የልጅ አመራር

11/85

ምዕራፍ 9—ራስን ለማሻሻል የተደረገ ጥሪ

ቀጣይነት ያለው ለውጥ አስፈላጊ ነው—የእናት ሥራ ልጆቿን ወደ የላቀ እና እጅግ የላቀ ክንውን ትመራቸው ዘንድ በራሷ ሕይወት ውስጥ ቀጣይነት ያለው ለውጥን የሚጠይቅ አይነት ሥራ ነው፡፡ ነገር ግን ሰይጣን የወላጆችን እና የልጆችን ነፍሳት ለመያዝ ሲል ዕቅዶችን ይዘረጋል፡፡ እናቶች ከቤት ኃላፊነቶችና ጨቅላ ልጆቿን በጥንቃቄ ከማሰልጠን ወደ ራስ እና ወደ ዓለም አገልግሎት ተወስደዋል፡፡ 103 CGAmh 67.1

እናቶች ለሌላ ምክንያት ብለው ሳይሆን፣ ለልጆቻቸው ሲሉ የአዕምሮ የማሳብ ችሎታዎቻቸውን ማሳደግ አለባቸው፣ ምክንያቱም በሥራቸው ንጉስ በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ከሚሰራ የላቀ ኃላፊነት ተሸክመዋል፡፡ የተሰጣቸው የኃላፊነት ክብደት የሚሰማቸው ወይም ልዩ ተግባራቸውን በትዕግስት እና ራስን በማሳደግ ጠንቃቃ ጥረት ብቃት ማግኘት እንዳለቸው የሚገነዘቡ ጥቂት እናቶች ናቸው፡፡ CGAmh 67.2

በመጀመሪያ፣ እናት የተበላሸ ወይም አንድ-መዳረሻ ተኮር ባህሪይ እንዳይኖራት እና የጉድለቷን አሻራ ወይም ቅብዝብዝነቷን ልጇ ላይ እንዳታሰርፍ፣ ችሎታዎቿን ሁሉ እና የልብና የአዕምሮን ስሜት በጥብቅ ሥርዓት ማስያዝና ማሳደግ አለባት፡፡ አያሌ እናቶች ወደ ጋብቻ ሕይወት ሲገቡ በፈቃደኝነት የተቀበሉትን ኃላፊነት ተቀባይነት ባለው ሁኔታ ለማከናወን፣ በዓለማቸውና ባህሪያቸው ውስጥ ያለውን አዎንታዊ ለውጥ አስፈላጊነትን ለማየት መንቃት አለባቸው’ የሰብዓዊውን ዘር ተምኔትን ወሳኝ በሆነው በእነዚህ ነገሮች ላይ ተገቢውን ትኩረት የምትሰጥ ከሆነ የሴቶች የጠቃሚታቸው ልክ ገደብ የለሽ እስኪሆን ደረስ መንገድ እና ተጽዕኖዋ የሰፋ ይሆናል' 2 CGAmh 67.3

ዘወትር በጥበብና ብቃት ማደግ—እናቶች፣ በጥበብና ብቃት ማደግ ከፈለጉ፣ ከሁሉም በላይ ከአሳቢነትና ከምርምር ጋር ራሳቸውን ማላመድ አለባቸው’ በዚህ መንገድ ላይ የሚጸኑት ራሳቸው ጉድለት አለብን ብለው በሚያስቡበት ነገር ላይ ችሎታ እያገኙ እንደሆነ ወድያው ይረዳሉ፤ እነርሱ የልጆቻቸውን ባህሪይ ትክክለኛ አድርገው መቅረጽን እየተማሩ ነው’ ለዚህ ሥራ የተሰጠ የተግባር እና የሐሳብ ውጤት በእነርሱ መታዘዝ፣ በእነርሱ ነገሮችን የማቅለል፣ በእነርሱ በመጠን የመኖርና ንጽህና ይታያል’ ይህ ውጤት የተደረገውን ጥረት ሁሉ አትረፍርፎ መልሶ ይከፍላል፡፡ CGAmh 68.1

እናቶች ዘወትር አዕምሮአቸውን እና ልባቸውን ማሻሻልን ዘወትር ይሹ ዘንድ እግዚአብሔር ይፈልጋል፡፡ ልጆቻቸውን በማስተማር እና በማሰልጠን ለርሱ የሚሰሩት ሥራ እንዳላቸው ሊሰማቸው ይገባል፤ እናም ሙሉ በሙሉ አቅማቸውን ማሻሻል በቻሉ ቁጥር፣ እንደ ወላጆች በሥራቸው ይበልጥ ብቃት ያላቸው ይሆናሉ፡፡ 104 CGAmh 68.2

