የልጅ አመራር
ምዕራፍ 55—ሥነ-ሥርዓት በማስተማር ረገድ አንድነት መፍጠር
መምህሩ በአመራር ላይ ብልሃት ያስፈልገዋል— በወጣቱ መካከል ትልቅ የባህሪይ እና የትምህርት ልዩነቶች አሉ፡፡ አንዳንዶች በውስጣቸው የግትርነት እና የእምቢተኝነት መንፈስ ያሳደገውን አምባገነናዊ ክልከላ እና ጭካኔ ውስጥ ይኖራሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ የራሳቸውን ዝንባሌ እንዲከተሉ ከልክ በላይ አፍቃሪ በሆኑ በወለጆቻቸው የተፈቀደላቸው የቤተሰቡ ብርቅዬ ናቸው፡፡ ባህሪያቸው እስኪበላሽ ድረስ እያንዳንዱ ጉድለት በይቅርታ ይሸፋፈናሉ። እነዚህን የተለያዩ አዕምሮዎችን በተሳካ ሁኔታ ለመያዝ መምህሩ በአመራር ላይ ታላቅ ብልህነት እና ጥንቃቄን እንዲሁም በአስተዳደርም ጽናትን ተግባራዊ ማድረግ አለበት፡፡ CGAmh 306.1
አግባብነት ላላቸው መመሪያዎች ጥላቻ እና ንቀት እንኳን ብዙውን ጊዜ ይንጸባረቃል። አንዳንዶቹ ቅጣትን ለማምለጥ ያላቸውን ብልሃት ሁሉ ሲጠቀሙ፣ ሌሎች ደግሞ ስለ መተላለፍ ውጤት ግድየለሽነታቸውን ያሳያሉ። ይህ ሁሉ ስለ ትምህርታቸው አደራ የተሰጣቸውን ሰዎች የላቀ ትዕግስት እና ከፍተኛ ጥረትን የሚጠይቅ ነው፡፡625 CGAmh 306.2
ሕጎች ጥቂቶች እና በደንብ የተጠበቁ ይሆኑ — በትምህርት ቤትም ሆነ ቤት ውስጥ ጥበብ የተሞላበት ተግሣጽ ሊኖር ይገባል። የተማሪዎቹን ባህሪይ ለመምራት መምህሩ ህጎችን ማውጣት አለበት፡፡ እነዚህ ህጎች ጥቂቶች እና በደንብ መጠበቅ አለባቸው፣ አንዴ ከወጡ በኋላ መተግበር አለባቸው። እዚያ ውስጥ የተካተተ እያንዳንዱ መርህ ተማሪው ስለ ፍትህ ማመን እንዲችል በእርሱ ፊት መቅረብ አለበት። 626 CGAmh 306.3
መምህሩ ታዛዥነትን ማስከበር አለበት— በትምህርት ቤትም ሆነ ቤት ውስጥ፣ የስ ነስርዓት ጥያቄ ግንዛቤ ማግኘት አለበት። በትምህርት ቤት ክፍል ውስጥ በትር የሚጠቀሙበት አጋጣሚ ፈጽሞ ሊኖር እንደማይችል ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ነገር ግን በትምህርት ቤት ስለ እነርሱ የሚደረገውን ምክር እና ልመናን ሁሉን፣ ጸሎቶችና የነፍስ ሸክምን ሁሉ የሚቃወሙ ካሉ፣ እነርሱ መታዘዝ እንዳለባቸው እንዲገነዘቡ ማድረግ አስፈላጊ ነው። CGAmh 306.4
አንዳንድ አስተማሪዎች ታዛዥነትን ማስከበሩ የተመረጠ እንደሆነ አይሰማቸውም። ተግባራቸው ማስተማር ብቻ እንደሆነ ያስባሉ። እውነት ነው ማስተማር አለባቸው፡፡ ነገር ግን እነርሱ በፊታቸው የተቀረቡትን መርኾዎችን ችላ ሲሉ መምህሩ ስልጠን የመጠቀም መብት እንዳለው ባይሰማው ትምህርት ምን ጥቅም ይኖረዋል? 627 CGAmh 307.1
የወላጆችን የትብብር ይፈልጋል — መምህር የሥራውን ሸክም ብቻውን እንዲሸከም መተው የለበትም። እርሱ ሐዘኔታ፣ ርህራሄ እና ትብብር እና የእያንዳንዱን የቤተክርስቲያን አባል ፍቅር ይሻል፡፡ ወላጆች መምህሩ ለሚያደርጋቸው ጥረቶች አድናቆታቸውን በመግለጽ እርሱን ማበረታታት አለባቸው፡፡ በልጆቻቸው ውስጥ በጭራሽ እርሱን ለማዋረድ የሚያበረታታ ማንኛውንም ነገር መናገር ወይም ማድረግ የለባቸውም፡፡ CGAmh 307.2
