ቀደምት ጽሑፎች

61/73

60—ጽኑው መድረክ

የመንጋውን እምነት ለማናጋት ለሚጥሩት አንዳችም ፊት ባለመስጠት በጽናት የቆሙትን ተመለከትኩ፡፡ እግዚአብሔር እነዚህን ህዝቦች በይሁንታ ዐይን ይመለከታቸው ነበር፡፡ ቅደም ተከተሉቻቸውን ጠብቀው የተቀመጡ ሦስት መልእክቶችን ተመልክቼ የነበረ ሲሆን እነርሱም የመጀመሪያው፣ የሁለተኛውና የሦስተኛው መልአክ መልእክቶች ነበሩ፡፡ አብሮኝ የነበረው መልአክ «እነዚህን መልእክቶች የሚጋርድ ወይም የሚገታ ወዮለት፡፡ የእነዚህ መልእክቶች እውነተኛ አስተውሎ አስፈላጊነቱ ከፍ ያለ በመሆኑ የነፍሳት የመጨረሻው መዳረሻ መልእክቶቹን በመቀበላቸው ላይ መተማመን ያደርጋል” አለኝ፡፡ አሁንም ወደ መልእክቶቹ በመወሰድ የእግዚአብሔር ህዝቦች ምን ያህል በከበረ መልኩ እነዚህን ተሞክሮዎች የግላቸው እንዳደ ረጉ ተመለከትኩ፡፡ ተሞክሮው መገኘት የቻለው በብዙ ሥቃይና በከፋ ውዝግብ ነበር፡፡ እግዚአብሔር እነዚህን ህዝቦች በማይነቃነቅ ጠንካራ መስ ረት ላይ እስኪያቆማቸው ድረስ ደረጃ በደረጃ መርቷቸዋል፡፡ ግለሰቦች ወደ መድረኩ በመቅረብ መሰረቱን ሲመረምሩ ተመልክቻለሁ:: አንዳንዶች በደስታ ፈጥነው ሲወጡበት ሌሎች ደግሞ በመሰረቱ ላይ እንከን ለማግኘት አሰሳ ማድረግ ጀምረው ነበር እነዚህ ሰዎች አንዳንድ መሻሻሎች ተደርገው መድ ረኩ ይበልጥ ፍጹም እንዲሆንና ሰዉ አብልጦ እንዲደሰት ተመኝተው ነበር፡፡ ጥቂቶች ከመድረኩ ወርደው በመመርመር በትክክለኛ መሰረት አልቆመም ብለው በይፋ ተናግረዋል፡፡ ነገር ግን ሁሉም በመድረኩ ላይ በጽናት በመቆም ከመድረኩ ወርደው አቤቱታ ሲያቀርቡ የነበሩት ማጉረምረማቸውን ተተው እንዲወጡ ይገፋፏቸው ነበር፡፡ መድረኩ የተገነባው የግንበኞች ሁሉ እራስ በሆነው እግዚአብሔር እንደመሆኑ እነዚህ ሰዎች ይጣሉ የነበረው ከእርሱ ጋር ነበር ጽኑ ወደ ሆነው መድረክ የመራቸውን አስገራሚ አምላካዊ ሥራ በመመርመር ዐይኖቻቸውን በአንድነት ወደ ሰማይ በማንሳት ድምጾቻቸውን ከፍ ኣድርገው ለእግዚአብሔር ክብር ሰጡ፡፡ ይህ ድርጊት በማጉረምረም መድረኩን ጥለው በወረዱ በአንዳንዶች ላይ ተጽእኖ በማሳደሩ እነዚህ ሰዎች ዳግመኛ ትህትና በተሞላው ማንነት ወደ መድረኩ ወጡ፡፡ EWAmh 190.1

