የልጅ አመራር

73/85

ምዕራፍ 71—የወላጅ ንቃት እና ዕርዳታ

ወላጆች ልጆችን ከጨቅላነታቸው ጀምረው ራስን መግዛትን ያስተምሯቸው— ልጆቻችንን ከልጅነታቸው ጀምሮ ራስን መግዛትን ማስተማር እና ፈቃዳቸውን ለእኛ የማስገዛት ትምህርት ማስተማር ምን ያህል አስፈላጊ ነው! ክፉ ውጤቱን ሁሉ ሳያውቁ የተሳሳቱ ልምዶችን በመማር ያልታደሉ ቢሆኑ፣ እንደነዚህ ያሉ ልማዶች አካልን የሚጎዱ እና አዕምሮ ላይ ተጽዕኖ የሚያደርጉ መሆናቸውን ወደ ሕሊናቸው በማምጣት እና በማሳመን ሊሻሻሉ ይችላሉ፡፡ የተቀሰቀሱ ፍርሃቶቻቸውን ለማረጋጋት እና ወደዚህ አስጸያፊ ልማዶች የሚመሯቸው ብልሹ ሰዎች ምንም ያህል ማሳመኛዎችን ቢጠቀሙ፣ አስመሳይነታቸው ምንም ያህል ቢሆን እነርሱ ጠላቶቻቸው እና የሰይጣን ወኪሎች ናቸው፡፡ 911 CGAmh 435.1

በንጽህና ያዟቸው— አእምሯቸውን አጎልብቱ— እናቶች የልጆቻቸውን ልምዶች በተመለከተ አላዋቂዎች ሆነው እንዲቆዩ መፍቀድ ወንጀል ነው። ንጹሃን ከሆኑ እንደዚያው ያዟቸው፡፡ የልጅነት አዕምሮአቸውን አጎልብቱ እና ይህን የጤና-እና ነፍስ-አጥፊ ብልግናን እንዲጸየፉ አዘጋጇቸው። 912 CGAmh 435.2

ሰይጣን የልጆችን አእምሮ እየተቆጣጠረ ነው፣ በመሆኑም እነርሱን ለማዳን በጽናትና በታማኝነት መስራት አለብን። በጣም ትናንሽ ልጆች ይህንን ብልግና ይለማመዳሉ፣ እናም እያንዳንዱ የተከበረ የአካል እና የአዕምሮ ክፍል እስኪዋረድ ድረስ በእነርሱ ላይ የሚያድግ እና ከዕድሜያቸው ጋር እየበረታ የሚሄድ ይሆናል፡፡ ይህ ተግባር በጤንነታቸው ላይ የሚያስከትለውን ውጤት በተመለከተ በጥንቃቄ የተማሩ ቢሆን ኖሮ ብዙዎች ሊድኑ ይችሉ ነበር፡፡ በራሳቸው ላይ ብዙ ሥቃይ እያመጡ እንደሆነ አያውቁም ነበር…፡፡ CGAmh 435.3

እናቶች፣ ልጆቻችሁ ወራዳ ልምዶችን እንዳይማሩ መከልከል ከልክ ያለፈ ጠንቃቃ አያስብላችሁም፡፡ ክፋት ከተለመደ በኋላ ከማስወገድ ይልቅ መማሩ ይቀላል። 913 CGAmh 436.1

ቆራጥነት የተሞላበት ንቁ መሆን እና ጥብቅ ምርመራን ማድረግ— ልጆቻችሁ ይህንን ብልግና እየተለማመዱ ከሆነ እናንተን ለማታለል እንደ መጨረሻ አማራጭ ውሸተኞች የመሆን አደጋ ሊያጋጥማቸው ይችላል፡፡ ነገር ግን እናቶች፣ በቀላሉ ፀጥ ማለት እና ምርመራዎቻችሁን ማቆም የለባችሁም፡፡ ሙሉ በሙሉ እስክትረኩ ድረስ ጉዳዩን መተው የለባችሁም። ይህንን ጉዳይ እጅግ ወሳኝ የሚያደርገው የውዶቻችሁ ጤና እና ነፍሳት አደጋ ላይ መሆን ነው፡፡ ለማምለጥ እና ለመደበቅ የተደረጉ ሙከራዎች ቢኖሩም በትኩረት መከታተል እና የጠበቀ ምርመራ ማድረግ በአጠቃላይ የጉዳዩን ትክክለኛ ሁኔታ የሚያሳይ ይሆናል፡፡ ታዲያ እናት የነገሩን አዋራጅ አዝማሚያ በማሳየት ይህንን ርዕሰ ጉዳይ በእውነተኛ ገጽታው ለእነርሱ ማቅረብ አለባት፡፡ በዚህ ኃጢአት መርካት የራስን ክብር እና የባህሪይን ጨዋነት እንደሚያጠፋ፣ ጤና እና ግብረ ገብን እንደሚያበላሽ እነርሱን ለማሳመን ሞክሩ፡፡ በካይ እድፉ ነፍስ ለእግዚአብሔር ያለውን እውነተኛ ፍቅርና የቅድስና ውበቱን ይደመስሳል፡፡ እናት ይህ ልምምድ መቆሙን በቂ ማስረጃ እስክታገኝ ድረስ ይህንን ጉዳይ መከታተል ይኖርባታል፡፡ 914 CGAmh 436.2

