የልጅ አመራር
ክፍል 18—የኃይማኖታዊ ልምድን መጠበቅ
ምዕራፍ 77—መጽሐፍ ቅዱስ ቤት ውስጥ
መጽሐፍ ቅዱስ ሁለገብ መጽሐፍ ነው— በሰፊው ዘይቤውና ርዕሰ ጉዳዩ መጽሐፍ ቅዱስ የእያንዳንዱን አእምሮ ፍላጎት የሚቀሰቅስ እና የእያንዳንዱን ልብ የሚስብ ነገር አለው፡፡ በገጾቹ ውስጥ እጅግ ጥንታዊ ታሪክ ይገኛል፤ ለሕይወት እጅግ ታማኝ የሆነ የሕይወት ታሪክ፤ መንግሥት የመንግሥትን የሚቆጣጠርበት፣ ቤተሰብ የሚተዳደርበት መርኾዎች— እነዚህ የሰው ጥበብ በጭራሽ የማይተካከላቸው መርሆዎች ናቸው። ስሜትን የሚነካ እና በጣም አሳዛኝ፣ እጅግ በጣም ጥልቅ ፍልስፍናን፤ እጅግ ጣፋጭ እና የላቀ ግጥምን የሚይዝ ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ ጽሑፎች በንጽጽር እንኳ ከማንኛውም ሰብዓዊ ደራሲያን ሥራዎች ጋር በእሴት ሊወዳደር የማይችል ነው፤ ነገር ግን ከታላቁ ማዕከላዊ አስተሳሰብ ጋር በሚዛመድበት ጊዜ እጅግ በጣም ሰፊ፣ እጅግ በጣም ትልቅ ዋጋ ያላቸው ናቸው፡፡ በዚህ አስተሳሰብ መሠረት ሲታይ እያንዳንዱ ርዕስ አዲስ ትርጉም አለው፡፡ እጅግ በቀላል መንገድ በተገለጹት እውነቶች ውስጥ እንደ ሰማይ ከፍ ያሉ እና ዘለአለማዊነትን አቅፎ የሚይዙ መርሆዎች ይገኙባቸዋል፡፡ 1011 CGAmh 482.1
የእግዚአብሔር ቃል በእውነት ውድ በሆኑ ጌጣጌጦች የተትረፈረፈ ነው፣ በመሆኑም ወላጆች ከሳጥኖቻቸው ሊያወጡዋቸው እና እውነተኛ ብርሃናቸውን ለልጆቻቸው ሊያቀርቡ ይገባል...፡፡ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ወድ ክምችቶችን ማግኘት የምትችሉበት እና ክርስቲያኖች እንደመሆናችሁ መጠን ለመልካም ሥራ ሁሉ ራሳችሁን የምታዘጋጁበት መሆን አለበት፡፡1012 CGAmh 482.2
በውስጡ እግዚአብሔር የተትረፈረፈ ግብዣ ያቀርባል— ቃሉን የማጥናት መብት ለእኛ በመስጠት፣ ጌታ የተትረፈረፈ ግብዣ በፊታችን አዘጋጅቷል። በሥጋውና ደሙ፣ በመንፈሱና በሕይወቱ የተወከለውን ቃል በመመገብ የሚገኙ ብዙ ጥቅሞች ናቸው፡፡ ከዚህ ቃል በመካፈል መንፈሳዊ ጥንካሬያችን ይጨምራል፤ በጸጋ እና በእውነት እውቀት እናድጋለን። ራስን የመቆጣጠር ልማዶች ይቀረጻሉ፣ ይጠነክሩማል፡፡ የልጅነት ድክመቶች— ብስጭት፣ ግትርነት፣ ራስ ወዳድነት፣ የችኮላ ቃላት፣ ስሜታዊ ድርጊቶች— በመጥፋት በእነርሱም ምትክ የክርስቲያን ወንድ እና ሴት ፀጋዎች ይዳብራሉ። 1013 CGAmh 482.3
የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች እና ምሳሌዎች ቆንጆ ትምህርቶች፣ የእግዚአብሔር ቅዱስ ቃል ንፁህ፣ ቀላል መመሪያ ለእናንተ እና ለልጆቻችሁ መንፈሳዊ ምግብ ነው፡፡ CGAmh 483.1
አቤት፣ በፊታችሁ እንዴት ያለ ሥራ ነው ያለው! እግዚአብሔርን በመውደድ እና በመፍራት ትጀምራላችሁን? በቃሉ አማካይነት ከእግዚአብሔር ጋር ትገናኛላችሁን? 1014 CGAmh 483.2
የታማኝነት መመዘኛ ነው— ስህተቶቻቸውን በማረም፣ አዕምሮአቸውን በመክፈት እና በመምራት ቁጣን የሚቀሰቅሱ የግልፍተኝነት ስሜቶችን እና ክፉ ቃላትን በመገደብ እና በመቆጣጠር በላቀ ሁኔታ ተፈላጊውን ውጤት ማስገኘት የሚያስችለው የእግዚአብሔር ቃል አእምሮ ላይ ተጽዕኖ እንዲያደርግ እና የአስተሳሰብ መመዘኛ እንዲሆን በፍትሃዊነት ለወጣቶች መቅረብ አለበት፡፡ ይህ የመጽሐፍ ቅዱስን መስፈርት ለማሟለት የሚደረግ የልጆች ሥልጠና ጊዜን፣ ጽናትንና ጸሎትን ይጠይቃል። ስለ ቤት አንዳንድ ነገሮች ችላ ከተባሉ ይህ መከተል ተገቢ ነው፡፡1015 CGAmh 483.3
ተቀባይነትን ያገኙ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች አእምሮን ከምድራዊነቱ እና ከውድቀቱ ከፍ ያደርጉታል፡፡ የእግዚአብሔር ቃል የተፈለገውን ያህል አድናቆት ቢያገኝ ኖሮ፣ ወጣቶችም ሆኑ አረጋውያን ፈተናዎችን ለመቋቋም የሚያስችላቸውን ውስጣዊ ታማኝነት እና የመርህ ጥንካሬ ያገኙ ነበር።6 CGAmh 483.4
የእስራኤል ቅዱስ የሰውን ልጅ የማሰብ ችሎታን ሁሉ የሚገዙ ደንቦችን እና ሕጎችን አሳውቆናል፡፡ እነዚህ “ቅዱስ፣ ጻድቅ፣ መልካም” የተባሉ እነዚህ መመሪያዎች በቤት ውስጥ የድርጊት መመዘኛን ለመመስረት ነው። እነርሱ የክርስትና ኃይማኖት መሠረት በመሆናቸው ያለ ኃጢአት ከእነርሱ መለየት አይቻልም፡፡ 1016 CGAmh 483.5
አእምሮን ያጠናክራል— መጽሐፍ ቅዱስ እንደ አስፈላጊነቱ ቢጠና ኖሮ ሰዎች በአእምሮ ጠንካራ መሆን በቻሉ ነበር፡፡ በእግዚአብሔር ቃል ላይ የተስተናገዱ ርዕሰ ጉዳዮች፣ ቀለል ያለ የንግግሩ ክብር፣ እርሱ ለአዕምሮ የሚያቀርባቸው ክቡር ጭብጦች በሰው ውስጥ በሌላ መልኩ ሊዳብሩ የማይችሉ ችሎታዎችን ያዳብራሉ፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለዓይነ-ሕሊና ወሰን የሌለው መስክ ተከፍቷል፡፡ ተማሪው ታላላቆቹ ጭብጦችን ከማሰላሰል፣ ከፍ ካሉ ምስሎቹ ጋር ከመገናኘት፣ ስለ እነዚያ ከንቱ ባህሪያት አንድም ነገር የማይናገር ምንጩ የሰው ልጅ የሆነ ማንኛውንም ሥራ በማንበብ ጊዜውን ከሚያሳልፍ ይልቅ በአስተሳሰብ እና በስሜቱ ንጹህ እና የከበረ ይሆናል፡፡ የልጅነት አእምሮዎች ከፍተኛ የጥበብ ምንጭ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል ቸል ሲሉ ክቡር ወደ ሆነው እድገታቸው መድረስ ያቅታቸዋል፡፡ ጥሩ አዕምሮ ያላቸው፣ የተረጋጉና ብርቱ አቋም ያላቸው ጥቂት ሰዎች ብቻ እንዲኖረን የሆነበት ምክንያት እግዚአብሔር ስላልተፈራ፣ እግዚአብሔር ስላልተወደደ፣ የኃይማኖት መርሆዎች በሕይወት ውስጥ እንደሚፈለገው ተግባራዊ ስላሆኑ ነው፡፡ CGAmh 484.1
እግዚአብሔር የእውቀት ኃይሎቻችንን ለማዳበር እና ለማጠንከር እንድንችል ማናቸውንም መንገዶች እንድንጠቀም ይፈልጋል…፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ይበልጥ ቢነበብ፣ በላቀ ሁኔታ እውነቶቹን መረዳት ቢቻል ኖሮ፣ እጅግ የተሻለ ብርሃን እና እውቀት ያለን ሰዎች እንሆን ነበር፡፡ ገጾቹን በመመርመር ኃይል ለነፍስ ይሰጣል፡፡ 1017 CGAmh 484.2
