የልጅ አመራር
ምዕራፍ 43—የቤት ውስጥ ሥልጠና
አግባብነት ያለው ሥርዓት፣ ጥሩ ሥነ-ምግባር ያላቸው ቤተሰቦች—አግባብነት ያለው ሥርዓት፣ ጥሩ ሥነ-ምግባር ያላቸው ቤተሰቦችን— ማለትም የክርስትናን እውነተኛ ኃይል የሚያሳዩ ቤተሰቦችን ለዓለም የማቅረብ የክርስቲያን ነን ባዮች ኃላፊነት ነው፡፡ 440 CGAmh 221.1
ልጆችን በጥበብ ማሠልጠንና ማስተማር ቀላል ነገር አይደለም፡፡ ወላጆች ፍርድን እና የጌታን ፍርሃት በፊታቸው ይዞ ለማቆየት ሲጥሩ ችግሮች ይነሳሉ፡፡ ልጆች በልባቸው ውስጥ የታሰረውን ጠማማነትን ይገልጣሉ፡፡ እነርሱ የከንቱነት፣ በራስ የመመራት ፍቅርን፣ የመገደብ እና የስነ-ስርዓትን ጥላቻ ያሳያሉ። አታላይነትን ይለማመዳሉ እንዲሁም ውሸት ይናገራሉ። አያሌ ወላጆች ልጆችን ለእነዚህ ስህተቶች ከመቅጣት ይልቅ ከእይታ በታች ያለውን እንዳያዩ ወይም የእነዚህን ነገሮች ትክክለኛ ትርጉም እንዳያስተውሉ እራሳቸውን ያሳውራሉ፡፡ ስለዚህ ልጆች እግዚአብሔር የማይደግፋቸውን ባህሪያትን በመመስረት በማታለል ተግባራቸው ይቀጥላሉ፡፡ CGAmh 221.2
በአምላክ ቃል ውስጥ የተቀመጠው መሥፈርት አንዳንዶች እንደሚሉት፣ ልጆቻቸውን በማስተማር ረገድ ቀጥተኛ ጃኬት እንዲጠቀሙ በማይፈልጉ ወላጆች ገሸሽ ተደርጓል፡፡ ብዙ ወላጆች ለእግዚአብሄር ቅዱስ ቃል መሰረታዊ መርኾዎች ጠንካራ ጥላቻ አላቸው፣ ምክንያቱም እነዚህ መሰረታዊ መርሆዎች በእነርሱ ላይ ከፍተኛ ኃላፊነት ያሳርፋሉ፡፡ ነገር ግን ሁሉም ወላጆች እንዲኖራቸው የሚገደዱት የኋላ ኋላ እይታ፣ የእግዚአብሔር መንገዶች ምርጥ መሆናቸውን እና ብቸኛው የደህንነት እና የደስታ መንገድ እንደ ለእርሱ ፈቃድ በመታዘዝ የሚገኝ መሆኑን ያሳያል፡፡ 441 CGAmh 221.3
ልጆችን መግታት ቀላል ሥራ አይደለም— በዚህ ወቅት ባለው የማኅብረተሰቡ ሁኔታ፣ ወላጆች ልጆቻቸውን መግታትና በመጽሐፍ ቅዱስ ትክክለኛ ደንብ መሠረት ማስተማር ቀላል ሥራ አይደለም፡፡ ልጆቻቸውን ከእግዚአብሔር ቃል ህጎች ጋር በሚስማማ መንገድ ሊያሠለጥኗቸው እና እንደ ጥንቱ አብርሃም፣ ከኋላቸው ቤተሰቦቻቸውን እንዲያዝዙ ሲፈልጉ፣ ልጆች ወላጆቻቸውን ከሚፈለገው በላይ ጠንቃቆች እና አላስፈላጊ ፍፁምነትን የሚፈልጉ እንደሆኑ ያስባሉ፡፡ 442 CGAmh 221.4
መግታትን በተመለከተ የተሳሳቱ ሀሳቦች— ወላጆች፣ የእግዚአብሔርን በረከት ከፈለጋችሁ፣ አብርሃም እንዳደረ ያድርጉገው አድርጉ፡፡ ክፉውን ተቆጣጠሩ፣ መልካሙን አበረታቱ፡፡ ከልጆች ዝንባሌ እና ደስታ ጋር በተያያዘ በምክር ፈንታ አንዳንድ ጊዜ ትእዛዝ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል። 443 CGAmh 222.1
