ቀደምት ጽሑፎች
57—ሌላ ማብራሪያ
በምድር ላይ ገቢራዊ እየሆነ ባለው ሥራ ዙሪያ መላው ሰማይ የነበ ረውን ፍላጎት እንድመለከት ተደርጌ ነበር የምድር ሕዝቦች ለዳግም ምጽአቱ እንዲዘጋጁ ያስጠነቅቃቸው ዘንድ የሱስ ኃያል የሆነውን መልአክ ወደ ምድር ልኮ ነበር፡፡ መልአኩ ትእዛዙን ተቀብሎ ከየሱስ ዘንድ ሲወጣ ብሩህና በግርማ የተሞላ ብርሃን በፊቱ ሄደ፡፡ የዚህ መልአክ ተልዕኮ ምድርን በክብሩ ማብራትና ስውን ከሚመጣው የእግዚአብሔር ቁጣ ማስጠንቀቅ እንደሆነ ተነግሮኝ ነበር:፡፡ ብዙዎች ብርሃኑን ተቀብለው የነበረ ሲሆን ከመካከላቸው በአንዳንዶቹ ጽናት፤ በሌሎቹ ደግሞ ደስታና መመሰጥ ይታይ ነበር፡፡ ብርሃኑን የተቀበሉ ሁሉ ፊቶቻቸውን ወደ ስማይ በማዞር ክብርን ለአግዚአብሔር ሰጡ፡፡ ምንም እንኳ ብርሃኑ በሁሉም ላይ በማብራቱ ጥቂቶች ብርሃኑን ተከትለው ቢመጡም ነገር ግን ከልባቸው አልተቀበሉ ትም ነበር፡፡ ብዙዎች ታላቅ የመከራ ስሜት ተሰምቶአቸው ነበር፡፡ አገልጋዮችና ሕዝቡ ከክፉው ጋር ግንባር በመፍጠር በኃያሉ መልአክ የበራውን ብርሃን ለመቀበል አሻፈረኝ ቢሉም ፤ ነገር ግን መልእክቱን የተቀበሉ ሁሉ እራሳቸውን ከዓለም በማግለል አርስ በርሳቸው ቅርበት ፈጠሩ፡፡ EWAmh 179.2
ሰይጣንና መክቱ የሰዎች አእምሮ ከዚህ ብርሃን እንዲያፈነግጥ በመመኘት በከባድ ሥራ ተጠምደው ነበር ይህን ብርሃን የተቃወሙ ቡድኖች በጽልመት ውስጥ ተተዉ፡፡ የመጣላቸው መልእክት ሥረ መሰረቱ ከሰማይ መሆኑን አምነው የተቀበሉት የእግዚአብሔር ሕዝቦች እያጎለበቱ ያለውን ባህሪ መልአኩ በጥልቅ ፍላጎት በመመልከት ይመዘግብ እንደነበር አይቻለሁ፡፡ የሱስን እንወደዋለን ይሉ የነበሩ ብዙዎች ፊታቸውን በፌዝና በጥላቻ ከሰማያዊው መልእክትበማዞራቸው መልአኩ በመዝገቡ ላይ አሳፋሪ ማስታወሻ ያዘባቸው፡፡ የሱስ ተከታዮቹ ነን በሚሉ በቸልታ መታየቱን ተከትሎ መላው ሰማይ በቅዱስ ቁጣ ተሞላ፡፡ EWAmh 180.1
ጌታቸውን በተጠባበቁት ሰዓት ማየት ባለመቻላቸው በኃዘን የተሞሉትን ታማኞች ተመልክቻለሁ፡፡ ወደፊት የሚሆነውን በመሸሸግ ሕዝቡ ውሳኔ ላይ ሊደርስ ወደ በሚችልበት ነጥብ ማምጣት አምላካዊው ዓላማ ነበር፡፡ ክርስቶስ በዚህ ጊዜ ይመጣል ተብሎ ባይሰበክ ኖሮ አምላካዊው ሥራ ከታመለት ግብ መድረስ ባልቻለ ነበር፡፡: ሰዎች ወደፊት እውን ከሚሆነው ከፍርድና ከፍርድ ምርመራ ጋር ቁርኝት ከነበራቸው ታላላቅ ክስተቶች እንዲርቁ በማድረግ ሰይጣን ብዙዎችን እያሳተነበር EWAmh 180.2