ለማህበረተሰብ እና ለሀገር ብልጽግና መሠረት ነው— የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ በጊዜያዊ የሕይወት ግንኙነቶች ውስጥ በሰው ልጅ ብልጽግና ላይ ወሳኝ ተጽዕኖ አለው፡፡ የአንድ ሀገር ብልጽግና የማዕዘን ድንጋይ የሆኑ መሰረታዊ መርሆዎችን የሚገልጥ ሲሆን ይህም የቤተሰብ ከለላ የሆነውን የህብረተሰቡን ደህንነት የተመሰረተበት መርኾዎች — ማለትም በዚህ ውስጥ ማንም ሰው ከዚህ ውጪ በጊዜያዊ ሕይወት ፋይዳ ሰጪነትን፣ ደስታ እና ክብር ማግኘት ወይም መጻኢውን ዘላለማዊ ሕይወት ሊያገኝ የማይችልበት መርሆዎች ናቸው፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ወሳኝ ዝግጅት የማይሆንበት የሕይወት ደረጃ፣ የሰው ተሞክሮ ምዕራፍ የለም፡፡ 1018 CGAmh 484.3
የቅዱሳት መጻሕፍት እውቀት ከለላ ነው— ጢሞቴዎስ ከልጅነቱ ጀምሮ ቅዱሳን መጻሕፍትን ያውቅ ነበር፤ እናም ይህ እውቀት በዙሪያው እርሱን ከበውት ከነበሩ ክፉ ተጽዕኖዎች እና ኃላፊነት ላይ ተድላና የራስ ወዳድነትን ፍላጎቶችን ማርካትን በመምረጥ ፈተና የሚጠብቀው ከለላ ነበር፡፡ ልጆቻችን ሁሉ እንደዚህ አይነቱ ከለላ ያስፈልጋቸዋል፣ በመሆኑም ልጆች ስለ እግዚአብሔር ቃል በአግባቡ የተማሩ ሆነው ማየት የወላጆች እና የክርስቶስ አምባሳደሮች የሥራ አካል መሆን አለበት፡፡ 1019 CGAmh 485.1
መጽሐፍ ቅዱስን መውደድ ተፈጥሮአዊ አይደለም— ወጣቶች አላዋቂ እና ልምድ የሌላቸው ናቸው፣ ደግሞም የመጽሐፍ ቅዱስ እና የቅዱስ እውነቶች ፍቅር በተፈጥሮ አይመጣም። እነርሱን ከሰይጣን ዘዴዎች ለመከለል በዙሪያቸው ከለላ ለመገንባት ከባድ ጥረት ካልተደረገ በስተቀር ለፈተናዎቹ ተገዥ ሆነው በእርሱ ፈቃድ የእርሱ ምርኮኞች ይሆናሉ፡፡ ልጆች ገና በልጅነታቸው የእግዚአብሔር ሕግ መጠይቆች እና ከኃጢአት እድፍ ለመንፃት ቤዛችን በሆነው በኢየሱስ ላይ መታመንን መማር አለባቸው፡፡ ይህን እምነት በየቀኑ፣ በትእዛዝ እና በምሳሌ ማስተማር ተገቢ ነው፡፡ 1020 CGAmh 485.2
በተለይም ወጣቶች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትን ችላ ይላሉ— ጎልማሰውም ወጣቱም መጽሐፍ ቅዱስን ችላ ይላሉ፡፡ እነርሱ እርሱን ጥናታቸው፣ የሕይወታቸው ደንብ አያደርጉትም፡፡ በተለይም በዚህ ቸልተኝነት ወጣቶች ወንጀለኞች ናቸው፡፡ አብዛኛዎቹ ሌሎች መጻሕፍትን ለማንበብ ጊዜ ያገኛሉ፣ ነገር ግን ወደ ዘላለማዊ ሕይወት የሚወስደውን መንገድ የሚያመለክተው መጽሐፍ በየቀኑ አይጠናም፣ ከንቱ ታሪኮች በትኩረት ይነበባሉ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ግን ችላ ተብሏል፡፡ ይህ መጽሐፍ ወደ ከፍታ እና ወደ ቅድስና ሕይወት የሚያደርስ መመሪያችን ነው፡፡ ወጣቶች የፈጠራ ታሪኮችን በማንበብ አስተሳሰባቸው ፈር የለቀቀ ባይሆን ኖሮ ከተነበቡ መጽሐፍት ሁሉ እጅግ ማራኪ መጽሐፍ እንደሆነ ይናገሩ ነበር፡፡ CGAmh 485.3