አንድ ልጅ ተፈጥሮአዊ ስሜቶቹን እንዲከተል መፍቀድ እርሱ እንዲበላሸ እና በክፉው ብቃት እንዲኖረው ማድረግ ማለት ነው፡፡ ብልህ ወላጆች ለልጆቻቸው “የራስህን ምርጫ ተከተል፤ ወደ ፈለክበት ሂድ፣ የፈለከውን አድርግ” ነገር ግን “የጌታን ትምህርት ስማ” ብለው አይናገሩም፡፡ የቤት ውበት እንዳይበላሽ የጥበብ ህጎች እና መመሪያዎች መውጣት እና መተግበር አለባቸው። 444 CGAmh 222.2
የአካን ቤተሰብ ለምን ጠፋ— ከአካን ጋር ተያያዥ የነበሩ ሁሉ የእግዚአብሔር ቅጣት ሰለባዎች ለምን እንደሆኑ ተገንዝበው ያውቃሉ? ይህ የሆነው በእግዚአብሔር ሕግ ታላቅ መስፈርት ውስጥ በተሰጡት መመሪያ መሠረት የሰለጠኑ እና ያልተማሩ ስለነበሩ ነው። የአካን ወላጆች ልጃቸውን የጌታን ቃል ከመታዘዝ ነፃ እንደሆነ እንዲሰማው አድርገው አስተምረውታል፡፡ በህይወቱ ውስጥ የሰረጹ መሰረታዊ መርሆዎች ከልጆቹን ብልሹ አደርጎ እንዲይዛቸው መርቶታል፡፡ አእምሮ በአእምሮ ላይ ይሠራል፣ አጸፋም ይመልሳል፣ እናም አካን ከእራሱ ጋር የነበረውን ግንኙነት ያካተተው ቅጣት፣ ሁሉም በበደሉ ውስጥ ተሳታፊ የመሆናቸውን እውነታ ያሳያል፡፡ 445 CGAmh 222.3
ዓይነ ስውር የወላጅነት ፍቅር በሥልጠና ውስጥ ትልቁ እንቅፋት— የወላጅ የቸልተኝነት ኃጢአት አለም አቀፋዊ ሆኗል ማለት ይቻላል። በተፈጥሮአዊ ትስስር ከእኛ ጋር ተያያዥነት ላላቸው ሰዎች አብዘኛውን ጊዜ ዕውር የፍቅር ስሜት ይኖረናል፡፡ ይህ የፍቅር ስሜት ረጅም ርቀት ይዘልቃል፤ በጥበብ ወይም እግዚአብሔርን በመፍራት ሚዛናዊ አይሆንም። ዓይነ ስውር የወላጅነት የፍቅር ስሜት ለልጆች በሚሰጥ አግባብነት ባለው ስልጠና ሂደት ውስጥ ትልቁ እንቅፋት ነው፡፡ ይህም በጌታ የተፈለገውን ተግሣጽ እና ስልጠና ያግዳል። በዚህ ጊዜ፣ በዚህ የፍቅር ስሜት ምክንያት፣ ወላጆች ምክንያታዊነታቸውን ያጡ ይመስላሉ፡፡ ይህ ለክፉዎች እንደሚደረግ የርህራሄ ምሕረት — ማለትም ፍቅር ተብሎ በሚጠራው ካባ ሥር ያለ ጭካኔ ይመስላል፡፡ ይህ ሕፃናትን ወደ ጥፋት የሚያደርስ የተዳፈነ አደገ ነው። 446 CGAmh 222.4
ወላጆች ለእግዚአብሔር ሕግ ታዛዥ ከመሆን ይልቅ የተፈጥሮ ስሜትን በማርካት አደጋ ላይ ናቸው፡፡ ብዙ ወላጆች፣ ልጆቻቸውን ለማስደሰት፣ እግዚአብሔር የሚከለክለውን ይፈቅዱላቸዋል። 447 CGAmh 223.1
ወላጆች ልጆች ምን መሆን እንዳለባቸው ኃላፊነት አለባቸው— ቤት ውስጥ እንዳሉ አስተማሪዎች አባት እና እናት ልጆች የመቆጣጠሪያውን መስመር በእራሳቸው እጅ እንዲያስገቡና አስቸጋሪዎች እንዲሆኑ ሲፈቅዱላቸው፣ ልጆቻቸው ከዚህ በተቃራኒ መሆን ስለነበረባቸው ነገር ሃላፊነት አለባቸው፡፡ 448 CGAmh 223.2
