የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

163/349

ውስን የሆነ ደሞዝን በተመለከተ ለአንድ ሐኪም የተሰጠ ምክር

በአንዳንድ የስራ መስመሮች ከደሞዝህ በላይ የሆነ ገቢ ለማግኘት ያለህ እቅድ ወደ ክፉ ውጤቶች ለሚመራ ፈተና በር እየከፈተ ነው፡፡ ይህ በአንተም ሆነ እነዚህን የስምምነት አንቀፆች ባዘጋጁት ሰዎች አልተስተዋለም፡፡ ነገር ግን ይህ ተግባር ለአንተ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት የሚያስከትል ከመሆኑም በላይ የእግዚአብሔርን ሥራ ያሰድባል፡፡ በዚህ ዕቅድ ውስጥ በደንብ መታየት ያለበት የስህተት መርህ አለ፡፡ ምንም ነገር ወደ ስህተት የሚመራ ክፍተት ማሳየት የለበትም፡፡ በሁሉም ነገር ክፍተቱ መደፈን አለበት፡፡ ለምትሰራው ሥራ የተወሰነ ደሞዝ መቀበልና በዚያ ገንዘብ መተዳደር አለብህ፡፡ Amh2SM 199.3

የዚህ ዓይነት ባሕርይ ያለው ነገር ከዶ/ር ዩ ጋር በተደረጉት ድርድሮች ውስጥ ተከናውኗል፡፡ ማጭበርበር ያለበት ድርድር ነበር፡፡ እግዚአብሔር ዝንባሌውንና ውጤቱን ይመለከታል፡፡ ሊቋቋሙ ባሉት የጤና ማሰልጠኛ ተቋማት ውስጥ ይህ የደሞዝ አከፋፈል ዘዴ መፈጸም የለበትም፡፡ በዚህ መመሪያ መሰረት ለአገልግሎቶችህ ተገቢ የሆነ ደሞዝ መከፈል አለበት፡፡ ከተቋሙ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሁሉ ከአገልግሎታቸው ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ደሞዝ መከፈል አለባቸው፡፡--Letter 99, 1900. Amh2SM 200.1