ግን ብዙ ወላጆች ከመምህሩ ጋር እንደማይተባበሩ አውቃለሁ፡፡ በትምህርት ቤት ውስጥ የሚታየውን በጎ ተጽዕኖ ቤት ውስጥ አያሳድጉትም። በትምህርት ቤት ውስጥ የሚታየውን በጎ ተጽዕኖ ቤት ውስጥ ከመተግበር ይልቅ ልጆቻቸው የፈለጉትን እንዲያደርጉ፣ ያለ ቁጥጥር ወዲያ እና ወዲህ እንዲሄዱ ይፈቅዱላቸዋል፡፡ መምህሩ ታዛዥነትን በመፈልግ ስልጣን ሲጠቀም ልጆቹ ስለተያዙበት መንገድ የተጋነነ እና የተዛባ ዘገባ ለወላጆቻቸው ያቀርባሉ፡፡ መምህሩ ያደረገው መወጣት የነበረበትን የትጉህነቱን ኃላፊነት ብቻ ተወጥቶ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን ምንም እንኳን ልጆቻቸቸው የተሳሳቱ ቢሆኑም ወላጆች ለልጆቻቸው ያዝናሉ፡፡ እናም ትምህርት ቤት ውስጥ ገደብ ሲደረግባቸው እና ሥርዓት እንዲይዙ ሲደረጉ በጣም ምክንያታዊነት የጎደላቸው የሚሆኑ ብዙውን ጊዜ እራሳቸ በቁጣ ልጆቻቸውን የሚገዙ ወላጆች ናቸው፡፡ 628 CGAmh 307.3
ወላጆች የልጆቻቸውን ቅሬታ ከትምህርት ቤት ስልጣን እና ስነ-ስርዓት በተቃራኒ ተገቢ አድርገው ሲያቀርቡ፣ አሁን በእንደዚህ ዓይነት አስፈሪ ደረጃ የተስፋፋውን እያሽቆለቆለ ያለውን የግብረ ገብ ኃይል እንዲጨምር እያደረጉ መሆናቸውን አልተመለከቱም። የወጣትነት ብልሹነት እየጨመረ በመሆኑ በወጣቱ ዙሪያ ያለው እያንዳንዱ ተጽዕኖ የቀና መሆን አለበት፡፡ 629 CGAmh 307.4
ታማኙን መምህር ይደግፉት— ለልጆቻቸው ነፍስ ሊደረግላቸው የሚገባውን እንክብካቤ በጭራሽ ተሰምቷቸው የማያውቁ፣ እንዲሁም ተገቢውን ቁጥጥርና መመሪያ ያልሰጧቸው ወላጆች ልጆቻቸው ገደብ ሲደረግባቸው፣ ሲገሰጹ እና ሲታረሙ እጅግ በጣም መሪር ተቃውሞ የሚያሳዩት እነርሱ ናቸው። ከእነዚህ ልጆች መካከል አንዳንዶቹ ለቤተክርስቲያኑ አሳፋሪ እና ለአድቬንቲስቶች ስም አሳፋሪ ናቸው። 630 CGAmh 308.1
እነርሱ [ወላጆች] ልጆቻቸው ለአምላክ ተማኞች፣ ለመርኾ ታመኞች፣ እና ለእራሳቸው እና ለሚገናኙ ሰዎች ሁሉ ታማኞች እንዲሆኑ ያስተምሯቸው…፡፡ CGAmh 308.2
ይህንን ስልጠና የሚሰጡ ወላጆች መምህሩን ሊነቅፉ የሚችሉ አይሆኑም፡፡ የልጆቻቸው ፍላጎት እና የትምህርት ቤቱ ፍትህ የሚጠይው በተቻለ መጠን ኃላፊነታቸውን ለሚጋራው ሰው ድጋፍ እና አክብሮት ይሰጡት ዘንድ ነው፡፡7 CGAmh 308.3
መምህሩን ፍጹም በተማሪዎቹ ፊት አትውቀሱት— ወላጆች ሆይ ልጆቻቸችሁ የዘላለምን ሕይወት ያገኙ ዘንድ የቤተክርስቲያኑ ትምህርት ቤት እነርሱን ለማሠልጠን እና ለመገሠጽ ሲሞክር፣ አደገኛ እንደሆነ ቢሳማችሁም እንኳ በፍፁም በእነርሱ ፊት የእርሱን ተግባር አትንቀፉ፡፡ ልባቸውን ለአዳኙ እንዲሰጡ ከፈለጓችሁ ለድነታቸው ከመምህሩ ጥረቶች ጋር ተባበሩ። ለልጆች የመምህራንን ሥራ በሚመለከት ከነቀፌታ ቃላት ይልቅ የምስጋና ቃላትን ከእናቶቻቸው አፍ መስማት ምንኛ የተሻለ ነው፡፡ እንደነዚህ ያሉት ቃላት ልጆች መምህሩን እንዲያከብሩ ላይ ዘላቂ ስሜቶች እና ተጸዕኖ ለአስተማሪው አክብሮት እንዲኖራቸው ያደርጋሉ፡፡ 631 CGAmh 308.4
