ቀደምት ጽሑፎች
50—ሞት እንጂ ዘላለማዊ ሥቃይ አለመኖሩ
ሰይጣን የማታለል ሥራውን የጀመረው በኤደን ገነት ነበር፡፡ እርሱ ሔ ዋንን «መሞት እንኳ አትሞቱም” ነበር ያላት፡፡ ይህ እንግዲህ ነፍስ አትሞትም የተሰኘው አስተምህሮው መጀመሪያ ነበር፡፡ እርሱ ይህን ማታለያውን ከዚያን ጊዜ አንስቶ አሁን ድረስ ይዞ በመጓዝ በግዞት ያሉ የእግዚአብሔር ልጆች እስኪስቱ ድረስ ይገፋበታል፡፡ በኤደን ወደ ነበሩት አዳምና ሔዋን እንድመለከት ተደርጌ ነበር፡፡ እነርሱ ከተከለhለው ፍሬ ከበሉ በኋላ እጆቻቸውን ዘርግተው ዳግመኛ በመብላት የማይሞቱ ኃጢአተኞች ሆነው እንዳይቀሩ ለመከላከል ወደ ዛፏ በሚወስደው መንገድ ላይ ነበልባላዊ ሰይፍ ተቀመጠ፤ እነርሱም ተባረሩ፡፡ የዚህ ዛፍ ፍሬ ዘላለማዊ ያደርግ ነበር፡፡ መልአኩ «ከአዳም ቤተሰብ ውስጥ ነበልባላዊውን ሰይፍ አልፎ ከህይወት ዛፍ የበላ ማን ነው?” በማለት ሲጠይቅ ሰማሁ፡፡ ከዚያም ሌላው መልአክ «ከአዳም ቤተሰብ ውስጥ ነበልባላዊውን ሰይፍ አልፎ ከፍሬው የበላ ማንም ባለመኖሩ ሟች ያልሆነ ኃጢአተኛ የለም” በማለት መለሰለት፡፡ ኃጢአት የምትሠራ ነፍስ የትንሳኤ ተስፋ የሌለው ዘላለማዊ ሞት ትሞታለች፤ የእግዚአብሔርም ቁጣ በላይዋ ይሆናል፡፡ EWAmh 156.1
«ኃጢአት የሠራች ነፍስ እርሷ ትሞታለች” በማለት እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ትርጓሜኃጢአት የሠራች ነፍስ በዘላለማዊ ሥቃይ ውስጥ ትኖራለች ነው ብሎ ሰይጣን ሰዎች እንዲያምኑት በማድረግ ስኬት በማግኘቱ በእጅጉ ተደንቄ ነበር፡፡ መልአኩ እንዲህ ኣለ «ህይወት—በህመም ወይም በደስታ ውስጥ ቢኮንም ያው ህይወት ነው፡፡ ሞት ግን ያለ ምንም ህመም! ያለምንም ደስታ ወይም ያለምንም ጥላቻ መሆን ነው፡፡» EWAmh 156.2
ሰይጣን በመጀመሪያ ላይ በኤደን ገነት ለሔዋን «መሞት እንኳ አትሞቱም” በሚል የተነገራት ሐሰት በሁሉም ስፍራ እንዲሰራጭ የተለየ ጥ ረት ያደርጉ ዘንድ ለመላእክቱ ነገራቸው፡፡ ሰዎች የቀረበላቸውን ስህተት በመቀበል ሰው አይሞትም ብለው ማመን ሲጀምሩ፧ ሰይጣን ኃጢአተኛው በዘላለማዊ ሥቃይ ይኖራል ወደሚለው አስተሳሰብ መራቸው: ይህ የሰይጣን ድርጊት ስወኪሎቹ ለሚሠራው ሥራ ፈር በመቅደድእግዚአብሔር የማያስደስቱት ሁሉ በገሃነም እየተሰቃዩ ቁጣው ለዘላለም እንዲሰማቸው በዘላለማዊው እሳት ውስጥ እየተንፈራገጡ የሚያደርግ ፣ የማይገልጻቸውን ሥቃይና መከራ ሲቀበሉእነርሱ ቃላት ከላይ ሆኖ በእርካታ ስሜት የሚመለከታቸው፣ በቀለኛና አምባገነን አምላክ ተደርጎ የሚሳልበትን ሞት እንጂ ዘስማዊ ሥቃይ ስስመኖሩ መንገድ አመቻቸ ይህ ማሳቻ ተቀባ3ነት ካገኘ እግዚአብሔር በመወደድና በመፈቀር ፋንታ በብዙዎች እንደሚጠላ ሰይጣን ያውቅ ነበር፡፡ እርሱ በቃሉ ከቀረበው አፍቃሪ ባህሪው በተጻራሪ ፍጡራኑ ከዘላለም እስከ ዘላለም በኃይለኛ እቶን እሳት ውስጥ ሲስቃዩ እንዲኖሩ የሚፈቅድ አምላክ ተደርጎ መስተዋሉI ወዳጃዊ የሆኑት አምላካዊ ቃላት የታለመላቸውን ግብ ሳይመቱ እንደሚስተጓጎሉ ሰይጣን ያውቅ ነበር፡፡ EWAmh 156.3
ሌላው ሰይጣን ሕዝቡን ያሳተበት መንገድ አምላካዊውን ፍትሕና ማስጠንቀቂያ ከማስተዋል እንዲታቀቡ በማድረግ ሲሆን ይኸውም እግዚአብሔር ከመሐሪነቱ የተነሳ ማንንም እንደማያጠፋ[ ነገር ግን ቅዱሱም ሆነ ኃጢአተኛው በመጨረሻ ድነው የመንግሥቱ ወራሾች ይሆናሉ የሚል ነው፡፡ EWAmh 157.1
ነፍስ ፍጻሜ ለሌለው ዘመን በስቃይ ትኖራለች እንጂ አትሞትም የተሰኘው የሰይጣን አስተምህሮ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር መንፈስ እንዳልተጻፈ በመቁጠር ቸል የማለታቸውን ውጤት አስከተለ፡፡ ምንም እንኳ እነዚህ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ ብዙ መልካም ነገሮች እንዳሉት ባይክዱም ነገር ግን ሊተማመኑበትና ሊወዱት አልቻሉም፡፡ ለዚህ መንስዔው ስለ ዘላለማዊ ሥቃይ እንደሚያስተምር ስለተነገራቸው ነው፡፡ EWAmh 157.2
የእግዚአብሔርን ሕልውና መካድ ሌላው ሰይጣን ሰዎችን ለማሳት የተጠቀመበት መንገድ ነው፡፡ እርሱ ሰብዓዊውን ቤተሰብ ፍጻሜ ለሌለው ዘመን ሲያሰቃይ የሚኖር ከሆነ ሰዎች ይህን ከመጽሐፍ ቅዱሳዊው ባህሪው ጋር የሚጋጭ ማንነት ተከትለው ለመጓዝ ይቸገራሉ፡፡ በዚህ የተነሳ መጽሐፍ ቅዱስንም ሆነ የመጽሐፉ ደራሲ የሆነውን አምላክ በመካድ ሞትን እንደ እንቅልፍ ለመመልከት ይመርጣሉ፡፡ ፍርሃትና ድንጋጤ የሚስተዋልባቸው ሌሎች ክፍሎችሞ አሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ኃጢአት እንዲሠሩ በሰይጣን ፈተና ቀርቦላቸው ኃጢአት ከሠሩ በኋላ የኃጢአት ዋጋ ለዘላለም እየተሰቃዩ በህይወት መኖር እንጂ ሞት አለመሆኑን ይነግራቸዋል፡፡ ሰይጣን በዚህ መልኩ ምስኪን በሆነው አእምሮአቸው ፍጻሜ የሌለውን ሥቃይ ግዙፍ አድርጎ በማቅረብ አእምሮአቸውንና መላ የማሰብ ኃይላቸውን ይቆጣጠራል፡፡ EWAmh 157.3