ለልጆቻቸው ባላቸው ጭፍን ፈቅር የራስ ወዳድነት ምኞታቸውን በማርካት ዝንባሌዎቻቸውን የሚከተሉ እና ኃጢአትን ለመገሠጽ እና ክፉን ለማረም የእግዚአብሔር ስልጣን እንዲኖረው የማያመጡ ሰዎች፣ እግዚአብሔርን ከሚያከብሩ ይልቅ ክፉ ልጆቻቸውን እንደሚያከብሩ ያሳያሉ፡፡ እግዚአብሔርን ከማክበር ይልቅ ዝናቸውን ለመጠበቅ ይጨነቃሉ፣ ጌታን ከማስደሰት ይልቅ ልጆቻቸውን ለማስደሰት ይመኛሉ…፡፡ CGAmh 223.3
ስህተትን ለመገሠጽ በጣም ጥቂት ድፍረት ያላቸው ወይም በሰንፍና ወይም ፍላጎት በማጣት ቤተሰቦቻቸውን ወይም የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን ለማፅዳት ከፍተኛ ጥረት የማያደርጉ፣ ግዴታቸውን ባለመወጣት ምክንያት ለሚመጣው ክፋት ተጠያቂ ይሆናሉ። የወላጅነትን እና የፓስተርነትን ሥልጣን በመጠቀም መቆጣጠር የነበረብንን ኃጢአቶች ባለመቆጣጠራችን ልክ ተግባሮቹ የኛ እንደሆኑ ተጠያቂዎች እንሆናለን፡፡ 449 CGAmh 223.4
ለአድልዎ ቦታ የለውም — ወላጆች በገዛ ልጆቻቸው መካከል አድልዎ እንደሚያደርጉ እጀግ ተፈጥሯዊ ነው፡፡ በተለይም እነዚህ ወላጆች እራሳቸው የላቀ ችሎታ እንዳላቸው የሚሰማቸው ከሆነ ልጆቻቸውን ከሌሎች ልጆች እንደሚበልጡ አድርገው ይቆጥራሉ፡፡ በመሆኑም በሌሎች ላይ አጥብቀው የሚገስጹትን በልጆቻቸው ላይ እንደ ብልጠት እና ቀልድ በመቁጠር ያልፏቸዋል። ይህ አድልዎ ተፈጥሮአዊ ቢሆንም ኢ-ፍትሐዊ እና ክርስቲያናዊ ያልሆነ ነው። የልጆቻችን ስህተቶች ሳይታረሙ እንዲሄዱ ስንፈቅድላቸው ትልቅ ስህተት እየፈጸምን ነው፡፡ 450 CGAmh 223.5
ከክፉ ጋር አትደራደሩ— የእግዚአብሔር መንግሥት ከክፉ ነገር ጋር እንደማይደራደር ግልፅ መደረግ አለበት፡፡ በቤትም ሆነ በትምህርት ቤት ውስጥ አለመታዘዝ በትዕግስት መታለፍ የለበትም፡፡ በእርሱ እንክብካቤ ሥር ያሉትን የሰዎች ደኅንነት በልቡ ያለ ወላጅ ወይም አስተማሪ ከመታዘዝ ለማምለጥ ሲል ሥልጣንን ከሚቃወም ወይም ወደ ማታለል ዘወር ከሚል ወይም ከሚያድበሰብስ ግትር የራስ ወዳድነት ፍላጎት ጋር አይደራደርም፡፡ ከስህተት አድራጎት ጋር የሚደራደር፣ በማባበል ወይም በጉቦ ለሕግ ታዛዥነትን ለማስጠበቅ የሚፈልግ እና በመጨረሻም ከተፈለገው ነገር ፈንታ ምትክን የሚቀበል ፍቅር ሳይሆን ስሜታዊነት ነው፡፡ 451 CGAmh 224.1
