የልጅ አመራር

75/85

ክፍል 17—መንፈሳዊ ኃይሎችን መቀስቀስ

ምዕራፍ 73—የዘላለማዊ ዓለማዎች ኃላፊነት

የእኛ ዘመን ለልጆች እጅግ አደገኛ ጊዜ ነው— የምንኖረው ልጆች ያልታደሉበት ዘመን ውስጥ ነው። የሆነ ከባድ ሁኔታ ወደ ጥፋት እየመራ ነው፣ እናም ይህንን ሁኔታ ለመቋቋም እና በእርሱ ላለመሸነፍ ከልጅነት ያላቀ ልምድ እና ብርታት ያስፈልጋል፡፡ ወጣቶች በአጠቃላይ የሰይጣን ምርኮኞች የሆኑ ይመስላሉ፣ እርሱ እና መላእክቱም እርግጠኛ ወደ ሆነ ጥፋት እየመሯቸው ነው፡፡ ሰይጣን እና ሠራዊቱ የእግዚአብሔርን መንግስት እየተዋጉ ናቸው፣ እንዲሁም ልባቸውን ለእርሱ የማስገዛት እና መስፈርቶቹን ለመታዘዝ ምኞት ያላቸው ሁሉ ተስፋ እንዲቆጥርጡ እና ጦርነቱን እንዲተው ሰይጣን እነርሱን በፈተናዎቹ ለማደናገር እና ለማሸነፍ ይጥራል። 938 CGAmh 448.1

እኛ ዛሬ ከሚያስፈልገን በላይ ከእግዚአብሔር ጋር የጠበቀ ግንኙነት አልነበረንም፡፡ የአምላክ ሕዝቦችን ከሚያስቸግሩ አደጋዎች መካከል ታላቁ ከዓለማዊ መሠረታዊ መርኾዎች እና ባሕል ጋር መመሳሰል አልነበረም፡፡ በተለይም ወጣቶች የማያቋርጥ አደጋ ላይ ናቸው፡፡ አባቶችና እናቶች የሰይጣን ሽንገላዎች ላይ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው። እርሱ የልጆቻቸውን ጥፋት እውን ለማድረግ ሲሻ፣ ወላጆች ምንም ዓይነት ልዩ አደጋ እንደሌለ ራሳቸውን እንዳይደልሉ፡፡ የልጆቻቸው የከበሩ ዘላለማዊ ዓለማዎች ቸል እያሉ ለዚህ ዓለም ጉዳዮች እንዳያስቡ፣ እንዳይጨነቁም። 939 CGAmh 448.2

በጥቅሉ ወላጆች ግድየለሾች ናቸው— ወላጆች በመንፈሳዊ ህይወታቸው ሲቀዘቅዙ እና በኃይማኖት የደከሙ እና ለእግዚአብሔር ያልተሰጡ ከመሆናቸው የተነሳ ልጆቻቸው የጌታን መንገድ እንዲጠብቁ በትዕግሥትና በጥንቃቄ የማሠልጠን ከፍተኛ ኃላፊነታቸውን አለመገንዘባቸው የሚያሳዝን ነገር ነው፡፡ 940 CGAmh 448.3

በጥቅሉ ወላጆች ልጆቻቸው ህይወት ነባራዊ እውነታዎች ውስጥ በትክክለኛው እና ስህተት መካከል እንዲወስኑ ሲፈለግባቸው እና ጠንካራ ፈተናዎች ሲገጥሟቸው፣ ለወደፊቱ ለሚጠብቋቸው ችግሮች ብቁ እንዳይሆኑ የተቻላቸውን ሁሉ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ ከዚያም ጠንካራ መሆን በነበረባቸው ቦታ ደካማ ሆነው ይገኛሉ፡፡ በመርህ እና በኃላፊነት ረገድ ይዋዥቃሉ፣ ሰብአዊ ሰውም ከደካማነታቸው የተነሳ ይሰቃያል፡፡ 941 CGAmh 449.1

