የልጅ አመራር

39/85

ምዕራፍ 37—የልማድ ኃይል

ልማዶች እንዴት እንደሚመሰረቱ—አንድ ድርጊት፣ መልካምም ሆነ ክፉ፣ ባህሪይን አይቀርጽም፤ ነገር ግን ልቅ ሀሳቦች እና ስሜቶች ለተመሳሳይ አይነት ድርጊቶች እና ተግባሮች መንገድ ያዘጋጃሉ። 362 CGAmh 189.1

… ልማዶች የሚሰረቱት እና ባህሪይ የሚረጋገጠው በድርጊቶች መደጋገም ነው፡፡ 363 CGAmh 189.2

መልካም ልማዶች የሚመሰረትበት ጊዜ—ባሕሪይ በከፍተኛ መጠን የሚመሰረተው በመጀመሪያዎቹ ዓመታት ውስጥ ነው፡፡ በዚህ ጊዜ የተመሰረቱ ልማዶች ሰዎችን በአዕምሮ ብቃት ግዙፍ ወይንም ድንክ በማድረግ ረገድ ተፈጥሮ ከምትለግሳቸው ከማናቸውም ተሰጥኦዎች ይልቅ የላቀ ተጽዕኖ አለው፤ ምክንያቱም እጅግ ምርጥ ተሰጥኦዎች ከተሳሳቱ ልማዶች የተነሳ ሊዛቡ እና ሊዳከሙ ይችላሉ፡፡ አንድ ሰው በልጅነት ዕድሜው ጎጂ ልማዶችን ይበልጥ ሲማር፣ ክፉ ልማዶቹ ሰለባዎቻቸውን ይበልጥ በባርነት አጥብቀው ይይዟቸዋል፣ ይበልጥም በእርግጠኝነት የመንፈሳዊነት ደረጃውን ዝቅ ያደርጋሉ፡፡ በሌላ በኩል፣ ትክክለኛ እና መልካም ልማዶች በወጣትነት ጊዜ ከተመሰረቱ በአጠቃላይ በባለቤቱ መላ የሕይወት ጉዞ ላይ አሻራ ያሳርፋሉ። አብዛኛውን ጊዜ፣ በኋለኛው ህይወታቸው እግዚአብሔርን የሚፈሩ እና ቀና የሆነውን የሚያከብሩ ሰዎች ዓለም የኃጢአት ምስሎችን ነፍሳቸው ላይ የምታትምበት ጊዜ ከመድረሱ በፊት ያንን ትምህርት ተምረውታል፡፡ በአጠቃላይ በዕድሜ የበሰሉ ሰዎች በአዳዲስ ተጽዕኖዎች ሥር ባለመውደቅ ረገድ ልክ እንደ ዓለት የጸኑ ናቸው፣ ነገር ግን ወጣቱ በተጽዕኖ ሥር ወዳቂ ነው፡፡ 364 CGAmh 189.3

ልማዶች ሊሻሻሉ ይችላሉ፣ ነገር ግን አልፎ አልፎ ነው የሚለወጡት—ልጁ የሚመለከታቸው እና የሚሰማቸው ነገሮች በህይወት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ሊጠፋ በማይቻል አይነት ሁኔታ ጨቅላ አእምሮው ላይ ጥልቅ መስመሮችን ያሰምራሉ፡፡ አዕምሮው አሁን በመቀረጽ ላይ ነው፣ ስሜቶቹም አቅጣጫ እና ብርታትን እያገኙ ናቸው። በተወሰነ ጊዜ ውስጥ የተደጋጋሙ ድርጊቶች ልማዶች ሆነዋል፡፡ እነዚህ ከጊዜ በኋላ በጥብቅ ስልጠና ሊሻሻሉ ይችላሉ፣ ነገር ግን የሚለወጡት አልፎ አልፎ ነው፡፡ 365 CGAmh 189.4

ልማዶች አንዴ ከተመሠረቱ በጥብቅ ይበልጥ ወደ ባህሪይ እየተቀረጹ ይሄዳሉ፡፡ አዕምሮ ክፉም ሆነ መልካም ቢሆን ከእድሎች እና ከአጋጣሚዎች ቅርጹን ያለማቋረጥ ይቀበላል፡፡ በየዕለቱ ተማሪዎች በደንብ እንደሰለጠኑ ወታደሮች በልዑል አማኑኤል ሰንደቅ አላማ፣ ወይም ደግሞ በአመፀኛው የጨለማ መሪ ሰንደቅ ስር የሚያደርጋቸውን ባህሪያት እንዲቀርጹ እናደርጋለን፡፡ የትኛው ይሆን?366 CGAmh 190.1