በዛሬው ጊዜ በብዙ ቤተሰቦች ውስጥ ብዙ የራስ ወዳድነት ፍላጎቶችን ማርካት እና አለመታዘዝ ሳይታረሙ ይታለፋሉ፣ ወይም በተቃራኒ በልጆች ላይ የባሰ ክፉ ባህሪይን የሚፈጥር የልዕልና እና የጌትነት መንፈስ ይታያል። ወላጆች አንዳንድ ጊዜ የልጆችን ሕይወት አደጋ ላይ በሚጥል ርህራሄ ባጣ አይነት መንገድ ያርሟቸዋል፣ በዚህም ሳቢያ ለአባት፣ ለእናት፣ ለወንድሞች እና እህቶች ያላቸውን አክብሮት ያጣሉ፡፡ 452 CGAmh 224.2
ወላጆች ትክክለኛ መርኾዎችን መረዳት ይሳናቸዋል— ወላጆች አምላክ የሰጣቸውን ሥልጣን በመጠቀም ረገድ የሚያሳዩት ጅልነት የሚያሳዝን ነው። በሌሎች ነገሮች ሁሉ ወጥነት ያላቸው እና ብልህ የሆኑ ሰዎች በትናንሽ ልጆቻቸው ስልጠና ላይ ሊካተቱ የሚገባቸውን መሰረታዊ መርሆችን መረዳት ይሳናቸዋል፡፡ በማንኛውም ሥፍራ የሚገጥማቸውን አታላይና አደገኛ ተጽዕኖዎች የማያውቁ ልምድ የሌላቸው አዕምሮዎችን በቀና መስመር ለመምራት ትክክለኛ መመሪያ፣ እግዚአብሔርን የመምሰል ምሳሌ እና ጽኑ ውሳኔ እጅግ ተፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ትክክለኛውን መመሪያ መስጠት ያቅታቸዋል፡፡ 453 CGAmh 224.3
ወላጆች የራሳቸውን አስተሳሰብ እና ፍጹም ያልሆኑ ሀሳቦቻቸውን ለመከተል ሲሉ መለኮታዊ እቅድን ከመከተል ስለተለዩ ታላቅ መከራ በሰብአዊው ቤተሰብ ላይ ደርሷል። ብዙ ወላጆች ስሜትን ይከተላሉ። ለአሁንም ሆነ ለመጻኢው የልጆቻቸው ደህንነት የታሰበበት ሥልጠና እንደሚያስፈልግ ይረሳሉ። 454 CGAmh 225.1
እግዚአብሔር በተዛበ መንገድ ለተረደረገ ምሪት ሰበብን አይቀበልም— ትክክለኛ አካሄድ ቢከተሉ ኖሮ፣ ልጆቹ ጥሩ እና ስምሙ ባህሪያትን መመስረት ሲችሉ፣ አመፅ በልጆች ልብ ውስጥ በተደጋጋሚ የሚመሰረተው በወላጆች የተሳሳተ ሥልጠና ሳቢያ ነው፡፡ 455 CGAmh 225.2
ወላጆች ልጆቻቸውን የመግራት፣ የማስተማር እና የማሠልጠን ሥልጣን ቢኖራቸውም፣ ያንን ሥልጣን ለእግዚአብሔር አሳልፈው ይሰጣሉ፡፡ እርሱ ከእነርሱ ንጹህ፣ እንከን የለሽ፣ እና የማያወላውል መታዘዝን ይፈልጋል፡፡ ከዚህ ሌላ ምንም ነገር አይታገስም። በተዛባ መንገድ ለተመሩ ልጆች ሰበብ አይቀበልም። 456 CGAmh 225.3
ተፈጥሯዊ የግትርነት መንፈስን ማሸነፍ— አንዳንድ ልጆች በተፈጥሮ ከሌሎቹ የበለጠ ግትር እና ለመገራት የማይረቱ፣ እናም በዚህ ምክንያት እጅግ የማይስቡ እና የማይመቹ እራሳቸውን ያደርጋሉ፡፡ እናት ይህን የመሰለ የባህሪይ ደረጃ ለመያዝ የሚያስችል ጥበብ ከሌላት እጅግ አሳዘኝ ጉዳይ ይከተላል፤ እንዲህ ያሉት ልጆች ለጥፋታቸው የሚሆን የራሳቸውን መንገድ ይከተላሉ። ነገር ግን በልጅነት ብቻ ሳይሆን ይበልጡን በሳል በሚሆኑበት ዓመታት እና በልጅነት የስምምነት እጦት ምክንያት ለአካለ መጠን የደረሱ ወንዶች እና ሴቶች ሲሆኑ ልጆቻቸውን መገደብ በተሳናት እናት ላይ ምሬትን ማብዛት እንዴት አስፈሪ ነው፡፡ 457 CGAmh 225.4