የወጣትነት አእምሮዎች ከፍተኛ የጥበብ ምንጭ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል ቸል ሲሉ ወደ ክቡር እድገታቸው መድረስ አቅቷቸዋል፡፡ በፈጣሪ ፊት በእግዚአብሔር ዓለም ውስጥ እንደሆንን፤ በእርሱ አምሳል እንደ ተፈጠርን፤ እርሱ እንደሚጠብቀን፣ እንደሚወደን እና እንደሚንከባከበን— እነዚህ ለአስተሳሰብ አስደናቂ ጭብጦች ናቸው፣ ደግሞም አዕምሮን ሰፊ ወደ ሆነ፣ ከፍ ወዳለ የማሰላሰል መስክ ይመራሉ። ስለ እነዚህ ጭብጦች ለማሰላሰል አእምሮን እና ልብን የሚከፍት እርሱ በከንቱ እና ስሜታዊ ርዕሰ ጉዳዮች በጭራሽ አይረካም። 1021 CGAmh 486.1
በልጆች ላይ የወላጆች ንቀት ይንጸባረቃል— ገና በልጅነታቸው እንኳን ልጆች ያስተውላሉ፤ በመሆኑም ወላጆች የእግዚአብሔር ቃል የእነርሱ መመሪያ እና አማካሪ አለመሆኑን ካሳዩ፣ ወደ እነርሱ የመጡትን መልእክቶች ችላ ካሉ፣ “ግድ የለኝም፣ የራሴን መንገድ እከተላለሁ” የሚል ተመሳሳይ የግድየለሽነት መንፈስ በልጆች ላይ ይታያል፡፡ 1022 CGAmh 486.2
ለቃሉ የተከበረ ሥፍራ ስጡ— ታላቅ ብርሃን እንዳገኘ ህዝብ፣ በልማዶቻችን፣ በቃላቶቻችን ፣ በቤት ውስጥ ህይወታችን እና በጓደኝነታችን የከበርን መሆን አለብን። ቃሉን ቤት ውስጥ መመሪያ በማድረግ የከበረ ሥፍራ ስጡት፡፡ በእያንዳንዱ ችግር አማካሪ፣ የእያንዳንዱ አሠራር መለኪያ እንደ ሆነም ይቆጠር፡፡ የእግዚአብሔር እውነት፣ የጽድቅ ጥበብ መሪ እስካልሆነ ድረስ ወንድሞቼ እና እህቶቼ በቤተሰብ ክልል ውስጥ ለማንኛውም ነፍስ እውነተኛ ብልጽግና በጭራሽ ሊኖር እንደማይችል እርግጠኛ ይሆኑ ይሆን? የእግዚአብሔርን አገልግሎት እንደ ሸክም ከመቁጠር የስንፍና ልማድ አእምሮአቸውን ለማውጣት አባቶችና እናቶች ያሉትን ጥረት ሁሉ ማድረግ አለባቸው፡፡ የእውነት ኃይል ቤት ውስጥ የሚቀድስ ወኪል መሆን አለበት።14 CGAmh 486.3
ወላጆች ሥርዓት በሥርዓት፣ በትእዛዝ ለልጆቻችሁ በእግዚአብሔር ቅዱስ ቃል ውስጥ ያለውን መመሪያ ስጧቸው። ይህ በተጠመቅህ ጊዜ ለመሥራት ቃል የገባኸው ሥራ ይህ ነው፡፡ ዓለማዊ ባሕርይ ያለው ምንም ነገር ይህንን ሥራ እንዳትሠሩ እንዳያግዳችሁ፡፡ የአጥንታችሁ አጥንት እና የሥጋችሁ ሥጋ ወይም በጉዲፈቻ ወደ ቤተሰባችሁ የተቀላቀሉ ቢሆኑ የልጆቻችሁን ነፍስ ለማዳን የምትችሉትን ሁሉ አድርጉ፡፡ 1023 CGAmh 487.1
የቤት መማሪያ መጽሐፍ አድርጉት— ወላጆች ሆይ፣ ልጆቻችሁ እግዚአብሔርን እንዲያገለግሉ እና በዓለም ውስጥ መልካም እንዲያደርጉ ልታስተምሯቸው ከፈለጋችሁ መጽሐፍ ቅዱስን የመማሪያ መጽሐፋችሁ አድርጉት። እርሱ የሰይጣንን ተንኮል ያጋልጣል፡፡ እርሱ የሰውን ዘር በእጅጉ ከፍ የሚያደርግ፣ የግብረ ገብ ክፋቶችን የሚገስጽ እና የሚያርም፣ እውነተኛውን እና ሐሰተኛውን ለመለየት የሚያስችለን ጠቋሚ ነው። በቤትም ሆነ በትምህርት ቤት ውስጥ ምንም ቢስተማር፣ መጽሐፍ ቅዱስ እንደ ታላቅ አስተማሪ ግንባር ቀደም ሆኖ ሊቆም ይገባል፡፡ ይህ ሥፍራ ከተሰጠው እግዚአብሔር ይከበራል፣ ልጆችንም በመለወጥ ለእናንተ ይሠራል፡፡ በዚህ ቅዱስ መጽሐፍ ውስጥ የበለጸገ የእውነት እና የውበት ማዕድን አለ፣ እናም ወላጆች ለልጆቻቸው እጅግ ማራኪ ካላደረጉ እራሳቸው ተጠያቂ ናቸው፡፡ 1024 CGAmh 487.2