ጽኑ ጥረት አስፈላጊ ነው—አንዴ ለመሥራት የደፈርነውን ነገር እንደገና ለማድረግ ይበልጥ ዝግጁ እንሆናለን። ራስን የመግዛትን፣ ራስን የመቆጣጠር፣ ምጣኔ ሐብትን፣ የቅርበት አተገባበርን፣ ጤናማ እና አስተዋይ ንግግርን፣ የትዕግሥትን እና እውነተኛ ትህትናን ልማዶችን ያለ ትጋት፣ በቅርበት ራስን በማየት ካልሆነ በስተቀር አይገኝም። ጉድለቶችን ከማሸነፍ፣ እራስን ከመቆጣጠር እና እውነተኛ ባህሪይን ከማሳደግ ይልቅ ምግብረ-ብልሹ እና ነውረኛ መሆን በጣም ቀላል ነው። የክርስትና ጸጋዎች በሕይወታችን ውስጥ ፍጹም እንዲሆኑ ከተፈለገ ትጋት የታከለበት ጥረትን ይጠይቃል፡፡ 367 CGAmh 190.2

ብልሹ ልጆች ሌሎችን አደጋ ላይ ይጥላሉ—ፈሪሃ አምላክ ያላቸው ወላጆች ልጆቻቸውን ለትክክለኛ ልማዶች እንዴት ማሠልጠን እንዳለባቸው ያስባሉ፣ እቅድም ያወጣሉ። እነርሱ ያለ ልምድ ጓደኞቻቸውን ለራሳቸው እንዲመርጡ ከመተው ይልቅ ራሳቸው ይመርጡላቸዋል፡፡ 368 CGAmh 190.3

ልጆች ገና በልጅነታቸው በትጋት እና ትዕግስት በትክክለኛው መንገድ ያልሰለጠኑ እንደሆነ የተሳሳቱ ልማዶችን ይመሰርታሉ፡፡ እነዚህ ልማዶች በመጪው ህይወታቸው ውስጥ ያድጉና ሌሎችን ያበላሻሉ፡፡ አዕምሮአቸው ወደ ዝቅተኛ ደረጃ የወረደ፣ በተሳሳተ የቤት ተፅእኖዎች፣ በአሳሳች ልማዶች የተበላሹ፣ የተሳሳቱ ልማዶቻቸውን በህይወት ዘመናቸው ይዘዋቸው ይሄዳሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች የኃይማኖት ሥራ ቢሰሩ እንኳ፣ እነዚህ ልማዶች በኃይማኖታዊ ሕይወታቸው ወስጥም ይገለጣሉ፡፡ 369 CGAmh 190.4

ንጉሥ ሳኦል፣ አሳዛኙ ምሳሌ—የእስራኤል የመጀመሪያ ንጉሥ ታሪክ የልጅነት ጊዜ የተሳሳቱ ልማዶች ኃይል አሳዛኝ ምሳሌን ያሳያል፡፡ ሳኦልም በወጣትነቱ እግዚአብሔርን አልወደደውም፣ ደግሞም አልፈራውም ነበር፣ እንዲሁም ያ ችኩል መንፈሱ፣ በልጅነቱ መገዛትን ባለመሠልጠኑ፣ መለኮታዊ ስልጣን ላይ ለማመጽ ዘወትር ዝግጁ ነበር፡፡ በወጣትነታቸው ለእግዚአብሔር ፈቃድ የተቀደሰ ክብር ያላቸው እና የኃላፊነታቸውን ግዴታ በታማኝነት የተወጡ፣ በኋለኛው ዕድሜያቸው ለከፍተኛ አገልግሎት የተዘጋጁ ይሆናሉ፡፡ ነገር ግን ሰዎች እግዚአብሔር የሰጣቸውን ሀይል ለዓመታት መለወጥ አይችሉም፣ ከዚያም ለመለወጥ ሲመርጡ እነዚህን ትኩስ እና ነጻ ኃይሎች ሙሉ ለሙሉ ተቃራኒ በሆነ መንገድ ላይ ያገኙታል።370 CGAmh 191.1

አንድ ልጅ ትክክለኛ የሃይማኖት መመሪያን ሊቀበል ይችላ፤ ነገር ግን ወላጆች፣ አስተማሪዎች፣ ወይም አሳዳጊዎች ባህሪው ወደ ተሳሳተ ልማድ እንዲያደላ ከፈቀዱለት፣ ያ ባህሪይ ያልተገራ እንደሆነ የበላይ ኃይል ይሆንና ልጁ ይጠፋል፡፡ 371 CGAmh 191.2