ልጅን “ከአንተ ወይም ከአንቺ ጋር ምንም ነገር መሥራት አንችልም” አትበሏቸው፡፡”— ልጅዎ “ከአንተ ወይም ከአንቺ ጋር ምንም መሥራት አልችልም” ብለው ሲናገሩ በጭራሽ እንዳይሰሙ፡፡ ወደ እግዚአብሔር ዙፋን መቅረብ እስከቻልን ድረስ፣ እኛ እንደ ወላጆች እንደዚህ አይነቱን ቃል ከመናገር እፍረት ሊይዘን ይገባል፡፡ ወደ ኢየሱስ ጮኹ፣ እርሱም ትንንሽ ልጆችቻችሁን ወደ እርሱ በማምጣት ይረዳችኋል። 458 CGAmh 225.5
ስለ የቤተሰብ አስተዳደር በትጋት ማጥናት— እናቶች ሌሎች ያሏቸውን የማስተዳደር ችሎታ፣ ይህን ልዩ ተሰጥኦ እነርሱ እንደሌላቸው ሲናገሩ ሰምቻለሁ፡፡ በዚህ ረገድ ጉድለታቸውን የተገነዘቡ ሁሉ የቤተሰብን ጉዳይ እጅግ በትጋት የሚያጠኑት ርዕሰ ጉዳይ ማድረግ አለባቸው፡፡ ሆኖም ግን በጣም ጠቃሚ የሆኑ የሌሎች ሰዎች ሀሳቦች ሳይታሰብበት እና ያለማስተዋል ተቀባይነት ማግኘት የለባቸውም፡፡ እነዚህ ለእያንዳንዷ የእናት ሁኔታ ወይም ቤተሰብ ውስጥ ላለው ለእያንዳንዱ የልጅ ልዩ ፀባይ እና ስሜት እኩል የሚስማሙ ላይሆኑ ይችላሉ፡፡ እናት የሌሎችን ተሞክሮ በጥንቃቄ ታጥና፣ በእራሷ እና በሌሎች መካከል ያለውን የአሰራር ዘዴዎች ልዩነት ልብ ትበል፣ ተጨባጭ ጠቃሜታ ያላቸው የሚመስሉትንም በጥንቃቄ ትመረምር፡፡ አንዱ የመግራት ዘዴ ተፈላጊውን ውጤት የማያመጣ ከሆነ ሌላ ዕቅድ ይሞከር እና ውጤቶቹም በጥንቃቄ ይታዩ። CGAmh 226.1
እናቶች፣ ከሁሉም በላይ፣ ከአሳቢነት እና ምርመር ጋር እራሳቸውን ማላመድ አለባቸው፡፡ በዚህ ሁኔታ ጸንተው ከቀጠሉ፣ ጉድለት እንዳለባቸው የሚያስቡትን ችሎታ እያገኙ መሆናቸውን፣ በልጆቻቸው ትክክለኛ ባህሪይ ለመቅረጽ እየተማሩ መሆናቸውን ይመለከታሉ፡፡ ለዚህ ሥራ የተሰጠው የጉልበት እና ሀሳብ ውጤት በታዛዥነታቸው፣ ቀላል የአኗኗር ዘዴን በመከተላቸው፣ በመጠን በመኖራቸው እና በንጽህናቸው ይታያል፤ ለተደረገውም ጥረት ሁሉ መልሶ አብዝቶ ይከፍላል። 459 CGAmh 226.2
ወላጆች በመግራት ሥራ መተባበር አለባቸው— እናት በልጆቿ ውስጥ መልካም የክርስትያን ባህሪይን ለመመስረት በምታደርገው ጥረት የአባት ትብብርን ማግኘት አለባት፡፡ ከልክ በላይ የሚያፈቅር አባት እርማት መስጠት አስደሳች ስላልሆነ የልጆቹን ስህተቶች ላለማየት ዓይኖቹን መዝጋት የለበትም። 460 CGAmh 226.3