ወላጆች በማሰብ ችሎታ እና በግብረ-ገብ ማደግ አለባቸው—አዕምሮአቸውን ማሳደግ እና ልባቸውን በንጹህና ማቆየት የእናቶች ኃላፊነት ነው፡፡ የልጆቻቸውን አዕምሮ ለማሻሻል ብቃት ይኖራቸው ዘንድ፣ የማሳብ ችሎታዎቻቸውን እና ግብረ-ገብን ለማሻሻል በአቅማቸው የሚችሉትን ማናቸውንም መንገዶች ማሻሻል አለባቸው፡፡ 105 CGAmh 68.3

ወላጆች በክርስቶስ ትምህርት ቤት ዘወትር የሚማሩ መሆን አለባቸው፡፡ ክርስቶስ እንዳደረገው ነገሮችን ቀለል በማድረግ የፈቃዱን እውቀት ወጣት የእግዚአብሔር ቤተሰብ አባላትን ማስተማር ይችሉ ዘንድ ማታደስ እና ኃይል ያስፈልጋቸዋል፡፡ 106 CGAmh 68.4

አስገራሚው የክርስቲያን ባሕል ኃይል—ወላጆች ስለ አስገራሚው የክርስቲያን ባሕል ኃይል ለመረዳት ገና አልነቁም፡፡ ባልተለመደ መልኩ ችላ የተባሉት ሊሰራባቸው የሚገባ የእውነት ማዓድናት አሉ፡፡ ይህን ግድ ያለሽ ችላ ባይነት እግዚአብሔር አያጸድቀውም፡፡ ወላጆች፣ በተቀባ አይን ይህን ጉዳይ እንድትመለከቱ እግዚአብሔር ይጠራችኋል፡፡ እናንት ገና ላይ ላዩን ብቻ ነው የገፈፋችሁት፡፡ ለረጅም ጊዜ ችላ የልከውን ተግባርህን ጀምር፣ እና ያኔ እግዚአብሔርም ይተባበርሃል፡፡ ተግባርህን በሙሉ ልብህ ፈጽም፣ እና እንትሻሻል እግዚአብሔር ይረዳሃል፡፡ ወንጌልን ወደ ቤትህ ሕይወት ውስጥ በማምጣት ጀምር፡፡ 107 CGAmh 69.1

እኛ አሁን በእግዚአብሔር ቤተ ሙከራ ውስጥ ነን፡፡ ከእኛ አብዛኞቻችን ካባ ላይ ያለን ሻካራ ድንጋዮች ነን፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔርን እውነት እንድንሸከም ወደ እኛ ሲመጣ፣ ከቅዱሳን መልአክት ጋር ብቻ ሳይሆን፣ ነገር ግን ከሰማይ ንጉስ ራሱ ጋር በምንገናኝበት ሥፍራ፣ በሰማያዊው ቤተ መቅደስ ውስጥ እያንዳንዱ ጉድለት ይወገድና እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ለማብረቅረቅ መዘጋጀት አለብን፡፡ 108 CGAmh 69.2

ዓለማው— ፍጽምና ነው— እናቶች፣ ከንቱ፣ ጥቅም ላይ እያለ ጠፊ የሆነውን አላስፈላጊ ተግባርን አታስወግዱም? ለዘለዓለም በሚኖር ሥራ ላይ ጥበቡ እንዲመራችሁና ጸጋው እንዲራዳችሁ፣ ወደ እግዚአብሔር መጠጋትን አትሹምን? ልጆቻችሁ በባህሪያቸው ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ አልሙ፡፡ እንደዚህ አይነቱ ብቻ እግዚአብሔርን እንደሚያይ አስታውሱ፡፡… CGAmh 69.3

አያሌ ወላጆች እግዚአብሔር የሰጣቸውን ሥራ ችላ ብለዋል፡፡ ራሳቸውም ከንጽህናና ከቅድስና ርቀዋል፣ አይኖቻቸው የክርስቶስን የባህሪይ ፍጽምና በማየት እንደሚደነቅ ሰው የልጆቻቸውን ጉድለቶች አይመለከቱም፡፡8 CGAmh 69.4

