የልጅ አመራር
ክፍል 1—ቤት፣ የመጀመሪያ ትምህርት ቤት
ምዕራፍ 1—የቤት ትምህርት ቤት አስፈላጊነት
ትምህርት በቤት ይጀምራል— የልጅ ትምህርት መጀመር ያለበት በቤት ነው፡፡ የርሱ የመጀመሪያ ትምህርት ቤት እዚህ ነው፡፡ እዚህ ወላጆች መምህር በመሆን፣ በሕይወት ጉዳና ውስጥ መመሪያ የሚሆነውን ትምህርት - አክባሪነትን፣ መታዘዝን፣ ፈርሃ እግዚአብሔርንና ራስን መግዛትን መማር አለበት፡፡ የቤት ውስጥ ትምህርት ተጽዕኖ ለመልካምም ሆነ ለክፉ የማያጠራጥር ኃይል አለው፡፡ በብዙ አንጻር ዝግ ያለና ቀስ በቀስ የሚሄድ ነው፣ ነገር ግን በትክክለኛው መንገድ ከተከናወነ፣ ለእውነትና ለጽድቅ አድማሱ ሰፊ የሆነ ኃይል አለው፡፡ ልጆች እዚህ ጋር ትክክለኛው መመሪያ ካልተሰጣቸው፣ ሰይጣን ራሱ በመረጣቸው ወኪሎች ያስተምራቸዋል፡፡ ስለዚህ የቤት ውስጥ ትምህርት ምን ያህል አስፈላጊ ይሆን! 1 CGAmh 17.1
መሠረት የሚጣለው እዚህ ጋር ነው፡- የአካል፣ የአዕምሮና የመንፈሳዊ ትምህርትን መስጠት በሁሉም ወላጆች ላይ የተጣለ ግዴታ ነው፡፡ የልጁን ምዛናዊና ሥነ-ልኬቱን የጠበቀ ባህሪይ ማረጋጋጥ የእያንዳንዱ ወላጅ ዓላማ መሆን አለበት፡፡ ይህ ቀላል የሚባል ጥልቀትና ጠቀሜታ ያላው ሥራ አይደለም— ከትዕግስትና ተግቶ የመስራት ጥረት የማይተናነስ በጥንቃቄ ማሰብ እና ፀሎትን የሚፈልግ ተግባር ነው፡፡ ትክክለኛ መሠረት መጣል አለበት፣ ጠንካራና ጽኑ መዋቅር መቆም አለበት፤ ከዚያም በኋላ የግንባታ፣ የማለስለስ እና ፍፁም የማድረግ ሥራ መቀጠል አለበት፡፡ 2 CGAmh 17.2
ሕጻናትን ከዚህ መብት ውጭ ማንኛውንም ነገር ከልክሏቸው—ወላጆች ሆይ፣ ቤቶቻችሁ ልጆቻችሁ ለላይኛው ቤት የሚሰናዱበት የስልጠና ማዕከል መሆኑን አስታውሱ፡፡ በልጅነታቸው ዓመታት መቀበል ካለባቸው ትምህርት ውጭ ያሉትን ማናቸውንም ነገሮች ከልክሏቸው፡፡ ትዕግስት ያለሽ ቃላቶችን አትፍቀዱ፡፡ ልጆቻችሁ ትሁትና ትዕግስተኞች ይሆኑ ዘንድ አስተምሯቸው፡፡ በዚህ አይነት ሁኔታ እነርሱን ለኃይማኖታዊ ጉዳዮች አገልግሎት ማዘጋጀታችሁ ነው፡፡3 CGAmh 17.3
ቤት ልጆችና ወጣቶች ለጌታ አገልግሎት ብቁ የሚሆኑበት፣ በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ያለውን ከፍተኛ ትምህርት ለመግባት የሚዘጋጁበት፣ የመሰናዶ ትምህርት ቤት መሆን አለበት፡፡ 4 CGAmh 18.1
ሁለተኛ ሥፍራ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም— ቤት ውስጥ የሚሰጥ ትምህርት ሁለተኛ ሥፍራ የሚሰጠው ጉዳይ እንደሆነ እንዳይቆጠር፡፡ በእውነተኛው ትምህርት ውስጥ ግንባር ቀደም ሥፍራ ይይዛል፡፡ አባቶችና እናቶች የልጆቻቸውን አዕምሮ የመቅረጽ አደራ ተሰጥቷቸዋል፡፡ 5 CGAmh 18.2
“ቀንበጥ ሲስተካከል፣ ዛፍ ይቃናል” የሚለው ምሳሌያዊ አነጋገር እንዴት አስገራሚ ነው! ይህ በልጆቻችን ሥልጠና ላይ ተግባራዊ መሆን አለበት፡፡ ወላጆች ሆይ፣ ልጆቻችሁን በልጅነታቸው ዓመታት ማሠልጠን በእናንት ላይ የተጣለ ቅዱስ አደራ መሆኑን ታስታውሳለችሁ? እነዚህን ለጋ ተክሎች፣ ወደ ጌታ የአትክልት ቦታ አዛውረው ለመትከል በጥንቃቄ ሊሰለጥኑ ይገባል፡፡ የቤት ውስጥ ስልጠና በማናቸውም አይነት ሁኔታዎች ችላ ሊባል አይገባም፡፡ ይህን ችላ የሚሉ ሰዎች የኃይማኖት ተግባራቸውን ችላ እያሉ ናቸው፡፡ 6 CGAmh 18.3
