የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

15/349

እንግዳ የሆኑ ወይም ወጣ ያሉ ነገሮች አያስፈልጉም

እንግዳ የሆኑ ወይም ወጣ ያሉ ነገሮች ቃሉ ማሳደር የሚችለውን አሻራ ደካማ ስለሚያደርጉ የእውነትን ቃል በሚናገሩ ሰዎች መካከል እንግዳ የሆኑ ወይም ወጣ ያሉ እንቅስቃሴዎች መኖር የለባቸውም፡፡ ሰይጣን ከተቻለው ከኃይማኖታዊ አገልግሎቶች ጋር የራሱን ክፉ ተጽዕኖ ለመቀላቀል ቁርጥ ውሳኔ ስላደረገ ራሳችንን መጠበቅ አለብን፡፡ ቲያትራዊ እይታ በእግዚአብሔር ቃል ላይ የሚኖረንን እምነት ለማጠንከር ስለማይረዳ ቲያትራዊ እይታ መኖር የለበትም፡፡ ይህ የሰብዓዊ መሳሪያን ትኩረት ወደ ሌላ አቅጣጫ ይመልሳል፡፡ {2SM 23.3} Amh2SM 23.3