በልጁ አእምሮ ውስጥ ትክክለኛ መርኾዎች መመስረት አለባቸው፡፡ ወላጆች በዚህ የመግራት ሥራ አንድነት ከፈጠሩ ልጅ ከእርሱ ምን እንደሚፈለግ ይገነዘባል፡፡ ነገር ግን አባት በንግግርም ሆነ በእይታ እናት የምትሰጠውን ተግሣጽ የማይደግፍ መሆንኑን የሚያሳይ ከሆነ፣ እጅግም ጥብቅ እንደ ሆነች ከተሰማው እና በልመና እና በማሞላቀቅ ብልሹነታቸውን ለማስተካከል ቢያስብ ልጅ ይበላሻል፡፡ አዛኝ በሆኑ ወላጆች ማታለል ይፈጸማል፣ ወዲያውም ልጁም እንደፈለገ መሆንን ይማራል፡፡ በልጆቻቸው ላይ ይህንን ኃጢአት የሚፈጽሙ ወላጆች ለነፍሳቸው ጥፋት ተጠያቂ ናቸው፡፡22 CGAmh 227.1
የፍቅር እና የሥልጣን ተጽዕኖ ጥምረት— በቤት ውስጥ የፀሐይ ብርሃን እንዲኖር የሰማይ ፀጋ ባህርይዎ ላይ እንዲያበራ ይፍቀዱ። ሰላም፣ አስደሳች ቃላት እና ደስታኛ ገጽታ ይኑር። ይህ ዓይነ ስውር ፍቅር አይደለም፣ ፍጹም ጭካኔ የሆነው ኃጢአትን የሚያበረታታ ያ ጥበብ በጎደለው ማሞላቀቅ አይደለም፣ ልጆች ወላጆቻቸው ላይ እንዲሰለጥኑ እና ለስሜቶቻቸው ባሪያዎች የሚያደርግ የውሸት ፍቅር አይደለም። የወላጅ አድልዎ መኖር የለበትም፣ ጭቆና መኖር የለበትም፤ የፍቅር እና የሥልጣን ጥምረት ቤተሰብ ላይ ትክክለኛውን ቅርጽ ላይ ይፈጥራል፡፡ 461 CGAmh 227.2
በመግራት ሂደት ውስጥ የእግዚአብሔርን ባሕርይ ያሳዩ— የመጽሐፍ ቅዱስን መመሪያ ተግባራዊ ስታደርጉ ጽኑ እና ቆራጥ ሁኑ፣ ነገር ግን ከስሜት ሁሉ ነፃ ሁኑ። በትናንሽ ልጆቻችሁ ፊት ኃይለኛ እና ምክንያታዊነት የሌላችሁ ስትሆኑ ከእናንት ጋር ተመሳሳይ እንዲሆኑ እያስተማራችኋቸው እንደሆነ አስታውሱ። ልጆቻችሁን በእግዚአብሔር ቁጥጥር ስር እንዳለ የጦር አዛዥ ጥበበኛ መምህር ወደ መግራት ሂደት በማምጣት እንዲያስተምሩ እግዚአብሔር ይፈልጋል። ቤት ውስጥ የሚለውጠው የእግዚአብሔር ኃይል ሲተገበር፣ እናንት ራሳችሁ የዘወትር ተማሪዎች ትሆናላችሁ። የክርስቶስን ባሕርይ የምትወክሉ ትሆናላችሁ፣ እናም በዚህ አቅጣጫ የምታደርጉት ጥረት እግዚአብሔርን ያስደስተዋል፡፡ ለትናንሾቹ የጌታ ቤተሰብ አባላት መደረግ ያለበትን ስራ በጭራሽ ቸል አትበሉ። እናንት የቤታችሁ ብርሃን የምትሆኑ፣ ወላጆች ናችሁ። እንግዲያው ደስ በሚያሰኙ ቃላትና በሚያነቃቁ የድምፅ ቃናዎች ብርሃናችሁ ይብራ፡፡ ራሳቸውን እንዲቆጣጠሩ ወደ እግዚአብሔር በመጸለይ መርዛቸውን አስወግዱ፡፡ ብርሃናችሁን ስለሚመለከቱ መልአክቶች ቤታችሁ ውስጥ ይሆናሉ፡፡ ለልጆቻችሁ የሰጣችኋቸው ሥልጠና በትክክል ከተመራ ቤታችሁ እስከ ዓለም ድረስ ጠንካራ እና ግልጽ ፈሳሽ ውሃ በመሆን ወደ ፊት ይጓዛል። 462 CGAmh 227.3