በጣም አስፈላጊው ሥራ ችላ ተብሏል— በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ ክፋት እጅግ የበዛበት ዋነኛው ምክንያት ወላጆች አእምሯቸው በሌሎች ነገሮች ተጠምደው በጣም አስፈላጊ የሆነውን ሥራ— ማለትም ልጆቻቸውን በትእግስት እና ርህራሄ የጌታን መንገድ የማስተማርን ሥራ ችላ ማለታቸው ነው፡፡ 942 CGAmh 449.2

እናቶች የብዙ ነገሮችን እውቀት ሊያገኙ ይችላሉ፣ ነገር ግን እንደ ግል አዳኛቸው ስለ ክርስቶስ እውቀት ከሌላቸው አስፈላጊውን እውቀት ሊያገኙ አይችሉም። ክርስቶስ ቤት ውስጥ ካለ፣ እናቶች እርሱን አማካሪያቸው ካደረጉ፣ ልጆቻቸውን ገና ከልጅነታቸው ጀምሮ ስለ እውነተኛ የሃይማኖት መርሆዎች ያስተምራሉ፡፡6 CGAmh 449.3

ሰይጣን እንዲቆጣጠር ተፈቅዶለታል— ወንዶች እና ሴቶች እግዚአብሔርን ስለማይታዘዙት፣ የራሳቸውን መንገድ ስለሚመርጡ እና የራሳቸውን የተሳሳተ አስተሳሰብ ስለሚከተሉ፣ ሰይጣን በቤተሰቦቻቸው ውስጥ የገሃነም ሰንደቅ ዓላማን እንዲያቆምና ኃይሉ በሕፃናት፣ በልጆች እና በወጣቶች ላይ እንዲንጸባረቅ ተፈቅዶለታል። የእርሱ ድምጽ እና ፈቃድ ባልተገራ ፈቃድ እና ፈሩን በለቀቀ የልጆች ባህሪዎች ይገለጻል፣ በእነርሱም አማካኝነት የቁጥጥር ኃይሉን ይዘረጋል፣ እቅዶቹንም ይፈጽማሉ፡፡ የእግዚአብሔርን አክብሮት በሚያስወግዱ እና ሳይጣን የሚያቀርባቸው ሐሳቦችን መታዘዝን በሚያስከትሉ ፈር የለቀቁ ስሜቶች መንጸባረቅ እግዚአብሔር ይዋረዳል፡፡ በዚህ መንገድ ሰይጣን እንዲቆጣጠር በመፍቀድ ወላጆች የሚፈጽሙት ኃጢአት መረዳት ከሚቻለው በላይ ነው፡፡ 943 CGAmh 449.4

ብዙ ወላጆች በስልጠናቸው፣ መሻትን ባለመግዛት ሞኝነት እና በምርጫ እና በምግብ አምሮት ማሞላቀቅ ለልጆቻቸው ጠማማ ጎዳና እና ፀባይ ራሳቸውን ተጠያቂ ያደርጋሉ፡፡ ሰይጣን በዚያ ጸባይ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት እንዳይታዘዙ መላውን አካል ሊቆጣጠር ይችላል፡፡ ወላጆች ልክ እንደ አብርሃም ከኋላቸው እንዲከተሏቸው ቤተሰቦቻቸውን አያዙም፡፡ ውጤቱስ ምን ይሆን? ልጆች እና ወጣቶች በአመፅ ሰንደቅ ዓላማ ስር ቆመዋል፡፡ እነርሱ ታዛዦች ሳይሆኑ የራሳቸውን ፈቃድ ለመከተል የወሰኑ ናቸው፡፡ ለልጆች ብቸኛው ተስፋ እራሳቸውን እንዲክዱ እና አግባብነት የሌላቸውን ምኞቶቻቸውን እንዳያረኩ ማስተማር ነው፡፡ 944 CGAmh 450.1

