ቀደምት ጽሑፎች
48—ታላቁ ክህደት
ጣኦት አምላኪያን ክርስቲያኖችን በጭካኔ ሲያሳድዱና ሲገድሉ ወደ ነበ ረበት ቀደም ወዳለው ጊዜ ተወስጄ ነበር፡፡ በዚያን ዘመን ደም እንደ ጎርፍ ፈሰሰ፡፡ ታዋቂው፣ የተማረው እንዲሁም ተራው የሕብረተሰብ ክፍል ሳይቀር ያለ ምህረት ታረደ፡፡ በሐብት ደርጅተው የነበሩ ቤተሰቦች እምነታቸውን አጽንተው በመያዛቸው ምክንያት ለድኅነት ተዳረጉ፡፡ እነዚህ ክርስቲያኖች በሥደትና በሥቃይ ጎዳና እንዲያልፉ ቢደረጉም እነርሱ ግን እውነትን ጠብቀው ይዘው ነበር፡፡ እምነታቸውን ያለ እንከን በንጽህና አቆይተዋል፡፡ ሰይጣን በእነዚህ ሰዎች ሥቃይ ድል አግኝቶ እንደነበር ተመልክቻለሁ: ነገር ግን እግዚአብሔር እነዚህን ታማኝ ሰማዕት በታላቅ ክብር ይመለከታቸው ነበር በዚያ -ስፈሪ ዘመን ይኖሩ የነበሩ ክርስቲያኖች ለጌታ ሲሉ ሥቃይን ለመቀበል ፈቃደኞች ስለነበሩ አብልጠው በእርሱ የተወደዱ ነበሩ፡፡ እነርሱ በጽናት ያልፉት የነበረ ማንኛውም ዓይነት ሥቃይ በሰማይ የነበራቸውን ሽልማት ይጨምረው ነበር EWAmh 149.2
ሰይጣን በቅዱኑ መከራና እንግልት ቢፈነጥዝም እንኳ እርካታ ግን አልነበረውም፡፡ በመሆኑም በአካላቸው ላይ ያገኘውን ዓይነት የበላይነት በአእምሮአቸውም ላይ ለመቀዳጀት ፈለገ፡፡ እነርሱ ያለፉባቸው የሥቃይ ጎዳናዎች አንዱ ሌላውን እንዲወድ በማድረግና እግዚአብሔርን እንዲፈሩ በመርዳት ይበልጥ ወደ ጌታ አቀረባቸው እንጂ ሌላ የፈየዱት አንዳችም ነገር አልነበረም:: እነዚህ ሰዎች በእግዚአብሔር ላይ ያላቸውን ብርታት፣ በእርሱ መከታነት መተማመናቸውንና ጽኑ እምነታቸውን እንዲያጡ በማሴር እግዚአብሔርን እንዲያሳዝኑት ለማድረግ ተመኘ: ምንም እንኳ በሺህ የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች ቢታረዱም ነገር ግን ሌሎቹ የእነርሱን ስፍራ ለመሙላት ወደፊት ይጓዙ ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች ሥቃይና ሞት ቢደርስባቸውም ነገር ግን በየሱስ ክርስቶስ ጥላ ስር በመዋል የመንግሥቱ ባለቤት በመሆናቸው ሰይጣን እያጣቸው መሆኑን ተመለከተ፡፡ በመሆኑም ሰይጣን ከቀድሞው ይበልጥ ስኬታማ በሆነ መልኩ ከእግዚአብሔር መንግሥተጋር በመዋጋት ቤተክርስቲያንን ለመገርሰስ ያስችለኛል ያለውን እቅድ ነደፈ:: ጣኦት አምላኪዎች ከክርስትና እምነት ውስጥ የተወሰኑ ክፍሎችን የእምነታች አካል አካል አድርገው እንዲይዙ በመምራት ልባቸው ሳይለወጥ በክርስቶስ ስቅለትና ትንሳኤ አምነው ከየሱስ ተከታይ ክርስቲያኖች ጋር አንድነት እንዲፈጥሩ አደረጋቸው:: ይህ አካሄድ በቤተክርስቲያን ላይ አስፈሪ አደጋ የሚጋርጥ እንደመሆኑ ወቅቱ አእምሮ ላይ ብርቱ ህመም የሚፈጥር ነበር አንዳንዶች ከነበሩበት ንጽህና ቁልቁል ወርደው መጠነኛ የክርስትና እምነት ከያዙ ጣኦት አምላኪዎች ጋር አንድነት መፍጠራቸው ምናልባትም hነርሱን ሙሉ ለሙሉ ወደ እውነት ለማምጣት የሚያስችል ዕድል ይከፍታል ብለው አስበው ነበር ሰይጣን መጽሐፍ ቅዱሳዊውን አስተምህሮ ከሐሰት ጋር ለመቀላቀል እየተመኘ ነበር EWAmh 149.3