ከትክክለኛ መርሆዎች ማፈንገጥ አያስፈልግም— በጥንት ጊዜ፣ የወላጅነት ስልጣን ይከበር ነበር፤ በዚያን ጊዜ ልጆች ለወላጆቻቸው ይገዙ፣ ይፈሩ እና ያከብሯቸውም ነበር፤ ነገር ግን በዚህ የመጨረሻ ዘመን ይህ ሥርዓት ተለውጧል። አንዳንድ ወላጆች ለልጆቻቸው ይገዛሉ። የልጆቻቸውን ፍላጎት ለመቃወም ይፈራሉ፣ ስለዚህም ለእነርሱ ይገዛሉ፡፡ ነገር ግን ልጆች በወላጆች ጣሪያ ሥር እና በእነርሱ ላይ ጥገኛ ሆነው እስካሉ ድረስ፣ በእነርሱ ቁጥጥር ሥር መሆን ይገባቸዋል፡፡ ወላጆች ትክክለኛ አመለካከታቸው ተቀባይነት እንዲያገኙ በማድረግ በውሳኔ መንቀሳቀስ አለባቸው፡፡ 463 CGAmh 228.1
ሆን ተብሎ የሚደረግ አለመታዘዝ መቆጣጠር ካልተቻለ ከፍተኛ እርምጃዎችን ይውሰዱ — አንዳንድ ልል እና ምቾት ወዳጅ ወላጆች ልጆቻቸው ከቤት እንዳይወጡ በመፍራት የማይታዘዙ ልጆቻቸው ላይ ሙሉ ሥልጣናቸውን መጠቀም ይፈራሉ። ለአንዳንዶች በወላጆቻቸው የሚቀርቡ በረከቶች ላይ ለመኖር ቤት ከመቆየት፣ እና በተመሳሳይ ጊዜ የሰዎች እና የመለኮታዊ ስልጣናንን ሁሉ ከመርገጥ ይልቅ ይህን ማድረጉ የተሸለ ነው። እንደነዚህ ላሉ ልጆች መኖር ልፋትን የሚጠይቅ እንደሆነ እንዲማሩ እጅግ የተሻለ እንደሆነ አድርገው የሚያስቡትን ያን ሙሉ ነፃነት ማግኘት በጣም ትርፋማ ተሞክሮ ሊሆን ይችላል፡፡ ወላጆቻቸው ከቤት ለመሸሽ ለሚያስፈራራ ልጅ እንዲህ በሉት “ልጄ፣ ትክክለኛና ተገቢ ደንቦችን ከማክበር ይልቅ ከቤት መውጣትን የወሰንክ እንደሆነ እኛ አናግድህም፡፡ ከልጅነትህ ጀምሮ ከሚንከባከቡህ ወላጆች ይልቅ ዓለም ምቹ እንደሆነ ካሰብህ ስህተትህን ራስህ መማር አለብህ፡፡ ለሥልጣኑ ለመገዛት ወደ አባትህ ቤት መምጣት ሲትፈልግ በደስታ እንቀበልሃለን፡፡ ግዴታዎች የጋራ ናቸው፡፡ ምግብ፣ አልባሳት እና የወላጅ እንክብካቤ ስታገኝ፣ ለቤት ህጎች እና ሁለገብ ሥነ-ስርዓት የመገዛት ግዴታ አለብህ፡፡ ቤቴ በትንባሆ ግማት፣ በበልግና ወይም በስካር ሊረክስ አይችልም። የእግዚአብሔር መላእክት ወደ ቤቴ እንዲመጡ እፈልጋለሁ፡፡ ሰይጣንን ለማገልገል ሙሉ በሙሉ ቁርጥ ውሳኔ ካደረክ፣ ልክ ቤት ውስጥ እንደሚሆነው ሁሉ አብረሃቸው መሆን ከምትወደው ጓደኞች ጋር ትሆናለህ፡፡” CGAmh 228.2
እንዲህ ዓይነቱ አካሄድ በሺዎች የሚቆጠሩ የቁልቁል ጉዞን የሕይወት ታሪክን ያግዳል። ነገር ግን ብዙ ጊዜ ልጆች በራሳቸው ሕይወት ላይ አደጋ የሚያመጣ ነገር ሊያደርጉ እንደሚችሉ ያውቃሉ፣ ነገር ግን ብልህ እናት ስለ እነርሱ ትማጸናለች፣ መተላለፋቸውን ትሰውራለች። ብዙ ዓመፀኛ ልጆች ወላጆቻቸው እነርሱን ለመከልከል ድፍረቱ ስላሌላቸው ይፈነጥዛሉ…፡፡ ታዛዥነትን አያስገድዱም፡፡ እንደነዚህ ያሉት ወላጆች ልጆቻቸውን ብኩን እንዲሆኑ እያበረታቱ እና ጥበብ በጎደለው ማሞላቀቅ እግዚአብሔርን እያዋረዱ ናቸው፡፡ በትምህርት ቤቶች እና በኮሌጆች ውስጥ ለመቆጣጠር በጣም አስቸጋሪ አካል የሚሆኑት እነዚህ አመፀኞች እና ብልሹ ወጣቶች ናቸው፡፡ 464 CGAmh 229.1