ፈታኙ ማታለያዎቹን ይዞ ሲመጣ “ተጽፏል” የሚለው ክርስቶስ የተጠቀመበት ብቸኛው መሣሪያ ነበር፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ትምህርት እያንዳንዱ ወላጅ ሊሠራው የሚገባ ታላቅና የተከበረ ሥራ ነው። ትህትና ባለው፣ ደስተኛ አስተሳሰብ እግዚአብሔር የተናገረው እውነት በልጆች ፊት ይቅረብ፡፡ እንደ አባቶች እና እናቶች፣ ትዕግሥትን፣ ደግነትን እና ፍቅርን በመለማመድ፣ እነርሱን ወደ ራሳችሁ በማቅረብ በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ ለልጆች የአርአያ ማስተማሪያ መሆን ትችላላችሁ፡፡ እነርሱ እንዳሻቸው እንዲያደርጉ አትፍቀዱላቸው፣ ነገር ግን ስራችሁ የእግዚአብሔርን ቃል ተግባራዊ ማድረግ እና በጌታ እንክብካቤ እና ተግሰጽ እነርሱን ማሳደግ እንደሆነ አሳዩአቸው፡፡17 CGAmh 487.3
በትጋት፣ በስርዓት ማጥናት— በቤተሰቦቻችሁ ውስጥ የቅዱሳት መጻሕፍትን ጥናት ሥርዓትን ተመልከቱ፡፡ የጊዜያዊነት ባህሪይ ያለውን ማንኛውንም ነገር ችላ አድርጉት፣ ... ነገር ግን ነፍስ የሕይወት እንጀራ እንደምትመገብ እርግጠኞች ሁኑ፡፡ በየዕለቱ የአንድ ሰዓት ወይም የግማሽ ሰዓት ያህል እንኳን በእግዚአብሄር ቃል በደስታ እና በአብሮነት ጊዜ የመስጠትን መልካም ውጤቶችን መገመት አይቻልም፡፡ በተለያዩ ጊዜያት እና በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ ስለ አንድ ርዕሰ ጉዳይ የተነገረውን ሁሉ በማሰባሰብ መጽሐፍ ቅዱስን የራሱ ገላጭ አድርጉ፡፡ ለእንግዶች ወይም ለጎብኝዎች ስትሉ የቤታችሁን ጥናት አታቋርጡ፡፡ ይህን በምታደርጉበት ጊዜ ከመጡ እንዲሳተፉበት ጋብዟቸው፡፡ የዓለምን ትርፍ ወይም ደስታ ከማግኘት ይልቅ የአምላክን ቃል እውቀት ማግኘቱ የበለጠ አስፈላጊ እንደሆነ አድርጋችሁ እንደምታስቡ ይታይ። The Review and Herald, October 9, 1883. 1025 CGAmh 488.1
መጽሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ በትጋት እና በጸሎት ብናጠና በየዕለቱ የተወሰነ አዲስ፣ ግልጽ እና ኃይል ያለውን ውብ እውነት እናገኛለን፡፡19 CGAmh 488.2
ሁሉም የሰንበት ትምህርትን ይማሩ— የሰንበት ትምህርት ለወላጆች እና ለልጆች የእግዚአብሔርን ቃል ለማጥናት እድል ይሰጣቸዋል፡፡ ነገር ግን በሰንበት ትምህርት ውስጥ ሊያገኙት የሚገባቸውን ጥቅም እንዲያገኙ ወላጆችም ሆኑ ልጆች የቀረቡትን እውነታዎች እና እንዲሁም እነዚህ ገሃዶች ለማስተማር ያለሙትን መንፈሳዊ እውነቶችን ለማግኘት በመሻት ትምህርቱን ለማጥናት ጊዜ መስጠት አለባቸው፡፡ በመታየት ላይ ያለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ሙሉ ትርጉም የመፈለግን አስፈላጊነትን በተለይ በወጣቶች አእምሮ ላይ መቅረጽ አለብን፡፡ CGAmh 488.3