መላው የሰማይ ሰራዊት በዚህ ድፍረት የተሞላው የሰይጣን ሥራ በቅዱስ ቁጣ ተሞልቶ እንደነበር ተመልክቻለሁ፡፡ የእግዚአብሔር መላእክት ኃያል እንደመሆናቸው አምላካዊው ትእዛዝ ቢሰጣቸው የጠላትን ኃይል በቀላሉ ማክሸፍ ሲችሉ ነገር ግን እንዲህ ያለው መጠነ ሰፊ ማታለያ በሰብዓዊው አእምሮ ላይ ይደርስ ዘንድ ለምን እንደተፈቀደ ጠየቅኩ፡፡ ሰይጣን ሰብዓዊውን ፍጡር ለማጥፋት የማይምሰው ጉድጓድ የለም፡፡ ይህን አስቀድሞ ያውቅ የነበረው አምላክ ደካማው ሰው እንኳ እንዳይስ በመጠንቀቅ ቃሉን ግልጽና ሰብዓዊው ዘር ሊያስተውለው በሚችል መልኩ ጽፎ በመስጠት ዓላማውን ማሳወቁን ተመለከትኩ፡፡ እግዚአብሔር ቃሉን ከሰጠ በኋላ በሰይጣን፣ በመላእክቱ ወይም በወኪሎቹ አማካኝነት ጥፋት እንዳይደርስበት በጥንቃቄ ጠብቆ አቆየው፡፡ ብዛት ያላቸው ሌሎች መጽሐፎች ሲጠፉ ነገር ግን አምላካዊው ቃል ህያው ሆኖ ይኖራል፡፡ የሰይጣን ማታለያ መንገዶች እየጨመሩ በሚሄዱበት የምድር ታሪክ መዝጊያ ላይ እያንዳንዱ ሰው hሰይጣን ሊሰነዘር የሚችለውን ማታለያና ተአምራት መለየት ይችል ዘንድ መጽሐፍ ቅዱስ በከፍተኛ ቅጂ ይባዛል፡፡ EWAmh 157.4
የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂ አነስተኛ በነበረበት ዘመን በጊዜው የተማሩ ሰዎች አምላካዊውን ቃል ይበልጥ ግልጽ ያደረጉ እየመሰላቸው ነገር ግን ባህልን ማዕከል ባደረገው የግል አመለካከታቸው ተጽእኖ ሥር የዋለና ግራ የሚያጋባ አድርገው ቢለውጡትም፧ እግዚአብሔር ለመጽሐፍ ቅዱስ የተለየ ጥበቃ አድርጎ እንደነበር ተመልክቻለሁ፡፡ የእግዚአብሔር ቃል በአጠቃላይ ሲታይ ፍጹም ትስስር የተላበሰና አንዱ ክፍል ሌላውን ለመግለጽ የሚያስችል ዝምድና እንዳለው ተመልክቻለሁ፡፡ የእግዚአብሔር ቃል የህይወትን መንገድ ይፋ አድርጎ ያቀረበልን ግልጽና ቀላል በሆነ መንገድ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ይህን የተገለጸ የህይወት መንገድ እንድናስተውል የሚመራንን መንፈስ ቅዱስ ጭምር ሰጥቶናል፡፡ በመሆኑም እውነትን የሚሹ እውነተኞች ሊስቱ አይገባም:: EWAmh 158.1
