የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

176/349

ክፍል 6—ማጽናናትና ማበረታታት

መግቢያ

የእግዚአብሔር መልእክተኛ የሆነችው ኤለን ጂ ኋይት የስቃይን ምንነት አውቃለች፡፡ የልጅነት ተስፋዎቿ ሕይወቷን ሊያጠፋ በነበረው በዘጠኝ ዓመት ዕድሜዋ በደረሰባት አደጋ ተቀስፎ ነበር፡፡ በእናትነት ልምምድ ውስጥ አራት ጊዜ አልፈበታለች፡፡ ሁለት ጊዜ በወንድ ልጆቿ ሞት አዝናለች፡፡ ከአገልግሎት ዘመኗ ወደ ግማሽ የሚጠጋውን ያሳለፈችው በባልቴትነት ነው፡፡ በየጊዜው እየተመላለሰ የሚመጣውን ሕመም ምንነት አውቃለች፡፡ በሥቃይ ውስጥ ላሉት፣ የሞት ሀዘን ለደረሰባቸው እና በዕድሜ ለገፉትና ላዘኑት የሰጠቻቸው የማበረታቻ መልእክቶች በራሷ የህይወት ልምምድ ውስጥ የተፈተኑ ናቸው፡፡ Amh2SM 220.1

የእግዚአብሔርን ፈቃድ ምስጢሮች ማብራራት የሚችል ማንም የለም፣ ነገር ግን በፈተናና በችግር ጊዜ በእግዚአብሔር የታመኑ ሰዎች እግዚአብሔር እቅዱን እየፈጸመ መሆኑን ያውቃሉ፡፡ ሚስስ ኋይት ይህንን ስላወቀች በሰው አገር ለአሥር ወራት ስለደረሰባት ሥቃይ የነበራትን ስሜት እጥር ምጥን ባለ በዕለታዊ ማስታወሻዋ በጻፈችበት በ1892 ዓ.ም ዕለታዊ መጽሔት ውስጥ ገልጣዋለች፡፡ ዘይት ቀብተው ጸሎት ቢያደርጉላትም ባለመፈወሷ የደረሰባትን ተስፋ መቁረጥና በሕይወትም ሆነ በሞት በእግዚአብሔር የነበራት የማይናወጥ መታመን በዚህ ቦታ ተገልጧል፡፡ Amh2SM 220.2

በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ በሚስስ ኋይት የተጻፉት እና ለሚሰቃዩት ማጽናኛ እንዲሆኑ በዚህ ቦታ የቀረቡት የግል መልእክቶች እግዚአብሔር የፍቅር አምላክ ከሆነ ሕዝቡ ለምን ለረዥም ጊዜ በሕመም ይሰቃያል? ከሕመም የተነሣ አልጋ ላይ ወድቀው ለምን ይመነምናሉ? የሚሉ ጥያቄዎችን ለመመለስ ይረዳሉ፡፡ በእነዚህ ገጾች ላይ የተገለጸው ዓይነት ባሕርይ ባላቸው ልምምዶች ውስጥ ለሚያልፉ ሰዎች መጽናናትና መበረታቻ ይመጣላቸዋል፡፡ ማንኛውም ዓይነት ድግግሞሽ ቢኖር በተቻለ መጠን ዓላማው በተለያዩ የግል ሁኔታዎች ውስጥ መጽናናትን ለማምጣት ነው፡፡ Amh2SM 220.3

የኋይት ባለአደራዎች፡፡