ጅማሮ ላይ ችኮላ እና ነቀፋን አስወግዱ— ቀድሞውኑ የነበሩትን ክፋቶች እንዴት እናርማቸዋለን? ሥራውን እንዴት እንጀምራለን? ብለህ ልትጠይቅ ትችላለህ፡፡ ጥበብ ከሌለህ ወደ እግዚአብሔር ሂድ፤ እርሱ በልግስና ለመስጠት ቃል ገብቷል፡፡ መለኮታዊ እርዳታ ለማግኘት አዘውትረህ እና አጥብቀህ ጸልይ፡፡ በእያንዳንዱ ሁኔታ አንድ ደንብ መከተል አይቻልም፡፡ የተቀደሰ ፍርድን ተግባታዊ ማድረግ አሁን አስፈላጊ ነው፡፡ አትቸኩል፣ አትሸበር፣ ልጆችህንም አትንቀፍ፡፡ እንዲህ ዓይነቱ አካሄድ በእነርሱ ውስጥ ዓመፅን ብቻ የሚያነሳሳ ይሆናል፡፡ ልጆችህን ሰይጣን ወደ ፈተና እንዲያመራቸው በር ለከፈተላቸው በወሰድከው ማንኛውም የተሳሳተ አካሄድ በጥልቀት ሊሰማህ ይገባል፡፡ የጤና ህጎችን መጣስ በተመለከተ ካላስተማራችኋቸው ጥፋቱ በእናንተ ላይ ነው፡፡ አስፈላጊ ሀላፊነትን ችላ ብለሃል፣ ውጤቱም በልጆችህ የተሳሳቱ ተግባራት ይገለጣል፡፡ 915 CGAmh 436.3

ራስን በመቆጣጠር እና የሌላውን ስሜት በመጋራት ማስተማር— ልጆቻችሁን ራስን ስለ መግዛት ትምህርት በማስተማር ሥራ ላይ ከመሰማራታችሁ በፊት ራሳችሁ መማር አለባችሁ። በቀላሉ የምትበሳጩ እና ትዕግሥት የሌላችሁ ከሆነ ልጆቻችሁ ስሜቶቻቸውን እንዲቆጣጠሩ በምታስተምሩበት ጊዜ ለልጆቻችሁ እንዴት ሚዛናዊ መሆን ትችላላችሁ? ራስን በመቆጣጠር እና ጥልቅ የአዘኔታ እና ርህራሄ ስሜት በመያዝ ስህተት ውስጥ ያሉትን ልጆቻችሁ ጋር በመቅረብ እና የጀመሩትን አካሄድ የሚቀጥሉ ከሆነ አካላቸውን የማውደማቸው ተግባር— ማለትም አካል እና አእምሮንን በሚያዳክሙበት ጊዜ፣ እንዲሁም ግብረ ገብም እንዲሁ እንደሚጠፋ፣ ደግሞም በራሳቸው ብቻ ላይ ሳይሆን በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት እየሠሩ መሆናቸው እርግጥ እንደሆነ በታማኝነት አስረዷቸው፡፡ CGAmh 437.1