ያለተገሩ ልጆች ፊት ከባድ ጦርነት ተጋርጦባቸዋል— ሳይገሩ በዚህ መንገድ ያደጉ ልጆች የክርስቶስ ተከታዮች እንደሆኑ በሚናገሩበት ጊዜ ሊማሩት የሚገባቸው ብዙ ነገሮች አሉ። መላው የኃይማኖታዊ ልምዳቸው በልጅነታቸው የአስተዳደግ ሁኔታ አደጋ ላይ ይወድቃል፡፡ ብዙውን ጊዜ ተመሳሳይ የራስ ፍላጎት ይታያል; ተመሳሳይ ራስን አለመካድ ይኖራል፣ በተግሳጽ ጊዜ ተመሳሳይ ትዕግስት ማጣት፣ ተመሳሳይ ራስን መውደድ እና የሌሎችን ምክር ለመፈለግ ፈቃደኛ አለመሆን፣ ወይም የሌላውን ፍርድ አለመቀበል፣ ተመሳሳይ ስንፍና፣ ሸክምን መሸሽ፣ ኃላፊነት አለመሸከም ይኖራል። ይህ ሁሉ የሚታየው ከቤተክርስቲያን ጋር በሚኖራቸው ግንኙነት ላይ ነው፡፡ እንደነዚህ ያሉት ማሸነፍ ይችላሉ፣ ነገር ግን ውጊያው ምን ያህል ከባድ ነው! ጦርነቱ ምንኛ ከባድ ነው! ለእነርሱ የክርስቲያናዊ ባህሪይ ከፍታ ላይ ለመድረስ ጥልቅ ሥልጠና ውስጥ ማለፍ ምንኛ ከባድ ነው! ሆኖም በመጨረሻ ካሸነፉ፣ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ከመልበሱ በፊት፣ በወጣትነታቸው ከተገቢ ስልጠና እጦት እና በልጅነታቸው ራሳቸውን ማስገዛትን ካለመማራቸው የተነሳ፣ ወደ ዘላለማዊ ጥፋት አዘቅት ምን ያህል ቀርበው እንደነበረ፣ እንዲያዩ ይፈቀድላቸዋል።945 CGAmh 450.2

ብልሹ ተጽዕኖዎችን እንዲቋቋሙ መሽጓቸው— ወላጆች ሆይ፣ ያለምንም የእነርሱ ድምጽ ልጆቻችሁን ወደ ዓለም የማምጣት ሀላፊነት ወስዳችኋል፣ በመሆኑም ለልጆቻችሁ ህይወት እና ነፍሶች ሀላፊነት አለባችሁ፡፡ የሚስቧቸው እና የሚያታልሏቸው የዓለም መስህቦች አሉ፡፡ ከብልሹ ተጽዕኖዎች እነርሱን ለመመሸግ ማስተማር ትችላላችሁ፡፡ የሕይወትን ሀላፊነቶች እንዲሸከሙ እና ለእግዚአብሔር፣ ለእውነት፣ እና ለኃላፊነት ያለባቸውን ግዴታዎች እንዲገነዘቡ እና ተግባሮቻቸውም በዘላለማዊ ህይወታቸው ላይ ሊኖረው የሚችለውን ተጽዕኖ እንዲገነዘቡ ልታሰለጥኗቸው ትችላላችሁ። 946 CGAmh 451.1

የዘመናችን ወጣቶች የሰይጣንን ዘዴዎች አያውቁም። በመሆኑም ወላጆች የመጀመሪያውን የጠላት አመጣጥ ለመግታት በጽናት እና በትጋት በመስራት በእነዚህ አደገኛ ጊዜያት ንቁ መሆን አለባቸው፡፡ በቤት ውስጥ በሚቀመጡበት ጊዜ፣ ወይም በመንገድ ላይ ሲጓዙ፣ ሲነሱ ወይም ሲተኙ ልጆቻቸውን ማስተማር አለባቸው፡፡ 11 CGAmh 451.2

ልጆች በፅድቅ መንገዶች እንዲመሩ፣ ዘወትር ነቅቶ መጠበቅ አስፈላጊ ነው። ሰይጣን ሥራውን የሚጀምረው ገና ከልጅነታቸው ጀምሮ ሲሆን እግዚአብሔር ለከለከለውም ነገር ምኞት እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡ የልጆች ደህንነት በአብዛኛው የተመሰረተው በወላጆቻቸው ንቁነት፣ ትጋት እና ጥንቃቄ ላይ ነው፡፡ 947 CGAmh 451.3

ልጆች ጌታን ሙሉ በሙሉ መታዘዝ እና መታመን ምን ማለት እንደሆነ እንዲገነዘቡ ወላጆች አስፈላጊ የሆነውን ሁሉ ዘወትር ከመስጠት የሚያግዳቸው ነገር እንዲኖር መፍቀድ የለባቸውም፡፡ 948 CGAmh 452.1