የመምህሩን ሥራ በተመለከተ ነቀፋ ወይም አስተያየት አስፈላጊ ሆነኖ ከተገኘ በግል ሊደረግለት ይገባል፡፡ ይህ ውጤታማ አለመሆኑን የተረጋገጠ ሆኖ ከተገኘ ጉዳዩ ለትምህርት ቤቱ አስተዳደር ኃላፊነት ወዳላቸው ይተላለፍ። ደህንነታቸው በከፍተኛ ደረጃ በእርሱ ላይ የተመሰረተውን ሰው ልጆች ለእርሱ ያላቸውን አክብሮት ዝቅ እንዲያደርጉ ምንም ነገር ማለት ወይም መድረግ የለባቸውም። 632 CGAmh 308.5
ወላጆች እራሳቸውን በመምህሩ ቦታ ቢያስቀምጡ እና የእያንዳንዱን በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን ክፍል እና የአእምሮ ደረጃ ማስተዳደር እና ሥነ-ሥርዓት ማስያዝ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ቢመለከቱ፣ ነገሮችን በተለየ መንገድ በጥልቀት ማየት ይችሉ ነበር፡፡ 633 CGAmh 309.1
ብዙውን ጊዜ አለመታዘዝ ከቤት ይጀምራል— ልጆች የፈለጉትን እንዲያደርጉ በመፍቀድ ወላጆች አፍቃሪዎች እንደሚሆኑ ራሳቸውን ይቆጥሩ ይሆናል፣ ነገር ግን እጅግ ከፍተኛ ጭካኔን እየተለማመዱ ናቸው፡፡ ልጆች ማመዛዘን የሚችሉ ሲሆን ምንም እንኳን እንደዚህ አይነቱን ርህራሄ በወላጆች እይታ ተገቢ ሆኖ ቢታያቸውም ነፍሳቸው አግባብነት በሌለው ርህራሄ ይጎዳል። ልጆቹ እያደጉ ሲሄዱ አለመታዘዛቸውም ያድጋል፡፡ አስተማሪዎቻቸው እነርሱን ለማስተካከል ሊሞክሩ ይችላሉ፣ ነገር ግን ብዙውን ጊዜ ወላጆች ለልጆቹን በመደገፍ ይቆማሉ፣ በዚህም ሳቢያ ክፋት ቢቻል ከበፊቱም በላቀ ማታለል አሁንም በጨለማ ሽፋን እያደገ ይቀጥላል። ሌሎች ልጆች በእነዚህ ልጆች የተሳሳተ አካሄድ ይስታሉ፣ ሆኖም ወላጆች ስህተቱን ማየት አይችሉም። በልጆቹ ስህተት ላይ ከሚያዝኑ አስተማሪዎች ይልቅ የልጆቻቸው ቃሎች ተሰሚነት ያገኛሉ። 634 CGAmh 309.2
ተባባሪ ባልሆኑ ወላጆች ሳቢያ የመምህሩ ሥራ እጥፍ ድርብ ይሆናል— ወላጆች ልጆቻቸውን ለማሠልጠን ቸል ማለታቸው የመምህሩን ስራ በእጥፍ ከባድ ያደርገዋል፡፡ ልጆች በወላጆቻቸው የተገለጠውን ያለመታዘዝ እና የማይመቹ ባሕሪያት አሻራ አርፎባቸዋል፡፡ ቤት ውስጥ ችላ ተብለው የትምህርት ቤቱን ስነ-ምግባር ጨቋኝ እና ከባድ አድርገው ይቆጥሩታል። እንደነዚህ ያሉ ልጆች በጥንቃቄ ካልተያዙ ባልተገራ እና በተበላሸ ባህሪያቸው ሌሎች ልጆችን ያበላሻሉ…። ልጆች ጉድለት ያለበት የቤት ውስጥ ሥልጠናን ለመጻረር በትምህርት ቤት ውስጥ የሚቀበሏቸው መልካም ነገሮች ወላጆች ልጆቻቸው በሚሰሯቸው ስህተቶች ላይ በሚያሳዩት ሐዘኔታ ምክንያት በንቀት እየታየ ነው፡፡ CGAmh 309.3
የእግዚአብሄርን ቃል የሚያምኑ ወላጆች ጠማማ አያያዛቸውን በመቀጠል በልጆቻቸው ላይ ክፉ የተፈጥሮ ዝንባሌዎቻቸው ማጽደቅ አለባቸው? የወቅቱን እውነት እናምናለን የሚሉ አባቶች እና እናቶች ወደ ልባቸው በመመለስ ያልተለወጡ ልጆቻቸውን ሐሰተኛ ምስክር በመቀበል ከአሁን ወዲያ በዚህ ክፋት ውስጥ ተካፋይ መሆን የለባቸውም፣ ከአሁን ወዲያ የሰይጣን መሳሪያዎችንም ሥራ ላይ ማዋል የለባቸውም፡፡ ለመምህራን የወላጆቹን ተጽዕኖዎች ሳይጨምር ከልጆች ተጽዕኖዎች ጋር መታገሉ በቂ ነው። 635 CGAmh 310.1