ጊዜው እያለፈ በሄደ ቁጥር የመልአኩን መልእክት ያልተቀበሉ ሕዝቦች መልእክቱን ከናቁት ጋር ህብረት ፈጥረው በኃዘን ውስጥ በነበሩት ላይ መሳለቅ ጀመሩ፡፡ መላእክት የክርስቶስ ተከታዮች ነን ይሉ የነበሩን ሕዝቦች ሁናቴ በአጽንኦት ይከታተሉ ነበር፡፡ ክርስቶስ ይመጣል ተብሎ ተቆርጦ የነበ ረው ጊዜ ማለፍ የእነዚህን ሕዝቦች እውነተኛ ማንነት ለማረጋገጥ በማስቻሉ ብዙዎች ተመዝነው ቀለው ተገኙ፡፡ እነርሱ አፋቸውን ሞልተው ክርስቲያን ነን ቢሉም ነገር ግን በእያንዳንዱ እርምጃ ክርስቶስን ከመከተል ተሰናክለው ነበር፡፡ ሰይጣን እነዚህን ሕዝቦች በወጥመዱ ውስጥ በማስገባቱ ከብሮ ነበር፡፡ አብላጫው ሕዝብ ቀጥተኛውን ጎዳና እንዲስት በማድረጉ እነዚህ ሰዎች በሌ ላ አቅጣጫ ወደ ሰማይ ለመግባት እየሞከሩ ነበር፡፡ መላእክት ንጹህና ቅዱስ የሆኑት ሕዝቦች ዓለምን ከሚወዱ ግብዝ ኃጢአተኞች ጋር በጽዮን ተቀላቅለው ተመልክተው ነበር፡፡ አመጸኞቹ ቅዱሳኑን እያውኩ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን መላእክት እውነተኞቹን የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ይጠብቁ ነበር፡፡ የሱስን ለማየት ልባቸው በማያባራ ምኞች ይቃጠል የነበረ ሕዝቦች ስለ ዳግም ምጽአቱ እንዳይናገሩ በነዚሁ የሱስን እንከተላለን በሚሉ ስዎች ተከልክለው ነበር፡፡ መላእክት ይህን ትዕይንት በመመልከት የጌታቸውን መገለጥ ለወደዱት ትሩፋን ድጋፋቸውን ሰጧቸው፡፡ EWAmh 180.3
ሌላ ኃያል መላእክ ወደ ምድር እንዲወርድ ተላከ፡፡ የሱስ በእጁ ላይ ጽሑፍ ያስቀመጠለት ይህ መልአክ ወደ ምድር ሲወርድ «ባቢሎን ወደቀች፣ ወደቀች» በማለት ጮኸ፡፡ ከዚያ> አዝነው የነበሩ ሕዝቦች ዳግመኛ ዐይኖቻ ቸውን ወደ ሰማይ አንስተው የጌታቸውን መገለጥ በእምነትና በተስፋ ሲመለከቱ አየኋቸው:: ነገር ግን ብዙዎች ያንቀላፉና በደካማ አስተሳሰብ ውስጥ የነበሩ ይመስሉ እንደነበር በገጽታቸው ላይ ከሚታየው ጥልቅ ኃዘን መመልከት ችዬ ነበር: በኃዘን ላይ የነበሩት ወገኖች የነበሩበትን ጊዜና የራእዩን ፍጻሜ በትዕግሥት መጠበቅ አንዳለባቸው ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ተመለከቱ፡፡ 1843 ላይ ጌታቸውን እንዲመለከቱ የመራቸው ተመሳሳይ ማስረጃ በ1844 ላይም እንዲሁ እንዲጠባበቁት ቢያደርጋቸውም ነገር ግን አብላጫው ሕዝብ በ1843 ላይ የተስተዋለውን ያህል ከፍ ያለ ብርታት እንዳልነበረው ተመልክቻለሁ፡፡ ለዚህ መንስዔው ደርሶባቸው የነበረው ኃዘን እምነታቸው እንዲቀንስ በማድረጉ ነው፡፡ EWAmh 180.4
የእግዚአብሔር ሕዝቦች ከሁለተኛው መልአክ ጩኸት ጋር ህብረት በፈጠሩ ጊዜ የሰማይ ሠራዊት ውጤቱን በጥልቅ ፍላጎት ተመለከቱ፡፡ የክርስናን ስም የተሸከሙ ብዙዎች በኃዘን በነበሩት ላይ ሲያሾፉና ሲሳለቁ ተመለከቱ፡፡ ከእነዚህ ሰዎች አንደበት ይወጡ የነበሩ «ዛሬም ወደ ሰማይ አልሄዳችሁም!» የተሰኙትን ንግግሮች መላእክት ይመዘግቡ ነበር፡፡ መልእኩ «በእግዚአብሔር ላይ ይዘብታሉ” ሲል ነገረኝ፡፡ በጥንት ጊዜ የተፈጸመ ተመሳሳይ ኃጢአት እንድመለከት ተደርጌ ነበር ኤልያስ ወደ ሰማይ በተነጠቀ ጊዜ ካባው በኤልሳዕ ላይ ወደቀ፡፡ ከዚያም የእግዚአብሔርን ሰው ሰለመናቅ ከወላጆቻቸው የተማሩ ክፉ ወጣቶች እየተከተሉ «አንተመላጣ፤ ውጣ! አንተመላጣ ውጣ!” እያሉ አፌዙበት፡፡ ይህ በእግዚአብሔር አገልጋይ ላይ የደረሰ ስድብ እግዚአብሔርን እንደ መስደብ ስለሚቆጠር ወዲያውኑ ቅጣታቸውን አገኙ፡፡ በተመሳሳይ በቅዱሳኑ ወደ ሰማይ የመሄድ ጽንሰ ሃሳብ ላይ ዘለፋ የሰነዘሩ፧በአምላካዊው ቁጣ በመጎብኘት ከፈጣሪያቸው ጋር መቀለድ ቀላል አለመሆኑ እንዲሰማቸው ይደረጋል EWAmh 181.1
የሱስ እየተዳከመ የነበረው የሕዝቡ እምነት ታድሶና ተበረታቶ የሁለተኛ ውን መልአክ መልእክት እንዲያስተውሉ የሚያዘጋጇቸውን ሌሎች መላእክትን በፍጥነት ልኮ ነበር፡፡ መላእክቱ ታላቅ ኃይልና ብርሃን ከየሱስ በመቀበል ሁለተኛውን መልአክ በማገዝ የተሰጣቸውን ተልዕኮ ለመፈጸም በፍጥነት ወደ ምድር ሲበሩ ተመልክቻለሁ፡፡ መላእክቱ «ሙሽራው እየመጣ ነው ወጥታችሁ ተቀበሉት!» በማለት ሲጮኹ ታላቅ ብርሃን በሕዘቡ ላይ አንጸባረቀ: ከዚያም እነዚህ አዝነው የነበሩ ሕዝቦች ከተቀመጡት ብድግ ብለው ከሁለተኛው መልአክ ጋር ኅብር በመፍጠር «ሙሽራው እየመጣ ነው፤ ወጥታችሁ ተቀበሉት!» ሲሉ ተመለከትኩ፡፡ በመላእክቱ ላይ ይታይ የነበረው ብርሃን በየአቅጣጫው የነበረውን ጽልመት ገፈፈው፡፡ ሰይጣንና መላእክቱ ይህን ብርሃን ከመራጨት ለመግታትና የታለመለትን ፅጤት እንዳያመጣ ለማድረግ ተመኙ፡፡ እነዚህ ህዝቦች ከፍተኛ መጠን ያለው ብርሃንና ኃይል ቢኖራቸውም ነገር ግን በክርስቶስ ዳግም ምጽአት ዙሪያ ዓለምን ማሳመን አለመቻላቸውንና በዚህም እግዚአብሔር ሕዝቡን አስቷል በሚል ሰይጣንና መላእክቱ የሰማይ መላእክትን ተገዳደሯቸው፡፡ ሆኖም እነርሱን መቋቋም ያልተቻለው ሰይጣን የሰዎች አእምሮ ብርሃኑን እንዳይቀበል አጥሮ ለመያዝ ፍልሚያ ቢያደርግም የእግዚአብሔር መላእክት ግን ተግባራቸውን ቀጠሉ፡፡ EWAmh 181.2
ብርሃኑን የተቀበሉ ሁሉ በደስታ ተሞልተው በጽናት ወደ ሰማይ ሲያመሩና የየሱስን መገለጥ ሲናፍቁ ታዩ:፡፡ አንዳንዶች ሲያነቡና በታላቅ መከራ ውስጥ ሆነው ሲጸልዩ ነበር ዐይኖቻቸው ወደ ራሳቸው እንጂ ወደ ላይ ለመመልከት ድፍረት አልነበራቸውም፡፡ ከሰማይ የተላከ ብርሃን በላያቸው አጥልቶ የነበረውን ጽልመት ስለ ከፈለው በተስፋ መቁረጥ ስሜት አቀርቅረው የነበሩ ዐይኖቻቸው ቀና ብለው ወደ ላይ ተመለከቱ:፡፡ በዚህን ጊዜ በእያንዳንዱ ገጽታ ላይ በምስጋና የተሞላ ቅዱስ ደስታ ፍንትው ብሎ ታየ፡፡ የሱስና መላው የመላእክት ሰራዊትም እነዚያን እየተጠባበቁ ያሉ ታማኝ ወገኖች በአዎንታ ዐይን ተመለከቷቸው:፡ EWAmh 182.1