ወላጆች፣ ከሞት መሰል እንቅልፋቸው ይንቁ— ከወላጆቻቸው ግድየለሽነት የተነሳ ብዙ ልጆች ወላጆቻቸው ለነፍሳቸው ግድ እንደሌላቸው ሆኖ ይሰማቸዋል። ይህ መሆን የለበትም፣ ነገር ግን እነርሱን ወደ ክርስቶስ በመምራት ረገድ የወላጆችን ተጽዕኖ የሚቀንስ ምንም ነገር በእነርሱ እና በልጆቻቸው መካከል በማያስገባ መልኩ የቤት እና የንግድ ሥራዎቻቸውን መምራት አለባቸው፡፡ ልጆቻችሁ በልባቸው፣ በድርጊታቸው እና በንግግራቸው ንጹህ እንዲሆኑ የኢየሱስን ፍቅር ትምህርት ማስተማር አለባችሁ…፡፡ CGAmh 452.2

ወላጆች ከመለኮታዊ ወኪሎች ጋር አብረው ቢሰሩ ኖሮ ጌታ በልጆች ልብ ላይ ይሠራ ነበር፣ ሆኖም ግን እርሱ እንደ ሥራ ድርሻችሁ የተሰጣችሁን እርሱ አይሰራላችሁም። ወላጆች፣ ሞት ከሚመስል እንቅልፋችሁ መንቃት አለባችሁ። 949 CGAmh 452.3

ታላቁ ተስፋችን የቤት ውስጥ ኃይማኖት ነው— ወላጆች አንቀላፍተዋል፡፡ ልጆቻቸው በዓይኖቻቸው ፊት ወደ ጥፋት እየተጓዙ ናቸው፣ ጌታም መልዕክተኛው የቤት ውስጥ ኃይማኖት አስፈላጊነትን በመመሪያ እና በምሳሌ በሕዝቡ ፊት እንዲያቀርብ ይፈልጋል፡፡ ይህንን ጉዳይ በጉባኤያችሁ ልብ ውስጥ እንዲሰርጽ አጥብቃችሁ አሳስቧቸው፡፡ ለረጅም ጊዜ ችላ የተባሉ እነዚህን የከበሩ ግዴታዎች በሕሊናቸው ውስጥ እንዲሰርጽ አድርጉ፡፡ ይህ የፈሪሳዊነትን መንፈስ እና እውነትን መቃወምን ሌላ ማንኛውም ነገር ከሚችለው በላይ ይሰብራል፡፡ የቤት ውስጥ ኃይማኖት ታላቁ ተስፋችን እና መላው ቤተሰብን ወደ እግዚአብሔር እውነት ለመለወጥ መጪውን ጊዜ ብሩህ የሚያደርግ ነው፡፡15 CGAmh 452.4

የሰይጣን ኃይል ሊሰበር ይችላል— ወላጆች ከሚገምቱት በላይ በጣም ከባድ የሆነ ኃላፊነት አላቸው። ልጆች ኃጢአትን ወርሰዋል፡፡ ኃጢአት ከእግዚአብሔር ለይቷቸዋል፡፡ የሱስ ሕይወቱን የሰጠው ከእግዚአብሔር ጋር የሚያቆራኛቸውን የተሰበረውን አጣምሬ ለማገናኘት ነው፡፡ ከመጀመሪያው አዳም ጋር በተያያዘ፣ ሰዎች ከእርሱ ከጥፋተኝነት እና ከሞት ፍርድ በስተቀር ምንም አልተቀበሉም፡፡ ነገር ግን ክርስቶስ በሰው ልጆች ሁሉ ፋንታ ፈተናን ሁሉ በመቋቋም ጣልቃ ገብቶ አዳም በወደቀበት ውስጥ አለፈ...፡፡ የክርስቶስ ፍጹም ምሳሌ እና የእግዚአብሔር ጸጋ ወንዶችና ሴቶች ልጆችን የእግዚአብሔር ወንዶች እና ሴቶች ልጆች እንዲሆኑ እንዲያሰለጥናቸው አስችሎታል፡፡ የሰይጣን ኃይል የሚሰበረው ሥርዓት በሥርዓት፣ ትዕዛዝ በትዕዛዝ ልብ እና ፈቃድን እንዴት ለክርስቶስ እንደሚሰጥ እነርሱን በማስተማር ነው፡፡ 950 CGAmh 453.1