ወላጆች፣ የሰንበት ትምህርትን ከልጆቻችሁ ጋር ለማጥናት በየቀኑ ትንሽ ጊዜ መድቡ፡፡ ለቅዱስ ታሪክ ትምህርቶች የተሰጠውን ሰዓት መስዋዕት ከማድረግ ይልቅ አስፈላጊ ከሆነ ማህበራዊ ጉብኝትን አስቀሩ፡፡ ወላጆችም ሆኑ ልጆች ከዚህ ጥናት ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ ከትምህርቱ ጋር የተያያዙ እጅግ አስፈላጊ የቅዱሳት መጻሕፍት ክፍሎች እንደ ሥራ ሳይሆን እንደ ዕድል ማህደረ ትውስታ ውስጥ ይቀመጡ፡፡ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ በእውነት ቃላት ክምችት ይደሰቱ ዘንድ ምንም እንኳን መጀመሪያ ላይ ማህደረ ትውስታው ጉድለት ቢኖረውም በልምምድ ይጎለብታል። ልማድም ለመንፈሳዊ እድገት እጅግ ጠቃሚ የሆነ እገዛ እንዳለው ያረጋግጣል፡፡ 1026 CGAmh 488.4
ወላጆች ስለ እግዚአብሔር ሕጎች እና መስፈርቶች እንዲሁም ስለ ትንቢቶች ልጆቻቸውን ማስተማር ቅዱስ ተግባር እንደሆነ ሊሰማቸው ይገባል፡፡ ልጆቻቸውን በቤት ውስጥ ማስተማር እና እራሳቸውም ለሰንበት ትምህርት ትምህርቶች ፍላጎት ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ከልጆቹ ጋር በማጥናት በትምህርቶቹ ውስጥ ለተገለጸው እውነት ትልቅ ቦታ እንደሚሰጡ ያሳያሉ፣ ደግሞም ለመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት ፍላጎት ለመፍጠር ይረዳሉ፡፡ 1027 CGAmh 489.1
በጥራዝ ነጠቅ እውቀት አትርኩ— የቅዱሳት መጻሕፍትን ጥልቅ እውቀትን የመሻት አስፈላጊነትን ለመገመት ይከብዳል፡፡ የእግዚአብሔር ሰው “ፍጹም እና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ” “በእግዚአብሔር መንፈስ የተሰጠን” “መዳን የሚገኝበትን ጥበብ” እንዲኖረን (2 ጢሞቴዎስ 3: 15- 17) መጽሐፍ ቅዱስ የከበረ ትኩረት ይጠይቃል፡፡ በጥራዝ ነጠቅ ዕውቀት የረካን መሆን የለብንም፣ ነገር ግን እግዚአብሔር የሚናገርበትን ቅዱስ መንፈስ ከጥልቀት ለመጠጣት የእውነትን ቃላት ሙሉ ትርጉም መማርን መሻት አለብን፡፡ 1028 CGAmh 489.2
በልጁ ተሞክሮ ላይ ትምህርቶችን ተግብሩ— ልጆችን መጽሐፍ ቅዱስን በማስተማር ረገድ የአእምሯቸውን ዝንባሌ፣ እነርሱ የሚማረኩባቸውን ነገሮች በመመልከት እና መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እነዚህ ነገሮች ምን እንደሚል ለማየት ፍላጎታቸውን በማነሳሳት ብዙ እናተርፋለን፡፡ በልዩ ልዩ አስተሳሰባችን የፈጠረን እርሱ በቃሉ ውስጥ ለእያንዳንዱ ሰው አንድ ነገር ሰጥቷል፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች በተማሪዎቹ በሕይወት ላይ ተግባራዊ እንደሆኑ ስትመለከቱ፣ እንደ አማካሪ እንዲመለከቱት አስተምሯቸው…፡፡ CGAmh 489.3
መጽሐፍ ቅዱስ ተሟጥጦ መጥፋት የማይችል ሙላት፣ ጥንካሬ እና ጥልቅ ትርጉም አለው፡፡ ልጆች እና ወጣቶች በሀሳብም ሆነ በአመለካከት እሴቱን እንዲፈልጉ አበረታቷቸው፡፡ 1029 CGAmh 490.1
እያንዳንዱ ለራሱ ማጥናት አለበት— እናቶች እና አባቶች ስለ ልጆቻቸው ከባድ ኃላፊነት አለባቸው። እነዚያ ቅዱሳን መጽሐፍትን የሚያምኑ እና የሚያጠኑ ወላጆች የእግዚአብሔርን ትእዛዛት መታዘዝ እንዳለባቸው፣ ከቅዱስ ሕጉ ጋር ተቃራኒ በሆነ መንገድ መሄድ እንደሌለባቸው ይገነዘባሉ። ማንም፣ አገልጋይም እንኳ የእግዚአብሔርን ቃል ችላ እንዲሉ እንዲመሯቸው የሚፈቅዱ ሁሉ የአካሄዳቸውን ውጤት በፍርድ ወቅት ያገኛሉ፡፡ ወላጆች ስለ ራሳቸው ነፍስና ስለ ልጆቻቸው ነፍስ በፍጥረት እና በመቤዠት የእርሱ በሆኑት በእግዚአብሄር ላይ መተማመን አለባቸው እንጂ በአገልጋዩ ላይ እምነታቸውን መጣል የለባቸውም፡፡ ወላጆች ሊድኑ ወይም ሊጠፉ የሚችሉ ነፍሳትን ስለያዙ ቅዱሳን ጽሑፎችን ለራሳቸው መመርመር አለባቸው፡፡ ለመዳን በአገልጋይ ላይ ጥገኛ መሆን የለባቸውም፡፡ እውነትን ለራሳቸው ማጥናት አለባቸው፡፡ 1030 CGAmh 490.2
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለልጆች አስደሳች እንዲሆን ያድርጉ— ወጣቶች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ይወዱ ዘንድ ይማሩ። ከሌላው ሁሉ በላይ የምንፈልገውን እውቀት በመያዙ በአስተሳሰባችን እና በባህሪያችን የመጀመሪያውን ቦታ ከመጽሐፍት ሁሉ በላይ ለሆነ መጽሐፍ እንስጥ፡፡ 1031 CGAmh 490.3
ይህንን ስራ ለመስራት ወላጆች ራሳቸው ከእግዚአብሔር ቃል ጋር መተዋወቅ አለባቸው...፡፡ እንዲሁም ከንቱ ቃላትን እና ተራ ተረታ ተረትን ለልጆቻቸው ከመንገር ይልቅ በመጽሐፍ ቅዱስ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ከእነርሱ ጋር ይነጋገራሉ፡፡ መጽሐፉ ለምሁራን ብቻ አልተዘጋጀም፡፡ እርሱ የተራውን ህዝብ ግንዛቤ ተደራሽ ለማድረግ በግልጽ፣ በቀላል ዘይቤ የተፃፈ ነው፤ እና ተገቢ በሆኑ ማብራሪያዎች፣ የእርሱ አብዛኛው ክፍል በጣም ትናንሽ ለሆኑ ልጆች በእጅጉ አስደሳች እና ትርፍ የሚሰጥ ሊሆን ይችላል። 1032 CGAmh 490.4
መጽሐፍ ቅዱስ ለልጆቹ አሰልቺ መጽሐፍ ይሆናል ብላችሁ አታስቡ፡፡ በጥበባዊ አስተማሪ ስር ቃሉ የበለጠ ተፈላጊ ይሆናል። የሕይወት እንጀራ ይሆንላቸዋል፤ በጭራሽም አያረጅም፡፡ ሕፃናትን እና ወጣቶችን የሚስብ እና የሚማርክ ውበት በውስጡ አለ፡፡ እርሱ ብርሃኗን እና ሙቀቷን እንደምትሰጥ ነገር ግን እንደማትዝል በምድር ላይ እንደምትፈነጥቅ ጸሐይ ነው፡፡ ልጆችና ወጣቶች ሁሉም ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ እና አስተምህሮ ትምህርቶች፣ ሌሎች መጽሐፍት ከዚህ በታች እንደሆኑ መማር ይችላሉ፡፡ እዚህ የምህረት እና የፍቅር ምንጭ ያገኛሉ፡፡1033 CGAmh 491.1