ከተቻለ፣ ኃጢአት እየፈፀሙበት ያሉት ንጹህ እና ቅዱስ አምላክ፣ እግዚአብሔር እንደሆነ፤ በአካሄዳቸው ታላቁ ልብ መርማሪ እንዳዘነባቸው፤ አንዳች ነገር ከእርሱ መሰወር እንደማይቻል እንዲሰማቸው አድርጉ፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድ ቅቡልነት የሚያገኘው ንስሃ፣ ወደ መዳን የሚያደርስ እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ የሆነ ሀዘንን እንዲተገብሩ ልጆቻችሁ ውስጥ ከቀረጻችሁ፣ ሥራው በጥንቃቄ የተሰራ፣ ተሃድሶውም እርግጥ ይሆናል፡፡ ኃጢአታቸው ስለ ታወቀባቸው ብቻ አያዝኑም፤ ዳሩ ግን የኃጢአተኛ ተግባራቸውን አደገኛ ባህሪይ በመመልከት ያላ መገደብ ለእግዚአብሔር እንዲናዘዙ በመመራት ይተውአቸዋል፡፡ እግዚአብሔርን ስላሳዘኑና በእርሱ ላይ ኃጢአትን ስለ ሠሩ በፈጠራቸው ፊት እና ለአዕምሮ የሚመች አገልግሎታቸው የሆነውን ሰውነታቸውን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት የሆነውን ሰውነታቸውን ስላዋረዱ ስለ ስህተት አካሄዳቸው የሐዘን ስሜት ይሰማቸዋል፡፡ 916 CGAmh 437.2

የልጆች ጓደኞችን መከታተል— የልጆቻችን አእምሮ በኃይማኖታዊ መርህ በጽናት ሚዛናዊ ካልሆነ በስተቀር፣ ሥነ-ምግባራቸው ከእነርሱ ጋር በሚገናኙ ልጆች ክፉ ምሳሌ ግብረ ገባቸው ብልሹ ይሆናል ይበላሻል፡፡ 917 CGAmh 438.1

ታማኝ የሆኑ እናቶች እንደሚያደርጉት ሁሉ ከእያንዳንዱ ልጆች ጋር ጓደኝነትን በመፍጠር እንዳይበከሉ ጠብቋቸው፡፡ እንደ ውድ ዕንቁዎች ከዚህ ዘመን ብልሹ ተጽዕኖዎች ጠብቋቸው። ከወጣት ባልደረባዎቻቸው ጋር የሚያደርጉት ግንኙነት ሁል ጊዜ እናንተ እንደምትፈልጉት የተሻለ ካልሆነ እናንተ በተገኛችሁበት ልጆቻችሁን ይጎብኙ፤ ደግሞም በምንም ሁኔታ እነዚህ ጓደኞች በአንድ አልጋ ወይም በአንድ ክፍል ውስጥ እንኳ እንዲያድሩ አትፍቀዱላቸው፡፡ ክፋት ከተከሰተ በኋላ ከማከም ይልቅ መከላከሉ በጣም ይቀላል…. CGAmh 438.2

[ወላጆች] ልጆቻቸው ራሳቸው የሚተዋወቋቸውን ሌሎች ወጣት ጓደኞቻቸውን እንዲጎበኙ፣ ያሻቸውን የሚያደርጉበት ከወላጆቻቸው ቁጥጥር ሥር ወጥተው፣ ከቤታቸው እንኳ ርቀው እንዲሄዱ ይፈቅዱላቸዋል፡፡ ሰይጣን እነዚህን ሁሉ እድሎች በማሻሻል እናቶች ባለማወቅ በእርሱ የጮሌነት ወጥመድ ሥር እንዲወድቁ ያደረጉትን ልጆች አዕምሮ እንደ ዕድል ይጠቀምባቸዋል፡፡ 918 CGAmh 438.3

አመጋገብ ወሳኝ ነው— ምግባቸውን በመምረጥ ረገድ ጠንቃቆች ሳትሆኑ የልጆቻችሁን ግብረ ገባዊ የስሜት ኃይሎችን ማነሳሳት አትችሉም፡፡ ወላጆች ብዙውን ጊዜ ለልጆቻቸው የሚያዘጋጃቸው ምግቦች ለእነርሱ ወጥመድ ናቸው፡፡919 CGAmh 438.4

