕይወቴ ፍላጎት ከእርሱ ፍላጎት ጋር የተሳሰረ ነው፡፡ እንደ መጽሐፍ አዘጋጅ በዕጣውና በቦታው እንዲቆም ብቁ ያደረጉትን መክሊቶች ይዞ ወደ እኛ የመጣው በወጣትነት ዕድሜው ነበር፡፡ እጅግ በጣም ጥሩ የሆኑና በመንፈሳዊ እውነት የተሞሉ ጽሁፎችን በሪቪውና ሄራልድ ውስጥ ሳነብ በጣም ያስደስተኛል፡፡ ስለ እርሱ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፡፡ ለኤልደር እስሚዝ ብርቱ ርኅራኄ ይሰማኛል፣ ስሙ ሁልጊዜ እንደ መሪ አዘጋጅ ሆኖ በሪቪው ላይ መውጣት አለበት ብዬ አምናለሁ፡፡ ይህንን እግዚአብሔር ያደርገዋል፡፡ ከጥቂት አመታት በፊት ስሙ በሁለተኛ ደረጃ ስለተቀመጠ ሀዘን ተሰማኝ፡፡ እንደገና ስሙ በመጀመሪያ ደረጃ በመቀመጡ አለቀስኩና «እግዚአብሔር ይመስገን” አልኩ፡፡ እግዚአብሔር ይሆናል ብሎ እንዳቀደው የሽማግሌው እስሚዝ ቀኝ እጅ ብዕር መያዝ እስከቻለ ድረስ ሁልጊዜ በዚያ ቦታ ይሁን፡፡ እጆቹ ሲደክሙ እሱ በቃል እየተናገረ ልጆቹ ይጻፉ፡፡ Amh2SM 225.3
ሽማግሌው ጄ ኤን ላፍቦሮ ለእግዚአብሔር ሥራ ችሎታዎቹንና ሥጦታዎቹን እስከሁንም ድረስ መጠቀም ስለሚችል አመሰግናለሁ፡፡ በወጀብና በፈተና ውስጥ ታማኝ ሆኖ ቆሟል፡፡ ከሽማግሌዎቹ እስሚዝ፣ ከባለቤቴ፣ በኋላ እኛን ከተቀላቀለው ከወንድም ቡትለር፣ እና ከአንተ ጋር (ኤስ ኤን ሃስከል) እንዲህ ማለት ይችላል፡- «ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም…እናወራለን፤ እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ሕብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን፡፡ ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው» (1ኛ ዮሐ. 1፡ 1-3)፡፡ Amh2SM 225.4