ሁነኛ እናት መሆን እንዴት እንደሚቻል—ራሷን በጥሩ ሁኔታ በመረጃዎች ታንጽ ዘንድ፣ ለባለቤቷ ባልደረባ ትሆን ዘንድ፣ እና በማደግ ላይ ከሚገኘው የልጆችዋ አዕምሮ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዲኖራት፣ አሰልቺ የቤተሰብ ሥራ ብቻ ላይ ከመዘፈቅ ይልቅ፣ ሚስት እና እናት ለማንበብ ጊዜ ሊኖራት ይገባል፡፡ ለላቀ ሕይወት ተወዳጆቿ ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር አሁን የእርሷ የሆኑ አጋጠሚዎችን በጥበብ ትጠቀም፡፡ ተወዳጁን አዳኝ የየዕለት ባልደረባ እና የቅርብ ጓደኛዋ ለማድረግ ጊዜ ትውሰድ፡፡ የእርሱን ቃል ለማጥናት ጊዜ ትውሰድ፣ ከልጆቿ ጋር ወደ መስክ ለመሄድ እና በውብ የእጅ ሥራዎቹ አማካይነት ከእግዚአብሔር ለመማር ጊዜ ትውሰድ፡፡ CGAmh 69.5

ደስተኛ እና ፍልቅልቅ ትሁን፡፡ እያንዳንዱን ሰዓት ፍጻሜ በሌለው የሥፌት ሥራ ከምታጠፋ፣ ከየቀኑ ተግባራት በኋላ ቤተሰብ የሚገናኝበት፣ ምሽትን ደስተኛ የማህበራዊ ጊዜ ታድርግ፡፡ አብዛኞቹ ወንዶች የክለብ ቤት ወይም ቡና ቤት ከመሄድ ይልቅ የቤታቸውን ማህበራዊነት የሚመርጡት በዚህ አይነት ሁኔታ ነው፡፡ ብዙ ወንዶች ልጆች ከጎዳናና ማዕዘን ላይ ከሚገኙ የመጠጥ ቤቶች ሊጠበቁ ይችላሉ፡፡ ብዙ ሴቶች ልጆች ከከንቱና ከአሳሳች ጓደኝነቶች ይተርፋሉ፡፡ የቤት ተጽዕኖ ለወላጆች እና ለልጆች እግዚአብሔር እንደወጠነው፣ የዕድሜ ልክ በረከት ይሆናል፡፡ 109 CGAmh 70.1

የተለመደውን ሕይወት ስኬታማ ያድርጉ—ለአንዲት እናት የተሰጠ ምክር— ዝንባሌሽን መከተል የለብሽም፡፡ በሁሉም ነገር ትክክለኛውን ምሳሌ ለማስቀረት እጅግ ጠንቃቃ መሆን አለብሽ፡፡ ፍዝ መሆን የለብሽም፡፡ የተኙ ኃይሎችሽን አንቂያቸው፡፡ ንቁና ጠቃሚ በመሆን ራስሽን ለባልሽ አስፈላጊ አድርጊ፡፡ በእያንዳንዱ ነገር ለእርሱ በረከት ሁኚ፡፡ መተግበር ያለባቸውን ተግባራቶችሽን መስራት ጀምሪ፡፡ ቀላል፣ የማይማርኩ እና የማይከብዱ፣ ነገር ግን እጅግ ተፈላጊ የሆኑ ከዕለት ተዕለት ሕይወት ጋር ግንኙት ያላቸውን ሥራዎችን እንዴት በፍጥነት መሥራት እንደሚቻል አጥኚ፡፡…. CGAmh 70.2

የዕለት ተዕለት ሕይወትሽ ላይ ስኬታማ ለመሆን ሞክሪ፡፡ የሚስት እና እናትን ሥፍራ ማግኘት ማለት አንቺ ከምታስቢው የላቀ ትርጉም ያዘለ ነው፡፡… የዕለት ተዕለት ሕይወትን ባሕልና ልምድ ያስፈልግሻል፡፡ የዚህ ሕይወት ውጤት የሆኑትን ሕብርነትን፣ መነሳሳት፣ ቆራጥነት የተሞላበት ጥረት፣ እና የፈቃድን ኃይል ማሳደግ ያስፈልግሻል፡፡10 CGAmh 70.3

ሥራ እጅግ የሚበዛባቸው ወላጆች— አያሌ ወላጆች አዕምሮአቸውን ለማሻሻል፣ ስለ ተግባራዊ ሕይወት ልጆቻቸውን ለማስተማር፣ ወይም የክርስቶስ መንጋ በጎች መሆን እንዴት እንዳለባቸው ለማስተማር ብዙ ሥራ ስላለብን አንችልም ሲሉ አቤቱታ ያቀርባሉ፡፡ 110 CGAmh 71.1

ወላጆች ኃጢአት ላይ ልባቸውን ከማጠንከር፣ እነርሱን ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ማናቸውንም አይነት ሕማም እና ስቃይ እና ክፋት ልጆቻቸው ላይ ከሚያስተላልፍ ነገር መጠበቅን ችላ ማለት የለባቸውም፡፡ ወላጆች በትክክል ራሳቸውን በማስተማር፣ በሰማያት ይገዛቸው ዘንድ ልጆቻቸውን ማስተማር አለባቸው፡፡ 111 CGAmh 71.2