የሚያሞላቅቁ ወላጆች ልጆቻቸውን ራስን ስለ መካድ አያስተምሩም። ከፊት ለፊታቸው የሚያቀርቡላቸው ምግቦች ጨጓራን የሚያስቆጡ አይነት ናቸው፡፡ በዚህ መንገድ የተፈጠረው ነውጥ ወደ አዕምሮ ይዛመት እና በዚህ ምክንያት ስሜቶች ይነሳሳሉ። ወደ ሆድ የሚወሰደው ማንኛውም ነገር በሰውነት ላይ ብቻ ሳይሆን በአዕምሮም ላይም ጭምር ተጽዕኖ እንደሚያሳርፍ ብዙ ጊዜ ሊደጋገም አይችልም፡፡ ከባድ እና አነቃቂ ምግብ ደምን ያተኩሳል፣ የነርቭ ሥርዓት እንዲሸበር ያደርጋል፣ በዚህም ሳቢያ ምክንያታዊነት እና ህሊና በፍትወታዊ ስሜቶች እንዲዋጥ ብዙውን ጊዜ የግብረ ገብን የመለየት አቅም ያደንዛል፡፡ በምግብ ራስን መግዛት የማይችል ሰው ትዕግስት እና ራስን መቆጣጠርን መተግበር ለእርሱ አስቸጋሪ ነው፣ ብዙውን ጊዜም የማይቻል ነው፡፡ ስለሆነም ባህሪያቸው ገና ያልተስተካከሉ ሕፃናት፣ ጤናማ እና የማያነቃቃ ምግብ መስጠት በተለየ ሁኔታ ወሳኝ ነው፡፡ ያልተገደበ የምግብ ፍላጎት እርካታ ከሚያስከትሏቸው ክፉ ውጤቶች እኛን ለመጠበቅ የሰማዩ አባታችን የጤና ተሃድሶ ብርሃንን በፍቅር ልኮልናል፡፡ 920 CGAmh 439.1

አመጋገብ በጣም ቀላል ያለ መሆን ያለበት ጊዜ ቢኖር አሁን ነው። ስጋ በልጆቻችን ፊት መቅረብ የለበትም። ተጽዕኖው ወራዳ ስሜቶችን የሚቀስቀስ እና የሚያጠንክር እንዲሁም የግብረ ገብ ኃይሎችን የመግደል ዝንባሌ ያለው ነው። 921 CGAmh 439.2

ንፅህና አስፈላጊ ነው— በተለይም ማታ ከመተኛት በፊት ወይም ጠዋት ከእንቅልፍ በሚነቁበት ጊዜ አዘውትሮ መታጠብ፣ ጠቃሚ ነው፡፡ የልጆችን ገላ ማጠብ እና አካሎቻቸው እስኪነጻ ድረስ ለማሸት ጥቂት ጊዜ ብቻ የሚወስድ ነው፡፡ ይህ ደም አዕምሮን ለቆ ወደ አካል የላይኛው ክፍል እንዲመጣ ያደርጋል፤ በመሆኑም እርኩስ የሆኑ ነገሮችን ለመተግበር ዝቅተኛ ዝንባሌ ይኖራቸዋል፡፡ ትናንሽ ልጆች በቆሸሸ እና ንጹህ ባልሆነ ሰውነት፣ በተቀደዱ ልብሶች ሲታዩ እግዚአብሔር የማይደሰት መሆኑን ለልጆች አስተምሯቸው፡፡ ከውጭም ሆነ ከውስጥ ንጹህ እንዲሆኑ እንደሚፈልግ ንገሯቸው፡፡ 922 CGAmh 439.3

ንፁህ፣ ላላ ያለ-ገጣሚ ልብስ— ልብስን ግሩም እና ንጹህ ማድረግ ሀሳቦችን ንፁህ እና አስደሳች የማድረጊያ አንዱ መንገድ ነው፡፡ እያንዳንዱን ልብስ ማጠብ እና መተኮስ አነስተኛ ሥራ እንዲሆን ልብስ አላስፈላጊ ማስዋቢያ የሌለው ጌጣጌጥ ያሌለው እና ቀላል ያለ መሆን አለበት፡፡ በተለይም ከቆዳ ጋር የሚነካካ ሊይዛቸው አይገባም፡፡ ለዚህ ርዕሰ ጉዳይ የበለጠ ትኩረት ተሰጥቶ ቢሆን ኖሮ ቆሻሻ በከፍተኛ መጠን ይቀንስ ነበር፡፡ 923 CGAmh 440.1