የቀድሞው ንጽህና ወርዶና ጣኦት አምላኪያን ከክርስቲያኖች ጋር አንድነት ፈጥረው ተመለከትኩ፡፡ ምንም እንኳ እነዚህ ጣኦት አምላኪያን እንደተለወጡ ቢናገሩም ነገር ግን ጣኦቶቻቸውን ከእነርሱ ጋር ወደ ቤተክርስቲያን ይዘው በመምጣት ቀድሞ ያመልኳቸው የነበሩ አማልክቶችን ምስልን አሁን--በቅዱሳን፣ በክርስቶስና በእናቱ በማርያም ሥዕል ተኳቸው፡፡ የክርስቶስ ተከታዮች ቀስ በቀስ ከእነርሱ ጋር አንድነት እየፈጠሩ በሄዱ ቁጥር ቤተክርስቲያን የነበራትን ንጽህናና ኃይል አያጣች መጣች:: አንዳንዶች የነበራቸውን ንጽህና ጠብቀው በመጓዝና እግዚአብሔርን ብቻ በማምለክ ከእነርሱ ጋር አንድነት ለመፍጠር ተቃውመው ነበር፡፡ እነዚህ ክርስቲያኖች ለሥዕልም ሆነ ለማንኛውም በላይ በሰማይ ወይም በታች በምድር ላለው አጎንብሰው አይሰግዱም ነበር፡፡ EWAmh 150.1
በብዙዎች ውድቀት የተነሳ የከበረው ሰይጣን ለሥዕልና ምሳሌ ሳይሰግዱ እምነታቸውን በንጽህና ጠብቀው የያዙትን እንደ ጠላት በመቁጠር ለሥዕልና ምሳሌ እንዲሰግዱ ወይም እንዲገደሉ ይህች የወደቀችው ቤተክርስቲያን በእነርሱ ላይ እንድትነሳሳ አመሳት የስደት እሳት በእውነተኛ የክርስቶስ ተከታዮች ላይ ዳግመኛ በመነሳሳቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ያለ ምህረት ተጨፈጨፉ፡፡ EWAmh 150.2
ሁኔታውን እንደሚከተለው ተመልክቼ ነበር፡፡- ከፍተኛ ቁጥር የነበራቸው ጣኦት አምላኪያን በላዩ ላይ የጸሐይ የጨረቃና የከዋክብት ምስል ያለበትን ጥቁር ሰንደቅ አንግበው ነበር፡፡ ቡድኑ በጣም ጸንፈኛና ቁጡ ይመስላል:: በዚሁ ጊዜ ንጹህ እና ነጭ በላ ላይ «ለጌታ--ንጹህና ቅዱስ መሆን” ‘ሚል የተጻፈበትን ሰንደቅ ያነገቡ ሌሎች ቡድኖችን ተመለከትኩ፡፡ በእነዚህ ሕዝቦች ገጽታ ላይ ጽናትና ሰማያዊ ተቀባይነት ይነበብ ነበር፡፡ ጣኦት አምላኪያኑ ወደ እነርሱ በመቅረብ ከፍተኛ ጭፍጨፋ በማካሄዳቸው ክርስቲያኖች በፊታቸው ቀልጠው ቢወድቁም ነገር ግን ሁናቴው ይበልጥ እንዲቀራረቡና ስንደቁን በበለጠ ጽናት እንዲይዙት መንስዔ ሆኗቸው ነበር፡፡ ብዙዎች በወደቁ ቁጥር ሌሎች በሰንደቁ ዙሪያ በመሆን ክፍተቶቹን ይሞሉ ነበር EWAmh 150.3