መልካምን ለማድረግ አትታክቱ — የወላጆች ሥራ ቀጣይ ነው። ለአንድ ቀን ያህል በአሸናፊነት ተይዞ ለሚቀጥለው ቀን ችላ መባል የለበትም፡፡ ብዙዎች ሥራውን ለመጀመር ዝግጁ ናቸው፣ ነገር ግን በዚያው ለመቀጠል ፈቃደኞች አይደሉም። አንዳች ታላቅ ነገርን ለመስራት፣ አንዳች ታላቅ መስዋዕትነትን ለመክፈል ጉጉት አላቸው፣ ነገር ግን በየእለት ተዕለት ኑሮ ጥቃቅን ነገሮች፣ በየሰዓቱ አስቸጋሪ ዝንባሌዎችን የመቁረጥ እና የማሰልጠን፣ ጥቂት በጥቂት እንዳስፈላጊነቱ መመሪያን የመስጠት፣ የመገሰጽ ወይም የማበረታታት ሥራ ወደ ኋላ ያፈገፍጋሉ። ልጆቻቸው በተከታታይ ደረጃዎች ሳይሆን በፍጥነት ስህተቶችን እንዲያስተካክሉ እና እና በአንድ ጊዜ ትክክለኛ ባህሪይን እንዲቀርጹ ማየትን ይመኛሉ፤ እናም ተስፋዎቻቸው ወዲያውኑ ስላማይከናወኑ ተስፋ ይቆርጣሉ። እንደነዚህ ያሉት ሰዎች ሁሉ “ባንዝልም በጊዜው እናጭዳለንና መልካም ሥራን ለመሥራት አንታክትም” የሚለውን የሐዋሪያውን ቃል በማስታወስ ይበረታቱ፡፡ 465 CGAmh 229.2
የሰንበት ጠባቂ ልጆች ለሚደረግባቸው ቁጥጥር ትዕግስት የለሾች እና ወላጆቻቸው በጣም ጥብቅ እንደሆኑ ሊያስቡ ይችላሉ፤ ከባድ ስሜቶች በልባቸው ውስጥ እንኳን ሊነሱ እና ቅር ሊሰኙ ይችላሉ፣ ለእነርሱ የአሁኑ ጊዜ፣ ለመጻኢው እና ለዘለአለም መልካም እየሰሩ ባሉት ደስተኛ ያልሆነ አመለካከት ሊኖራቸው ይችላል። ነገር ግን ሕይወት ለጥቂት ዓመታት ቢቆይ ኖሮ እነርሱ ተሞክሮ ባሌላቸው ዓመታት ወላጆቻቸው ላደረጉላቸው ጥብቅ እንክብካቤ እና የታማኝነት ክትትል ወላጆቻቸውን ይባርካሉ።28 CGAmh 229.3
ከእግዚአብሄር ቃል የተሰጡ ተግሳጾችን ያንብቡ— ልጆች በሚሳሳቱበት ጊዜ ወላጆች በተለይ ለጉዳዩ ገጣሚነት ያላቸውን ተግሳጾችን ከእግዚአብሄር ቃል ላይ በርህራሄ ሊያነቡላቸው ይገባል፡፡ መከራ ሲደርስባቸው፣ በሚፈተኑበት፣ ወይም ተስፋ በሚቆርጡበት ጊዜ፣ ውድ ወደ ሆኑት የመጽናኛ ቃላት ጠቁሟቸው፣ በኢየሱስም ላይ እምነት እንዲጥሉ በትህትና ምሯቸው። በዚህ መንገድ የልጅነት አእምሮ ንጹህ እና ክቡር ወደ ሆነ ሊመራ ይችላል፡፡ እናም የህይወት ታላላቅ ችግሮች እና ከሰብአዊ ዘር ጋር ያለው የእግዚአብሔር ግንኙነት ለአዕምሮአቸው ግልጽ ሲሆን እና መለኮታዊ የእውነት ትምህርቶች ልብ ላይ ሲቀረጽ የማመዛዘን ኃይሎች ጥቅም ላይ ይውላሉ፣ ሂሊናም ዕርዳታን ይፈልጋል፡፡ በዚህ መንገድ ወላጆች ልጆቻቸው ለመጻኢ ህይወት ብቁ ይሆኑ ዘንድ በየእለቱ ባህሪያቸውን ሊቀርጹ ይችላሉ፡፡ 466 CGAmh 230.1