ወደ መጀመሪያው የክርስቶስ ምጽአት እወጃ ተወሰድኩ፡፡ ዮሐንስ ለየሱስ ምጽአት መንገዱን ያመቻች ዘንድ በኤልያስ መንፈስና ኃይል ተልኮ ነበር፡፡ የዮሐንስን ምስክርነት የተቃወሙ ሁሉ የየሱስ አስተምህሮ አካል የመሆን ዕድል አላገኙም ነበር፡፡ የእርሱን ምጽአት በሚያበስረው መልእክት ላይ የነበራቸው ተቃውሞ እርሱ መሲህ መሆኑን የሚያመላክቱ ጠንካራ ማስ ረጃዎችን ለመቀበል ዝግጁ ሊሆኑ የማይችሉባቸው ሁናቴዎች ውስጥ ዘፈቃቸው፡፡ ሰይጣን የዮሐንስን መልእክት የተቃወሙት ሁሉ በተቃውሞአቸው እንዲገፉበት በመምራት ክርስቶስን እንዲቃወሙና እንዲሰቅሉት አደረገ፡፡ ይህን በማድረጋቸው ስለ ስማያዊው መቅደስ ትምህርት ሊሰጣቸው ይችል የነበረውን በጴንጤቆስጤ ወቅት የወረደውን በ ረከት የማይቀበሉበት ሁናቴ ውስጥ እራሳቸውን ፈረጁ የቤተመቅደሱ መጋረጃ ለሁለት መቀደድ በአይሁዳውያኑ ይቀርቡ የነበሩ መስዋዕቶችና ሥርዓቶች ተቀባይነት ማግኘታቸው እንዳከተመለት አሳየ፡፡ ታላቁ መስዋዕት በመሰጠቱና ተቀባይነት በማግኘቱ በጴንጤቆስጤ ወቅት ወርዶ የነበረው መንፈስ ቅዱስ የደቀመዛሙርቱን አእምሮ ከምድራዊው መቅደስ አንስቶ የሱስ የገዛ ደሙን ይዞ ወደ ገባበት ወደ ሰማያዊው መቅደስ ወሰደው፡፡ አይሁዳውያኑ ግን በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ተተዉ፡፡ እነዚህ ህዝቦች በደኅንነት እቅድ ውስጥ ሊኖሯቸው ይችሉ የነበሩትን ብርሃኖች በሙሉ በማጣት ጥቅመ ቢስ በነበሩት መሥዋዕቶቻቸውና ሥርዓቶቻቸው ላይ ተጣብቀው ቀሩ፡፡ ሰማያዊው መቅደስ የምድራዊውን ቦታ ተከቶ ቢወስድም እነርሱ ግን ስለ ተደረገው ለውጥ አንዳችም ዕውቀት አልነበራቸውም:: በዚህ የተነሳ በቅዱሱ ስፍራ በየሱስ ገቢራዊ በሚሆነው የምልጃ ሥራ ተጠቃሚ መሆን አልቻሉም፡፡ EWAmh 190.2