የእግዚአብሔር መላእክት ሰብዓዊውን ፈቃድ የመቆጣጠር ባህሪ እንደሌ ላቸው ተመልክቻለሁ:: እግዚአብሔር በሰው ፊት ህይወትና ሞት በማስቀመጡ ምርጫው የግለሰቡ ነው፡፡ ምንም እንኳ ብዙዎች ህይወትን ቢመኙም ነገር ግን አሁን ድረስ በሰፊው ጎዳና መመላለስን መርጠዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች እግዚአብሔር ልጁ እንዲሞትላቸው በመስጠት ባሳያቸው ታላቅ ምህረትና ርኅራኄ በመገዛት ፋንታ በመንግሥቱ ላይ ማመጽ መረጡ፡፡ ይህን በከበረ ዋጋ የተገዛ ደኅንነት ለመቀበል የማይመርጡ ሁሉ ቅጣት መቀበላቸው የግድ ቢሆንም ነገር ግን እግዚአብሔር በዘላለማዊ የገሃነም እሳት ውስጥ ሲያሰቃያቸው እንደማይኖር ወይም ሰማይ እንደማይወስዳቸው ተመልክቻለሁ: እነዚህ ሰዎች ንጹሃንና ቅዱሳን በሚኖሩበት ሰማያዊ ስፍራ እንዲኖሩ ቢደረጉ የስቃይ ስፍራ ይሆንባቸዋል፡፡ በመሆኑም እግዚአብሔር እነዚህን ሰዎች እንዳልነበሩ አድርጎ ሙሉ ለሙሉ ያጠፋቸዋል፡፡ በዚህም ፍትሐዊነቱ እውን ይሆናል፡፡ እግዚአብሔር በመጀመሪ ያ ሰውን ከምድር ዐፈር እንደፈጠረው ሁሉ አመጸኛና ቅዱስ ያልሆኑት በሙሉ በእሳት ጠፍተው ዳግመኛ ወደ ምድር አፈርነት ይመለሳሉ፡፡ በዚህ ዙሪያ የሚስተዋለው አምላካዊ ደግነትና ርኅራኄ ሁሉም የእርሱን ባህሪ እንዲያደንቁና ቅዱስ ስሙን እንዲያፈቅሩ እንደሚያደርጋቸው ተመልክቻ ለሁ፡፡ ኃጥአን ከምድር ገጽ ከጠፉ በኋላ መላው የሰማይ ሰራዊት «አሜን!” ይላል፡፡ EWAmh 158.2
የክርስቶስን ስም እንጠራለን እያሉ ነገር ግን እራሱ ሰይጣን በፈጠራቸው ማታለያዎች ላይ ተጣብቀው የሚኖሩ ሰዎችን ሰይጣን በታላቅ አርካታ ይመለከታቸዋል፡፡ የእርሱ ሥራ አዳዲስ ማታለያዎችን መቀየስ እንደመሆኑ በዚህ ዙሪያ የሚኖረው ኃይልና ክህሎት ያለማቋረጥ እየጨመረ ይሄዳል፡፡ ሰይጣን---ተወካዮቹ፣ ጳጳሳቱና ቀሳውስቱ እራሳቸውን ከፍ ከፍ እንዲያደርጉ በመምራትና ሕዝቡን በማወክ በእርሱ የቀረቡትን ማታለያዎች ለመቀበል ፈቃደኛ ያልሆኑትን አምርረው እንዲያሳድዱና እንዲያጠፉ አደረገ፡፡ ውዶቹ የክርስቶስ ተከታዮች እንዲያልፉባቸው የተደረጉት የሥቃይና ህማም ጎዳናዎች እንዴት ብርቱ ናቸው! መላእክት ይህን ሁሉ በታማኝነት መዝግበው ይዘዋል፡፡ ሰይጣንና ክፉ መላእክቱ በምድር ላይ አንድም እውነተኛ ክርስቲያን እንዳይኖር ለማድረግ ሁሉንም ቅዱሳን እንደሚገድሏቸው ሥቃይ ይደርስባቸው የነበሩ ቅዱሳንን ያገለግሉ ለነበሩ መላእክት በመታበይ ነግረዋቸው ነበር፡፡ እምነቱን በይፋ የሚናገር ታማኝ ክርስቲያን ሰይጣንና ክፉ መላእክቱ ሊፈጥሩት በሚችሉት ሥቃይ አደጋ ውስጥ ነበር፡፡ EWAmh 159.1