አባቶች እና እናቶች ሆይ፣ በእምነት ሙሉ በሙሉ እርግጠኛነት ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁን ተማጸኗቸው፡፡ አንዳችም ትዕግሥት የሌለው ቃል ከከንፈሮቻችሁ አይስሙ፡፡ አስፈላጊ ከሆነ፣ ሁሉም ይቅርታን እና የኃጢያት ስርየት እንዲቀበሉ፣ ልጁን ከጠፋው ዓለም ያልነፈገውን ጌታን የከንቱነትን መንገድ እንዲከተሉ እና እርሱን እንዲያሳዝኑ በመፍቀዳችሁ ስለ ልጆቻችሁ ልባዊ ንስሃ አድርጉ…፡፡ CGAmh 453.2

ልጆቻቸው እስኪጎዱ ድረስ በተለያዩ መንገዶች አግባብነት የሌላቸውን የልጆቻችሁን ምኞቶች የምታረኩ አባቶች እና እናቶች፣ እግዚአብሔር ዘመኑን እንድትዋጁ ይፈልጋል። ዛሬ ጊዜ እየለ ማስጠንቀቂያውን ተቀበሉ፡፡951 CGAmh 453.3

ወላጆች የተከበረ የሚስዮናዊነት መስክ አላቸው— የልጆቻችሁን ባህሪይ በመለኮታዊ ቅርጽ መሠረት መቅረጽን የዕድሜ ልክ ሥራ አድርጉ። የየዋህነት እና የረጋ መንፈስ ጌጥ የሆነውን ውስጣዊ ውበት ካላቸው፣ የእግዚአብሔርን ቃል ትምህርቶች እንዲወዱ እና በዓለም ዘንድ ተቀባይነት ከማግኘት ይልቅ በየሱስ ዘንድ ቅቡልነት ማግኘትን እንዲፈልጉ በትጋት ስላሠለጠናችኋቸው ነው። 952 CGAmh 453.4

የእግዚአብሔር ሠራተኞች እንደመሆናችን የእኛ ሥራ በአቅራቢያችን መጀመር አለበት፡፡ በእኛ ቤት መጀመር አለበት፡፡ ከዚህ የበለጠ ጠቃሚ የሚስዮናዊነት መስክ የለም፡፡ 953 CGAmh 454.1

የህይወትን ቃል በቤተሰቦቻችን ፊት ማቅረብ እንድንችል እና በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ቤት እንዲኖራቸው ዘንድ እንዲሹ ለመምራት፣ በቤታችን ውስጥ የሚስዮናዊነት የጋለ ስሜት ያስፈልገናል። 954 CGAmh 454.2

ልጆችን ማስተዳደር እና ማስተማር ማንኛውም ወንድ ወይም ሴት ሊያከናውን የሚችለው የከበረ የሚስዮናዊነት ሥራ ነው። 955 CGAmh 454.3