ከአካል ብቃት እንቅስቃሴ ነጻ አይሆኑ— [ወጣቶች] ከመጠን በላይ መሥራትን ከመፍራት የተነሳ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ከመስራት በጣም ገሸሽ ይላሉ። ወላጆች ልጆቻቸው ሊሸከሟቸው የሚገባቸውን ሸክሞች ይሸከማሉ። ከመጠን በላይ መሥራት መጥፎ ነው፣ ነገር ግን የስንፍና ውጤት ይበልጥ አስፈሪ ነው። መሞላቀቅ ብልሹ ልማዶችን ወደ መመኘት ይመራል። ታታሪነት ራስን በራስ የመጉዳት አስከፊ ልማድ ከሚያደርሰው አንድ-አምስተኛውን ያህል አንድን ሰው አያደክምም፣ አያዝልምም፡፡ ቀላል፣ በደንብ ቁጥጥር የተደረገበት ሥራ ልጆቻችሁን የሚያደክም ከሆነ፣ ወላጆች ሆይ፣ እርግጠኛ ሁኑ፣ ከስራ ውጭ፣ የአካላቸውን ስርዓቶችን የሚያዳክም እና የማያቋርጥ የድካም ስሜት የሚያመጣ ነገር አለ፡፡ ነርቮቻቸው እና ጡንቻዎቻቸሁ እንዲሰራ የሚያደርግ ሥራ ለልጆቻችሁ ስጡ፡፡ እንደዚህ ዓይነቱን ሥራ ተከትሎ የሚመጣ ድካም በክፉ ልምዶች የመርካት ዝንባሌያቸውን ይቀንሳል፡፡ 924 CGAmh 440.2

ስንፍና ለፈተና በር መክፈት ነው— እናቶች ሆይ፣ ልጆቻችሁ የሚሰሩትን በቂ ነገር ስጧቸው ...፡፡ ስንፍና ለአካላዊ፣ ለአእምሮ ወይም ለግብረ ገባዊ ጤንነት ተስማሚ አይሆንም፡፡ ይህም ሰይጣን ዕድሉን በማሻሻል ወጣቶችን ወደ ወጥመዱ የሚያስገባበትን በር በመክፈት እርሱን ይጋብዛል፡፡ በስንፍና የግብረ ገብ ጥንካሬ ብቻ የሚዳከም እና የስሜት ግፊት የሚጨምር ብቻ ሳይሆን የሰይጣን መላእክት የአዕምሮን አጠቃላይ ኃይል በመቆጣጠር ህሊና ለክፉ ፍላጎት እንዲገዛ የሚያስገድድ ነው። ልጆችን ትዕግስት የሚጠይቅ ልማዶችን ማስተማር አለብን፡፡ 925 CGAmh 440.3

እግዚአብሔር የሚጸጸት ሰው እንዲጠፋ አይተወውም— መሃሪ የሆነ አምላክ እውነተኛ የልብ ንስሓን እንደሚቀበል እና ከስጋ እና ከመንፈስ ርኩሰት ሁሉ ለማፅዳት የሚያደርጉትን ጥረታቸውን እንደሚባርክ ለልጆቻችሁ ማበረታቻ ማቅረብ አለባችሁ፡፡ ሰይጣን የልጆቻችሁን አእምሮ ቁጥጥር ማግኘቱን እንደሚያጣ ሲያይ በጥብቅ ይፈትናቸው እና ይህን አስጸያፊ ድርጊት በቀጣይነት እንዲተገብሩ ሊያስራቸው ይሻል፡፡ ነገር ግን በጽኑ ዓላማ እንስሳዊ ምኞቶችን የማርካት የሰይጣን ፈተናዎችን መቃወም አለባቸው፣ ምክንያቱም ይህ በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት መሥራት ነው። ሰይጣን በእርሱ ቁጥጥር ሥር ሊያደርጋቸው የይገባኛል ጥያቄ ሊያቀርብ የሚችልበት የተከለከለ ሥፍራ ላይ ለመቆም መድፈር የለባቸውም፡፡ ራስን በማዋረድ እግዚአብሔርን ስለ ሀሳባዊ ንፅህና እና ለተሻለ እና ለተቀደሰ ሕሊና እግዚአብሔርን የሚለምኑ ከሆነ እርሱ ይሰማቸዋል፣ የለመኑትንም ይሰጣቸዋል፡፡ እግዚአብሔር በኃጢአታቸው እንዲጠፉ አልተዋቸውም፣ ዳሩ ግን እራሳቸውን በእምነት በእርሱ ላይ ቢጥሉ እርሱ ደካማ እና ምስኪኖችን ይረዳል፡፡ 926 CGAmh 441.1