እነዚያ የመጀመሪያውን መልአክ መልእክት የተቃወሙ የሁለተኛውን መልአክ ብርሃን ማግኘት ባለመቻላቸው «ሙሽራው እየመጣ ነው ወጥታችሁ ተቀበሉት!» በተሰኘው መልእክት ኃይልና ክብር ተጠቃሚ መሆን አልቻሉም:: እነዚህ ሕዝቦች የሱስን በማሳዘናቸውና በመቃወማቸው ፊቱን አኮሳትሮባቸው የነበረ ሲሆን መልእክቱን የተቀበሉ 7ን በክብር ደመና ተጠቅልለው ነበር፡፡ እነዚህ ወገኖች እግዚአብሔርን አጥብቀው በመፍራት አምላካዊውን ፈቃድ ያውቁ ዘንድ እየጸለዩ ይጠባበቁ ነበር ሰይጣንና መላእክቱ ይህ መለኮታዊ ብርሃን ወደ እግዚአብሔር ሕዝቦች እንዳይደርስ ለመዝጋት ጥረት ያደርጉ እንደነበር ተመልክቻለሁ፡፡ ነገር ግን እየተጠባበቁ የነበሩት ወገኖች ብርሃኑን የከበረ አድርገው አስhያዙና ዐይኖቻቸውን ከምድር ላይ በማንሳት ሽቅብ የሱስ ላይ እስከተከሏቸው ድረስ ሰይጣን እነዚህን የከበሩ ጨረሮች መከልከል አልተቻለውም ነበር፡፡ ከሰማይ የተሰጠው መልእክት ሰይጣንንና መላእክቱን በቁጣ እንዲሞሉ በማድረግ የሱስን እንወደዋለን ይሉ የነበሩ ሕዝቦች ምጽአቱን በመናቅ ይጠባበቁ በነበሩት የታመኑ ወገኖች ላይ እንዲያሾፉና እንዲሳለቁ መንስዔ ሆነ፡፡ የእግዚአብሔር ልጆች እርሱን እንከተላለን በሚሉ ወንድሞቻቸው የደረሰባቸውን እያንዳንዱን ስላቅና ማሾፍ መልአኩ ይመዘግብ ነበር፡፡ EWAmh 182.2
ብዙዎች «ሙሽራው እየመጣ ነው፧ ወጥታችሁ ተቀበሉት!» ብለው ለመጮ ድምጾቻቸውን ከፍ በማድረግ የስን መገለጥ ካልወደዱት ወንድሞቻቸው ተነጥለው ሄዱ፡፡ የሱስ የእርሱን ዳግም ምጽአት ከተቃወሙትና ከናቁት ላይ ፊቱን በማዞር መላእክት ህዝቡን ከረከሱት መሃል ለይተው ንዲያወጡ ትእዛዝ ሲሰጥ ተመልክቻለሁ፡፡ ለመልእክቱ ታማኝ የነበሩት ነጻ ሆነውና ህብረት ፈጥረው ሲቆሙ ቅዱስ ብርሃን በላያቸው በራ፡፡ እነዚህ ሕዝቦች ምድራዊውን ነገር በማውገዝና ጥቅሞቻቸውን ሁሉ መስዋዕት አድርገው በማቅረብ ተወዳጁን አዳኛቸውን ለማየት ተስፋ በማድ ረግ ዐይኖቻቸውን ሰማይ ላይ ተከሉ፡፡ በውስጣቸው የነገሠውን ሰላምና ደስታ የሚናገር በቅድስና የተሞላ ብርሃን በገጽታቸው ላይ አብርቶ ይታይ ነበር፡፡ የእነዚህ ወገኖች የመፈተኛ ሰዓት በመቅረቡ ያበረቷቸው ዘንድ የሱስ መላእክቱን ላከ፡፡ እነዚህ የክርስቶስን መገለጥ ይጠባበቁ የነበሩ ህዝቦች መፈተን የነበረባቸውን ያህል እንዳልተፈተኑ ተመልክቻለሁ:፡፡ ከስህተት የጸዱም አልነበሩም:: ሰዎች ሲወርድ ሲዋረድ ከመጣው ከአረማውያንና ከጳጳሳት ስህተቶች እራሳቸውን እንዲጠብቁ፣ ልቦቻቸውን በጥንቃቄ እንዲመ ረምሩና መጽሐፍ ቅዱሳቸውን እንዲያጠኑ ማስጠንቀቂያውን በመስደድ ረገድ የእግዚአብሔርን ምህረትና መልካምነት ተመልክቻለሁ፡፡ እግዚአብሔር በእነዚህ መልእክቶች አማካኝነት ከፍ ባለ ኃይል ለህዝቡ የሚሠራበትንና እነርሱም ትእዛዛቱን ሁሉ የሚጠብቁበትን መንገድ እውን አደረገ፡፡ EWAmh 182.3