ወላጆች ህያው ሸክላን እንደሚቀርጹ ኪነ-ጥበበኞች— ኪነ-ጥበበኞች በውስጡ ያለውን ፍጹም የሆነውን ምስል የሥዕል ሸራው ላይ ለማሳረፍ ምን ያህል በትጋት እና በትዕግስት ይሰራል! የቅርፃ ቅርጽ ሠራተኛ እየተከተለ ያለውን ቅጂ ድንጋዩ ላይ ለመቅረጽ ምን ያህል በትጋት ይጠርባል፣ ይቆረቁርማል፡፡ እንዲሁ ወላጆች በክርስቶስ የሱስ ከተሰጣቸው አርአያነት አንጻር ልጆቻቸውን ለመቅረጽ፣ ለማለስለስ እና ለማንጻት መጣር አለባቸው፡፡ ትዕግስተኛ ኪነ-ጥበበኛ ሥራው የላቀ ውጤት እንዲኖረው እንደሚያጠና፣ እንደሚሠራ፣ እና ዕቅድ እንደሚነድፍ ሁሉ ወላጆችም እንዲሁ ልጆቻቸውን ፋይዳ ላለው ሕይወት ለማሠልጠን እና ለዘላለማዊ መንግስት እነርሱን ብቁ ለማድረግ በአግባቡ ጊዜ ሊወስድባቸው ይገባል፡፡ የኪነ-ጥበበኛው ሥራ ከወላጅ ጋር ሲወዳደር አነስተኛ እና አላስፈላጊ ነው፡፡ አንደኛው የውበት ቅርጾችን ከሚያወጣበት የሕይወት አልባ ቁሳቁሶች ላይ ይሰራል፣ ሌላኛው ደግሞ ህይወቱ ለመልካም ወይም ለክፋት፣ የሰው ልጆችን ለመባረክ ወይም ለመርገም፣ በጨለማ ወይም ለወደፊቱ ኃጢአት በሌለበት ዓለም ውስጥ ለዘላለም ከሚኖር ሰው ጋር ነው የሚሰራው፡፡ 956 CGAmh 454.4

ፍጽምናን ግባችሁ አድርጉ— ክርስቶስ በአንድ ወቅት ትንሽ ልጅ ነበር፡፡ ስለ እርሱ ስትሉ ልጆችን አክብሯቸው፡፡ እንደ የተቀደሰ ኃላፊነት ተመልከቷቸው፣ ንጹህ እና የከበረ ሕይወት እንዲኖሩ መማር አለባቸው እንጂ እንደ ብርቅዬ እና እንደ ጣኦት መታየት የለባቸውም፡፡ እነርሱ የእግዚአብሔር ንብረት ናቸው፡፡ እርሱ ይወዳቸዋል፣ ፍጹም ባህሪይ እንዲኖራቸውም ከእርሱ ጋር አብራችሁ እንድትሰሩ ጥሪ ያደርግላችኋል፡፡ ጌታ ከተቤዠው ቤተሰቡ ፍጽምና ይፈልጋል፡፡ ከእነርሱ ክርስቶስ በሰብአዊነቱ የገለጠውን ፍጽምና ይጠብቃል፡፡ አበቶች እና እናቶች በተለይም ከእግዚአብሔር ጋር መተባበር ይችሉ ዘንድ ልዩ የአሰለጣጠን ዘዴዎችን መረዳት አለባቸው፡፡23 CGAmh 455.1

የተለወጡ ወላጆች ይፈለጋሉ— ቀን እና ሌሊት የተለወጡ ወላጆች እጅግ እንደሚያስፈልጉን የማሰብ ሸክም ይሰማኝ ነበር፡፡ እነርሱ በቤተሰቦቻቸው ላይ የማዳን ተፅእኖ ቢያሳድሩ ኖሮ በእግዚአብሔር ፊት ልባቸውን ዝቅ ማድረግ የሚሹ እና ከሰማይ ጋር ወደ ትክክለኛ ግንኙነት የሚገቡ ስንት ሰዎች አሉ፡፡ ልጆቻቸውን የተቤዡት ለሚወርሱት ርስት የሚያሰለጥኑ ከሆነ የዘላለም ሕይወት ለመውረስ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ማወቅ አለባቸው። በየቀኑ የሰማይን ብርሀን ወደ ነፍሳቸው መቀበል አለባቸው፣ በየቀኑ የመንፈስ ቅዱስን አሻራ በልባቸው እና በአዕምሮአቸው መቀበል አለባቸው፡፡ በየቀኑ የእውነትን ቃል መቀበል እና ህይወታቸውን እንዲቆጣጠር መፍቀድ አለባቸው። 957 CGAmh 455.2

ትልልቅ ኃላፊነቶች በወላጆች ላይ ያርፋሉ፣ በመሆኑም እግዚአብሔር እነርሱን የሾመበትን ተልእኮ ለመወጣት ልባዊ ጥረት ማድረግ አለባቸው፡፡ የሰብአዊ ሰው ኃይላትን ሁሉ ልጆቻቸውን ለእግዚአብሔር ወደ በማሠልጠ ሥራ የማዞር አስፈላጊነትን ሲመለከቱ፣ አሁን የሚታየው ብዙ ከንቱነት እና አላስፈላጊ ማስመሰል ይወገዳል። ጌታን በደስታ ለመገናኘት የሚያስችላቸውን ማንኛውንም መስዋእትነት ወይም ታላቅ ስራ ከቁጥር ውስጥ አያስገቡም። ይህ እንደ እግዚአብሔር ተከታዮች ችላ ሊሉት የማይችሉ የአገልግሎታቸው እጅግ ውድ ክፍል ነው። 958 CGAmh 455.3