የቤት ትምህርት ታላቅ ሰፊው ገጽታ— የቤት ውስጥ ትምህርት ትልቅ ትርጉም ያለው ነው፡፡ አብርሃም የታማኞች አባት ተብሎ ተጠራ፡፡ የእግዚአብሔር ሰው በመሆን ጉልህ ምሳሌ ካደረጉት ነገሮች ምክንያቶች ውስጥ አንዱ በቤት ውስጥ ለእግዚአብሔር ሕግጋት ያሳየው ጥብቅ አቋም ነበር፡፡ የቤት ውስጥ ኃይማኖትን ዓለማው አደረገ፡፡ በእያንዳንዱ ቤት ውስጥ የሚሰጠውን ትምህርት የሚያውቅና፣ የዚህን ትምህርት ተጽዕኖ የሚመዝን እርሱ፣ “ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤቱ እንዲያዝዝ አውቃለሁና” ሲል ተናግሯል፡፡7 ልጆቻቸውን የርሱን መስፈርቶች ያስተምሩ ዘንድ እና ፣ እርሱ ከሕዝባቸው ጋር ያደረገውን ግንኙነት ይላመዱ ዘንድ ለማድረግ እግዚአብሔር ዕብራውያንን ያዛቸዋል፡፡ ቤትና ትምህርት ቤት አንድ ነበሩ፡፡ እንግዳ ቋንቋዎች በሚነገርበት ሥፍራ፣ ወዳጁ የአባት እና የእናት ልብ ለልጆቻቸው ምሪት መስጠት ነበረባቸው፡፡ የእግዚአብሔር ሐሳቦች በቤት ውስጥ ከዕለታዊ ክስተቶች ጋር የተገናኙ ነበሩ፡፡ እግዚአብሔር ህዝቡን ነፃ ያወጣበት ታላላቅ ሥራዎች በአንደበተ ርቱዕነት እና በአክብሮታዊ ፍርሃት ተነግረዋል፡፡ ስለ እግዚአብሔር ጥንቃቄ እና ስለወደፊቱ ህይወት የሚያወሱ ታላላቅ እውነቶች በሕጻናት አዕምሮ ውስጥ ተተክለው ነበር፡፡ አዕምሮአቸው ከእውነተኛው, ከመልካሙ እና ውብ ከሆነው ጋር ተላመደ፡፡ CGAmh 18.4
ቅርጻ ቅርጾችና ተምሳሌቶችን በመጠቀም የተሰጠው ትምህርት የተብራራ ሲሆን ይህም በአዕምሮ ላይ ሰርጸዋል፡፡ በእነዚህ ተምሳሌታዊ ምስሎች አማካኝነት ልጁ ገና ከሕፃንነቱ ጀምሮ ወደ ምስጢሮች, ወደ ጥበብ እና ወደ አባቶቹ ተስፋ ተነሳሽነት ይኖረው ነበር፣ በአስተሳሰብ እና በስሜት እንዲሁም ተስፋ በማድረግ፣ ከሚታየውና ከጊዜያዊ ወደ ማይታየውና ዘላለማዊ ወደ ሆነው ይመራ ነበር፡፡7 CGAmh 19.1
የየዕለቱን የትምህርት-ቤት ተግባር የሚቀድም እንዲሁም የሚያዘጋጅ ነው— የወላጆች ስራ ከመምህሩ ስራ ይቀድማል፡፡ እነርሱ በቤት የሚሰጥ ትምህርት ማለትም የአንደኛ ክፍል ትምህርት የሚሰጥበት ትምህርት ቤት አላቸው፡፡ በጥንቃቄ እና በጸሎት ኃላፊነታቸውን ለማወቅ እና ለመሥራት የፈለጉ እንደሆነ፣ ከመምህር መመሪያዎችን ይቀበሉ ዘንድ ልጆቻቸውን ወደ ሁለተኛው ክፍል እንዲገቡ ያዘጋጃሉ፡፡ 8 CGAmh 19.2
ባህሪይን ይቀርጻል— ቤት በእርግጥም የልጆች ባህሪይ በሰማያዊው ቤተ መንግስት ተምሳሌት የሚቀረጽበት ሥፍራ ሊሆን ይችላል፡፡10 CGAmh 19.3
ትምህርት በናዝሬቱ ቤት ውስጥ—ኢየሱስ ትምህርቱን በቤት ውስጥ አግኝቶ ነበር፡፡ እናቱ የመጀመሪያ ሰብዓዊ አስተማሪው ነበረች፡፡ እርሱ ከከንፈሮቿና ከነቢያት መጻሕፍት፣ ስለ ሰማያዊ ነገሮች ተምሯል፡፡ በገበሬ ቤት ውስጥ ይኖሩ የነበረ ሲሆን የቤቱን ሸክም ለመሸከም ያለውን ድርሻ በታማኝነት እና በደስታ ያከናውን ነበር፡፡ የሰማይ አለቃ የነበረው በፍቃዱ የሚያገለግል፣ ተወዳጅ እና ታዛዥ ልጅ ሆነ፡፡ ሙያ በመማር፣ ከዮሴፍ ጋር በመሆን በእጆቹ በአናጺዎቹ ሱቆች ውስጥ ነበር፡፡ 9 CGAmh 19.4