ወላጆች ሆይ፣ ለልጆቻችሁ የምትሰጡት መመሪያ ቀላል ይሁን፣ እንዲሁ በግልጽ መረዳታቸውንም እርግጠኞች ሁኑ፡፡ ለልጅነት አዕምሮአቸው የምታቀርቧቸው ትምህርቶችን መረዳት እንዳያቅታቸው እጅግ ቀላል ሊሆን ይገባል፡፡ ከእግዚአብሔር ቃል በተወሰዱ ቀላል ትምህርቶች እና ከራሳቸው ተሞክሮዎች ህይወታቸውን ከከፍተኛው ደረጃ ጋር እንዴት መስማማት እንደሚችሉ ልታስተምሯቸው ትችላላችሁ፡፡ በልጅነት እና በወጣትነት ጊዜያቸው እንኳን አሳቢነት እና ጥሩ ሕይወት ያለው የበለፀገ መከር የሚያስገኝ ቀናተኛ ኑሮ መኖርን መማር ይችላሉ፡፡ 1034 CGAmh 491.2
ንጹህ አስተሳሰብን ማበርከት፤ የተሻሉ ዘዴዎችን ተጠቀሙ— የሰማይ አባታችን ቃሉን ሲሰጥ ልጆችን ችላ አላለም ነበር፡፡ ሰዎች በጻፏቸው ጽሁፎች ሁሉ ውስጥ፣ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች የትናንሽ ልጆችን ፍላጎት ለማንቃት እና ልብን የሚነካ ነገር የት ይገኛል? CGAmh 491.3
በእነዚህ ቀላል ታሪኮች ውስጥ የእግዚአብሔር ሕግ ታላላቅ መርሆዎች ሊገለጹ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ለልጁ ግንዛቤ ተስማሚ በሆኑ ሥዕላዊ መግለጫዎች ወላጆች እና አስተማሪዎች ጌታ ትእዛዛቱን በተመለከተ “ለልጆችህም አስተምረው፣ በቤትህም ስትቀመጥ፣ በመንገድም ስትሄድ፣ ስትተኛም፣ ስትነሳም ተጫወተው፡፡” (ዘዳግም 6፡7) የሰጠውን ትእዛዝ ለመፈፀም ገና በጊዜ መጀመር አለባቸው፡፡ CGAmh 491.4
ትምህርት አሰጣጥ ላይ ምሳሌን፣ የጥቁር ሰሌዳዎችን፣ ካርታዎችን እና ስዕሎችን መጠቀሙ እነዚህን ትምህርቶች ለማስረዳት እና በማህደረ ትውስታ ላይ ለመቅረጽ እገዛ ይሆናል፡፡ ወላጆች እና አስተማሪዎች ያለማቋረጥ የተሻሻሉ ዘዴዎችን መፈለግ አለባቸው፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ንጹህ አስተሳሰባችንን፣ ምርጥ ዘዴዎቻችንን እና እጅግ ልባዊ ጥረታችንን ማግኘት አለበት፡፡ 1035 CGAmh 492.1
መጽሐፍ ቅዱስን እንደ መመሪያ ውሰዱት— ልጆቻችሁን በጌታ እንክብካቤ እና ተግሳጽ ማሳደግ ከፈለጋችሁ መጽሐፍ ቅዱስን መመሪያችሁ ማድረግ አለባችሁ። የክርስቶስ ሕይወት እና ባሕርይው እነርሱ መኮረጅ እንዳለባቸው ሞዴል በፊታቸው ይቅረብ፡፡ ከተሳሳቱ ጌታ ስለ እነዚያ ተመሳሳይ ኃጢአቶች የተናገረውን አንብቡላቸው፡፡ በዚህ ሥራ ውስጥ የማያቋርጥ ተግባር እና ትጋት ያስፈልጋል፡፡ ወላጆች አንድ የታገሱት የተሳሳተ፣ በአስተማሪዎች ያልታረመ ባህሪይ፣ መላውን ባህሪይ እንዲዛባ እና ሚዛናዊነት የጎደለው ሊያደርግ ይችላል፡፡ ልጆች አዲስ ልብ እንዲኖራቸው አስተምሯቸው፤ አዲስ ምርጫ መፈጠር አለበት፣ አዲስ ተነሳሽነት መነቃቃት አለበት፡፡ እነርሱ ከክርስቶስ እርዳታ ሊያገኙ ይገባል፤ በቃሉ ውስጥ ከተገለጸው የእግዚአብሔር ባሕርይ ጋር መተዋወቅ አለባቸው፡፡ 1036 CGAmh 492.2