ዘወትር ወደ የሱስ ተመልከቱ — ወላጆች ሆይ፣… ትንሹ መንጋችሁን ለማዳን መላውን መንፈሳዊ ብርታታችሁን እና ጡንቻችሁን ተጠቀሙ። የገሃነም ኃይሎች እርሱን ለማጥፋት አንድ ይሆናሉ፣ ሆኖም ግን እግዚአብሔር ሰንደቅ ዓለማውን ጠላት ላይ ያነሳል፡፡ እስከ አሁን ከምታደርጉት በላቀ ሁኔታ ብዙ ጸልዩ። በፍቅር፣ በርኅራሄ፣ ልጆቻችሁ እንደ ሰማያዊ አባታቸው ወደ እግዚአብሔር እንዲመጡ አስተምሯቸው፡፡ ምሳሌ በመሆን ራስን መግዛትን እና አጋዥነትን አስተምሯቸው። ክርስቶስ ራሱን ለማስደሰት አለመኖሩን ንገሯቸው ፡፡ CGAmh 456.1

በመንገዳችሁ ላይ በማብራት ላይ የሚገኙትን መለኮታዊ የብርሃን ጨረሮችን ሰብስቡ፡፡ ክርስቶስ በብርሃን እንደ ሆነ በብርሃን ተመላለሱ፡፡ ልጆቻችሁ እግዚአብሔርን እንዲያገለግሉ የመርዳት ስራ ስትጀምሩ፣ በጣም የሚያበሳጩ ፈተናዎች ይመጣሉ፤ ሆኖም ግን እጃችሁን አትስጡ፤ ከየሱስ ጋር ተጣበቁ። እርሱም “ጉልበቴን ይያዝ፣ ከእኔ ሰላም ያድርግ፤ ከእኔ ጋር ሰላም ያድርግ፡፡” ኢሳ 27፡5 ይላል፡፡ ችግሮች ይነሳሉ፤ መሰናክሎች ይገጥሟችኋል፤ ሆኖም ግን ዘወትር የሱስን ተመልከቱ፡፡ ድንገተኛ ሁኔታ ሲከሰት፣ ጌታ ሆይ፣ አሁን ምን ማድረግ አለብን ብላችሁ ጠይቁት? መበሳጨትን ወይም መናደድን አሻፈኝ ካላችሁ ጌታ መንገዱን ያሳችኋል፡፡ ሰላም እና ፍቅር ቤት ውስጥ እንዲነግስ በሚያደርግ መልኩ ክርስቶስ መሰል የንግግር መክሊትን እንድትጠቀሙ እርሱ ይረዳችኋል፡፡ ወጥ የሆነ የድርጊት አካሄድ በመከተል፣ ለልጆቻችሁ የጸጋ አገልጋዮች በመሆን የቤት ውስጥ ወንጌላዊ መሆን ትችላላችሁ። 959 CGAmh 456.2

ይህ ሥራ ወሮታ ይከፍላል— ልጆችን በእግዚአብሔር መንገድ ለማሳደግ አንድ ነገር ያስከፍላል፡፡ የእናትን እንባ እና የአባትን ጸሎቶች ያስከፍላል፡፡ እዚህ ጥቂት እዚያ ጥቂት፣ የማይታክት ጥረት፣ ትዕግስት የተሞላበት መመሪያ ይጠይቃል። ሆኖም ግን ይህ ሥራ ወሮታ ይከፍላል፡፡ ወላጆች በዚህ መንገድ በልጆቻቸው ዙሪያ ዓለማችንን ከሚያጥለቀቀው ክፋት ሊጠብቋቸው የሚችሉ ግድቦችን መገንባት ይችላሉ፡፡27 CGAmh 457.1