ትናንሽ እርምጃዎች አስፈላጊ ናቸው—እያንዳንዱ እርምጃ ድርብ ባህሪይና ጠቀሜታ አለው፡፡ በአነሳሹ ስሜት ላይ ተመስርቶ በጎ ወይም ክፉ፣ ትክክል ወይም ስህተት ይሆናል። የተሳሳተ ተግባር፣ በብዙ ጊዜ ድግግሞሽ በተግባሪው አእምሮ እንዲሁም በማናቸውም አይነት ሁኔታ፣ በመንፈሳዊም ሆነ ጊዜያዊ ከእርሱ ጋር ግንኙነት ባላቸው አእምሮዎች ላይ ዘላቄታ ያለውን ተጽዕኖ ያሳርፋል፡፡ ትክክል ባልሆኑት ትናንሽ ድርጊቶች ላይ ትኩረት የማይሰጡ ወላጆች ወይም አስተማሪዎች እነዚህን ልማዶች በወጣቱ ውስጥ ይመሰርታሉ፡፡ 372 CGAmh 191.3

ወላጆች በአደራ የተሰጣቸውን ነፍሳት በታማኝነት ሊይዙ ይገባል። እነርሱ በልጆቻቸው ውስጥ ትዕቢትን፣ ብኩንነትን እና የታይታ ፍቅርን ማበረታታት የለባቸውም። በትናንሽ ልጆች ላይ ብልጣ ብልጥነት የመሚስሉ እነርሱ መማር የሌለባቸው እና ሲያድጉ የሚታረሙበት ትናንሽ ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉ ቀልዶችን ማስተማር ወይም እንዲማሩ መፍቀድ የለባቸውም፡፡ 373 CGAmh 191.4

ትናንሽ ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉ ቀልዶች እና ስህተቶች ልጁ ህፃን እያለ አስቂኝ ይመስሉ ይሆናል፣ ሊፈቀድለት እና ሊበረታታም ይችላል፡፡ ነገር ግን ህፃኑ እያደገ ሲሄድ አፀያፊ ይሆናል፡፡ 374 CGAmh 192.1

መጥፎ ልማዶች ከመልካም ልማዶች ይልቅ በቀላሉ ይቀረጻሉ—እነርሱ የሚማሯቸው ትምህርቶች በሙሉ ልል ከሆነ የአስተዳደግ ሳቢያ ሊመጣ የሚችለውን ውጤት ሊያስቀር አይችልም፡፡ አንድ ቸልተኝነት ብዙ ጊዜ ተደጋግሞ ሲከሰት ልማድ ይሆናል። አንድ የተሳሳተ ድርጊት ለሌላው ስህተት መንገድ ያዘጋጃል፡፡ ክፉ ልማዶች ከመልካም ይልቅ በቀላሉ የሚመሰረቱ እና ይበልጥ በብዙ ትግል የሚወገዱ ናቸው፡፡375 CGAmh 192.2

ትናንሽ ልጆች፣ ለእራሳቸው ከተተው፣ ከጥሩው ይልቅ መጥፎውን በቀላሉ ይማራሉ። መጥፎ ልማዶች ከተፈጥሮ ልብ ጋር በተሻለ ሁኔታ ይስማማሉ፣ እናም በጨቅላነት እና በልጅነት ጊዜ የሚያዩት እና የሚሰሙት ነገር በአዕምሮአቸው ላይ በጥልቀት ይቀረጻል፡፡ 376 CGAmh 192.3

የልጅነት ልማዶች መጻኢውን ድል ወይም ሽንፈት ይወስናሉ—እኛ በግለሰብ ለጊዜያውም እና ለዘለአለም ልማዶቻችን እንደሚቀርጹን እንሆናለን። ከትክክለኛ ልማዶች የተነሳ የየዕለቱን ግዴታ በመወጣት ረገድ ታማኝ የሆነ ሰው፣ በሌሎች ሰዎች ጎዳና ላይ ብሩህ ብርሃን እንደሚያበራ መብራት ይሆናል፤ ነገር ግን ታማኝነት የማጉደል ልማዶች ያደጉ እንደሆነ፣ የልቅነት፣ የስንፍና፣ የቸልተኝነት ልማዶች እንዲጎለብቱ ከተፈቀደላቸው ከእኩለ ሌሊት ይልቅ የጠቆረ ደመና በምድራዊ መጻኢ ህይወት ላይ ይሰፍንና ግለሰቡን ከለዘላለም ሕይወት ያግዳዋል፡፡16 CGAmh 192.4

በልጅነት እና በወጣትነት ላይ ባሕሪይ እጅግ ተጽዕኖ ያሳድራል፡፡ ራስን የመቆጣጠር ኃይል በዚያን ጊዜ ነው የሚገኘው። ቤት ውስጥ እሳት አጠገብ እና በቤተሰብ ሕብረት ላይ፣ ውጤታቸው እስከ ዘላለም የሚዘልቁ ተጽዕኖዎች ያርፋሉ። ከማንኛውም የተፈጥሮ ተሰጥኦዎች በላይ፣ በልጅነት ዓመታት የተመሰረቱ ልማዶች አንድ ሰው በህይወት ውጊያ ውስጥ አሸናፊ ወይም ተሸናፊ መሆኑን ይወስናል፡፡ 377 CGAmh 192.5