ወላጆች ምክር መቀበል አለባቸው—እነርሱ በኃይማኖት የለሽ ግድየለሽነት ውስጥ ሲያንቀላፉ፣ ሰይጣን በልጆቻቸው ልብ ውስጥ አድጎ የሞትን መኸር ለመሰብሰብ የሚያስችለውን ዘር ይዘራል፡፡ ሆኖም ግን እንደነዚህ አይነቶቹ ወላጆች በስህተቶቻቸው ላይ ምክር ሲሰጣቸው ቅር ይሰኛሉ፡፡ ምክር የሚሰጣቸውን ሰው፣ በልጆቼ መካከል ጣልቃ ትገባ ዘንድ ምን መብት አለህ? ብለው የሚየይቁ ይመስላሉ፡፡ ነገር ግን ልጆቻቸውስ ጭምር የእግዚአብሔር ልጆች አይደሉምን? ኃላፊነታቸውን ችላ የማለታቸውን ኃጢአት እርሱ እንዴት ነው የሚመለከተው? ልጆቻቸውን የሰይጣን ፈተናዎች እስፖርት እንዲሆኑ ለምን ወደ ዓለም እንዳመጧቸው ሲጠየቁ ምን ምላሽ ይሰጣሉ? 112 CGAmh 71.3

ምክርን ከሌሎች ለመቀበል የተዘጋጃችሁ ሁኑ፡፡ ልጆቻችሁን እንዴት መያዝ እንዳለባችሁ ወይም ልጆቻችሁ ምን አይነት ባህሪይ ማሳየት እንዳለባቸው የወንድሞች ወይም የእህቶች ጉዳይ አይደለም የሚል ስሜት አይሰማችሁ፡፡14 CGAmh 71.4

እርስ በእርስ የመመካከር ጠቀሜታ [ማሳሰቢያ፡- እዚህ ጋር የተጠቀሰው በመንፈሳዊ ስብሰባ ውስጥ እንደነበረው አይነት የቡድን ጥናትን ነው፡፡]—እግዚአብሔር እጅግ የተቀደሰ ሥራ በእጃችን ላይ አሳልፍ ሰጥቶናል፣ ይህንንም ሥራ ለመስራት ብቁ እንሆን ዘንድ፣ መመሪያ ለመቀበል መገናኘት አለብን፡፡… በቤታችን ውስጥ ያለውን ሥራ ለመረዳት አንድ ላይ በመገናኘት የመለኮትን ንካት መቀበል ያስፈልጋናል፡፡ ወላጆች ወንዶች እና ሴቶች ልጆቻቸው ዓለም ውስጥ ብርሃን ይሆኑ ዘንድ ከቤታቸው ቤተ መቅደስ በመሰልጠን እና በመማር እንዴት መላክ እንዳለባቸው መረዳት ያስፈልጋቸዋል፡፡ 113 CGAmh 72.1

ከመንፈሳዊ ስብሰባ ስለ ቤታችን ኃላፊነት የተሻለ መረዳት እንወስዳለን፡፡ እግዚአብሔር እህቶቻችን በቤታቸው እንዲሰሩ የሚፈልግባቸውን ሥራ የሚማሯቸው ትምህርቶች እዚህ አሉ፡፡ እነርሱ ባሎቻቸውን እና ልጆቻቸውን ሲናገሩ የትህትና ንግግሮችን ማሳደግን መማር አለባቸው፡፡ እያንዳንዱን የቤተሰብ አባል በእግዚአብሔር ሥርዓት ሥር ለማድረግ እንዴት መርዳት እንዳለባቸው ማጥናት አለባቸው፡፡ አባቶችና እናቶች ቤታቸውን አስደሳች እና ማራኪ የማድረግ ግዴታ እንዳለባቸው እና መታዘዝ በቁጣና በማስፈራራት መገኘት እንደሌለበት መገንዘብ አለባቸው፡፡ አያሌ ወላጆች በቁጣ መገንፈል ጥሩ ውጤት እንደማያመጣ ገና መማር ይገባቸዋል፡፡ ብዙዎች በትህትና ልጆቻቸውን የመናገርን አስፈላጊነትን አይገነዘቡትም፡፡ እነዚህ ትናንሽ ልጆች በዋጋ እንደተገዙና እነርሱ የተገዙ የጌታ ኢየሱስ ንብረቶች እንደሆኑ አያስታውሱም፡፡16 CGAmh 72.2