በዙዎች አይሁዳውያኑ ክርስቶስን በመቃወም መስቀላቸውን ሲያስቡ የፈጸሙት ድርጊት ይዘገንናቸዋል፡፡ በአርሱ ላይ የደረሰውን አሳፋሪ ውርደት ሲመለከቱ እርሱን እንደሚወዱት በማመን እንደ ጴጥሮስ እንደማይክዱት ወይም እንደ አይሁዳውያኑ እንደማይሰቅሉት ያስባሉ፡፡ ነገር ግን የሁሉንም ልብ የሚያነበው እግዚአብሔር ለየሱስ አለን የሚሉትን ፍቅር ወደ ፈተና አምጥቶት ነበር፡፡ የመጀመሪያውን መልአክ መልእክት ተቀባይነት ማግኘት መላው ሰማይ በጥልቅ ጉጉት ይመለከት ነበር፡፡ ነገር ግን የሱስን እንወደዋለን የሚሉና የመስቀሉን ታሪክ ሲያነቡ እምባዎቻቸውን የሚያፈሱ ብዙዎች በዳግም ምጽአቱ የምሥራች ላይ ተሳልቀዋል፡፡ መልእክቱን በደስታ በመቀበል ፋንታ ከንቱ ስሜት ነው ብለው በይፋ ይናገሩ ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች የክርስቶስን መገለጥ የወደዱትን በመጥላት ከየቤተክርስቲያኑ አባ ረሯቸው: የመጀመሪያውን መልአክ መልክት የተቃወሙ ከየሱስ ጋር በእምነት ወደ ሰማያዊው ቅድስተቅዱሳን ክፍል እንዲገቡ ሊያዘጋጃቸው ይችል በነበረው በእኩለ ሌሊቱ ጩኸት ተጠቃሚ እንዳልነበሩ ሁሉ በሁለተኛ ው መልአክ መልእክትም ተጠቃሚ መሆን አይችሉም ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች ሁለቱን የኋለኛ መልእክቶች መቃወማቸውን ተከትሎ ማስተፃ ላቸው በጽልመት ውስጥ ስለወደቀ ወደ ቅድስተቅዱሳኑ ክፍል ያመላክት በነበረው የሦስተኛው መልአክ መልእክት ውስጥ አንዳችም ብርሃን ማየት አልቻሉም ነበር፡፡ አይሁዳውያኑ የሱስን በመስቀል ላይ እንደቸነከሩት ሁሉ የክርስቶስ ተከታዮች ነን ይሉ የነበሩ ቤተክርስቲያኖችም እነዚህን መልእክቶች በመስቀላቸው ወደ ቅድስተቅዱሳን የሚወስደውን መንገድ በመሳት በዚያ ቦታ ሆኖ ኃጢአት በሚያስተሰርየው በየሱስ አማላጅነት ተጠቃሚ መሆን አልቻሉም፡፡ ጥቅመ ቢስ የነበረውን መስዋዕት ያቀርቡ እንደነበሩት አይሁዳውያን እነርሱም የሱስ ትቶት ወደ ሄደው ክፍል ያነጣጠረውን ፋይዳ ቢስ ጸሎታቸውን ያቀርቡ ነበር፡፡ ሰይጣን በእነዚህ የኃይማኖት መልክ ባላቸው ክርስቲያን ነን ባይ ህዝቦች መሳት በመደሰት አእምሮአቸውን ወደ ራሱ ይስብ ነበር፡፡ በኃይል በመሥራት እንደ ወጥመድ በተጠቀመባቸው ምልክቶችና ድንቃድንቅ ተአምራቶች አማካኝነት ወደ ጉያው ይመራቸው ነበር፡፡ ሁሉንም በተለያዩ አቅጣጫዎች ያስት ነበር: ሰይጣን የተለያዩ አእምሮዎችን ለማሳት የሚጠቀምባቸው ልዩ ልዩ ማታለያ ዘዴዎች አሉት፡፡ አንዳንዶች አንደኛውን የማታለያ ዘዴ በታላቅ ፍርሐት ይመለከቱና ሌላውን ለመቀበል ግን ዝግጁ ይሆናሉ፡፡ ሰይጣን አንዳንዶችን ከሙታን መንፈስ ጋር መገናኘትን (ስፕሪችዋሊዝምን) ተገን በማድረግ ያታልላቸዋል፡፡ እንዲሁም እንደ ብርሃን መልአክ ሆኖ በመምጣትም ሆነ በሐሰተኛ የተሐድሶ አራማጆች አማካኝነት በምድሪቱ ላይ ተጽእኖውን ያዛምታል፡፡ ቤተ ክርስቲያኖች በእነዚህ ነገሮች አብልጠው ደስ በመሰኘት ሥራው የሌላ መንፈስ ውጤት ሆኖ ሳለ እነርሱ ግን እግዚአብሔር በአስደናቂ መልኩ በመካከላቸው እየሠራ እንደሆነ አድርገው ያስባሉ፡፡ ነገር ግን ደስታው ይከስምና ዓለምንም ሆነ ቤተክርስቲያንን ከቀድሞው የላቀ የከፋ ሁናቴ ውስጥ ትቶ ይሄዳል፡፡ EWAmh 191.1

እግዚአብሔር ስሙን ብቻ በተሸከሙ አድቬንቲስቶችና በወደቁት አብያተክርስቲያናት ውስጥ ታማኝ ልጆች እንዳሉት ተመልክቻለሁ:: መቅሰፍቶቹ ከመውረዳቸው አስቀድሞ በእነዚህ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ያሉ አገልጋዮችም ሆኑ ህዝቦች ጥሪው ሲደርሳቸው እውነትን በደስታ ይቀበላሉ፡፡ ይህን የሚያውቀው ሰይጣን ከታላቁ የሦስተኛው መልአክ ጩኸት አስቀድሞ በእነዚህ ኃይማኖታዊ አካላት መሃል የደስታ ስሜትን በመፍጠር እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር እንደሆነ እንዲያስቡ ያደርጋል፡፡ ነገር ግን ከብርሃኑ አንጸባራቂነት የተነሳ ታማኝ የሆኑ ሁሉ የወደቁትን አብያተክርስቲያናት ትተው በመውጣት አቋማቸውን ከትሩፋኑ ጋር ያጸናሉ፡፡ EWAmh 192.1