የልጅ አመራር
የልጅ አመራር
መቅድም
ጋብቻ ሁለት ልቦችንና ሕይወትን በፍቅር ሲያስተሳስር፣ እና አዲስ ቤት ሲመሰረት፣ የጋብቻ መስራቾቹ ቀደምት ዓለማ ለአዲሱ ቤት ሞገስ የሚሆኑ ልጆች በአግባቡ ያድጉ ዘንድ ነው፡፡ “የልጁ ሥርዓት ምንድነው?” የሚለው የቀደምቱ የማኑሄ ጥያቄ፣ የዚህ ዘመን ወላጆች ይንከባቡት ዘንድ በአደራ የተሰጣቸውን ውድና ረዳት አልባ የሆነውን የልጃውን ፊት ሲመለከቱ አጥብቀው በጥንቃቄ የሚጠይቁት ጥያቄ ነው፡፡ CGAmh 13.1
በልጆች መምሪያ ላይ የተሰጠውን መመሪያ አስፈላጊነት በውል የምንረዳው መጽሐፉ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ያለውን ጉልህ ሥፍራና ርዕሱ በትንቢት መንፈስ ጽሁፎች ውስጥ በተደጋጋሚና በዝርዝር መጠቀሱን ስንገነዘብ ነው፡፡ በአያሌ መጽሐፎቿ ውስጥ፣ በተለይም ደግሞ በቤተ እምነቱ የተለያዩ መጽሄቶች ላይ በየሳምንቱ ብቅ ሲል በነበረው ተግባራዊ የክርስቲያን አኗኗር ተብሎ በሚታወቅ ጽሁፍ ላይ፣ ኤለን ጂ ኋይት ለወላጆች ዘርፈ ብዙ ምክሮችን ገልጻለች፡፡ በተጨማሪም፣ የአያሌ ቤተሰብ በመቶ የሚቆጠሩ ሲገጥማቸው ለነበሩት ችግሮች እንደ ችግሩ አይነት የሰጠቻቸውን መፍትሔዎች የግል ሕይወት ተሞክሮ ምስክርነቶችን አቅርባለች፡፡ በእነዚህ ጽሁፎችና የግል ተሞክሮዎች ውስጥ ወላጆች ሊመሩባቸው የሚገባቸውን መርሆዎችንና ሊከተሏቸው የሚገባቸውን ቅደም ተከተሎችን ልክ በራዕይ እንደታዩዋት ገልጻለች፡፡ CGAmh 13.2
ኤለን ጂ ኋይት በሕይወቷ የመጨረሻ ዓመታት ላይ “የእናት ተግባር እና በልጆቿ ላይ ያላትን ተጽዕኖ” ለክርስቲያን ወላጆች የሚያብራራ መጽሐፍ የማቅረብ ምኞት ነበራት፡፡ በቅርብ ጊዚያት በቀረበው የአድቬንቲስት ቤት በመባል በሚታወቅ መጽሐፍ እና ተጓዳኝ ሥራዎች፣ ይህ ምኞት ከግብ ደርሷል፡፡ እግዚአብሔር ለወላጀች ኃላፊነት እንደሰጣቸው ሁሉ ለልጆች አግባብነት ያለውን ሥልጠና በመስጠት ረገድ የዚህ ቅጽ እጅግ ጠቃሚ፣ አስገራሚና አድማሰ-ሰፊ ያላቸው ምክሮች ተጽዕኖ የሚገለጡት በጥንቃቄና በፀሎት ብቻ ሲነበብ ነው፡፡ CGAmh 13.3
ኤለን ጂ ኋይት የአራት ልጆች እናት መሆኗ የተሠጣትን መመሪያዎች በእውቀትና በርህራሄ እንድታቀርብ ዘንድ ረድቷታል፡፡ በሌሎች ሰዎች ፊት ያቀረበቻቸው በተግባር የተደገፉ መርሆዎች በአንባቢዎች ልብ ውስጥ እርግጠኛነትን አስገኝቶላቸዋል፡፡ CGAmh 14.1
የታተሙና ለሕትመት ያልበቁ የኤለን ጂ ኋይት ጽሑፎች ሁሉም፣ ይህን የልጆች መምሪያን ለመዘጋጀት ተሰብስበዋል፡፡ የእያንዳንዱ ጽሑፍ ምንጭ ማጣሻዎች በየምዕራፎቹ መጨረሻ ላይ ይገኛሉ፡፡ የዚህ ቅጽ ይዘት በሰባ ዓመታት ቆይታ ውስጥ ከተጻፉት አያሌ ምንጮች አንድ ላይ ስለተሰበሰበ፣ አልፎ አልፎ ሊወገዱ የማይችሉ የሐሳብና የአድራሻ ሁኔታ መቋረጥ ይከሰታል፣ ምክንያቱም አረፍተ-ነገሮቹ በተለምዶአዊ የአርዕስት አገባብ ቅደም ተከተል የተቆራኙ ስለሆነ ነው፡፡ አዘጋጆቹ የተለያዩ አረፍተ-ነገሮችን በመምረጥና በማደረጀት እና ርዕስ በመስጠት ሥራ ተወስነዋል፡፡ CGAmh 14.2
የልጆች መምሪያ የተዘጋጀው በኤለን ጂ ኋይት ጽሁፎች አደራ ጠበቂ ቦርድ ምሪት ዋሽንግተን ዲ.ሲ በሚገኘው ጽ/ቤታቸው ውስጥ በመሆን ነበር፡፡ ሥራው የተሰራው ኤለን ጂ ኋይት ለአደራ ጠባቂዎቿ ለሕትመት ካልቀረቡና ከታተሙ ጽሑፎቿ ወስጥ አንድ ላይ የተቀናጀ ጽሑፍ ለሕትመት መቅረብ እንዳለበት የሰጠችውን መመሪያ መሠረት በማድረግ ነበር፡፡ CGAmh 14.3
ይህ ቅጽ እጅግ አስፈላጊነት ያለው ነው፡፡ ዘላለማዊው ዓለማ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ይገኛል፡፡ ዘርዘር ባለ ሁኔታ የቀረቡ የሥርዓታዊነት፣ የባህሪይ ዕድገት፣ እና የአካልና የመንፈስ ትምህርቶችን ያዘሉ ምክሮች ብልህ በሆኑ ወላጆች እንደ ሀብት የሚካበቱ ናቸው፡፡ ይህ ቅጽ፣ ከአድቬንቲስ ቤተሰብ፣ መልዕክት ለወጣቶች እና ኤለን ኋይት ለወላጆችና ለወጣቶች የሰጠቻቸውን ምክሮችን ካዘሉ ሌሎች መጽሐፎች ጎን በመቆም፣ እናቶችና አባቶች እጅግ ወሳኝ በሆነው ተግባራቸው ላይ መምሪያ በመሆን ያገለግላቸው ዘንድ የአሳታሚዎችና የኤለን ጂ ኋይት ጽሑፎች አደራ ጠበቂዎች ልባዊ ምኞት ነው፡፡ CGAmh 14.4