በአንድነት ሆነው ይመክሩ የነበሩ የጣኦት አምላኪያንን ሰብስብ ተመልክቼ ነበር፡፡ በክርስቲያኖች ላይ ያሰቡትን ውጤት ማምጣት ባለመቻ ላቸው ሌላ ሃሳብ ለማመንጨት ተስማምተው ነበር፡፡ ስብስቡ የያዘውን ሰንደቅ ዝቅ በማድረግ ጽኑ የክርስቲያን ቡድኖች ያመነጩትን ሃሳብ እንዲቀበሏቸው ያግባቧቸው ነበር፡፡ በመጀመሪያ ላይ ያቀረቧቸው ሃሳቦች ሙሉ ለሙሉ ተቀባይነት ሳያገኙ ቀርተው ነበር፡፡ በመቀጠል በአንድ ላይ ሆነው የሚመክሩ ክርስቲያኖችን ተመለከትኩ፡፡ አንዳንዶች (ንደቃቸውን ዝቅ አድርገው የቀረቡትን ሃሳቦች በመቀበል ህይወታቸውን ካዳኑ በኋላ በመጨረሻ ሰንደቃቸውን በጣኦት አምላኪያኑ ላይ ከፍ ለማድረግ ብርታት ማግኘት እንደሚችሉ ይናገሩ ነበር፡፡ ነገር ግን ከመካከላቸው ጥቂቶቹ በቀረበው ሃሳብ ባለመስማማት ሰንደቃቸውን ዝቅ በማድረግ ፋንታ ከፍ እንዳረጉ መሞት እንደሚመርጡ አጽንኦት ሰጥተው ይናገሩ ነበር፡፡ ከዚያም ብዙዎች ስንደቃቸውን ዝቅ አድርገው ከጣኦት አምላኪዎቹ ጋር አንድነት ሲፈጥሩ ጽኑና ብርቱዎቹ ግን ሰንደቁን እንደገና በመያዝ ከፍ ሲያደርጉት ተመለከትኩ፡፡ ከንጹሑ ሰንደቅ ስር እየፈለሱ ወደ ጣኦት አምላኪያኑ ጥቁር ሰንደቅ ያለማቋረጥ በመቀላቀል ባለ ነጭ ሰንደቆቹን ሚያሳድዱ ብዙዎችን ተመለከትኩ፡፡ ብዙዎች ቢታረዱም ነገር ግን ነጩ (ንደቅ ከፍ እንዳለና አማኞችም በስሩ እንደተሰባቡ ነበር፡፡ EWAmh 151.1
ጣኦት አምላኪዎችን በመጀመሪያ በየሱስ ላይ አነሳስተው የነበሩ አይሁድ ከቅጣት አያመልጡም:: ጲላጦስ በየሱስ ላይ ለመፍረድ ባመነታ ጊዜ በፍርድ ሸንጎው ውስጥ በቁጣ የተሞሉ አይሁዳውያን «ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን” እያሉ ጮኹ፡፡ ይህ በልጆቻቸው ላይ እንዲደርስ የጠሩት አስፈሪ እርግማን በሕዝበ አይሁድ ላይ ደረሰ፡፡ ጣኦት አምላኪያኑም ሆኑ ከእነርሱ ጋር አንድነት የፈጠሩት ክርስቲያን ነን የሚሉ ሁሉ ጠላቶቻ ቸው ሆኑ፡፡ እነዚሁ ክርስቲያኖች አይሁዳውያኑ በሰቀሉት ክርስቶስ ላይ ካላቸው ቅንአት የተነሳ ሲናገሩ---አይሁዳውያኑ የላቀ ሥቃይ በላይቸው እንዲመጣ ባደረጉ ቁጥር እግዚአብሔር አብልጦ ይደሰታል፡፡ በዚህ ምክንያት ብዙዎች የማያምኑ አይሁዶች ሲገደሉ ሌሎች ደግሞ ከቦታ ወደ ቦታ በመንከራተት በእያንዳንዱ የህይወታቸው ገጽታ ቅጣት ተቀብለዋል፡፡ EWAmh 151.2
የክርስቶስና የገደሏቸው ደቀ መዛሙርት ደም በላያቸው ስለነበር አስፈሪ ፍርድ እንዲጎበኛቸው ሆኑ፡፡ አምላካዊው እርግማን ስለተከተላቸው በጣኦት አምላኪያኑና ክርስቲያን ተብለው በተጠሩት ፊት ጥሩ የመላገጫ ተምሳሌት ሆኑ፡፡ የቃየን ምልክት በላያቸው ያለ ያህል ተዋረዱ፣ ተነቀፉ እንዲሁም ተጠሉ፡፡ የእነዚህ ሕዝቦች በአምላካዊው እርግማን በተለይ መጎብኘት በጉልህ ይታይ ዘንድ እግዚአብሔር እነዚህን ሕዝቦች በመላው ምድር በመዝራት እንዳይጠፉ በአስደናቂ ሁኔታ ጠበቃቸው፡፡ እግዚአብሔር አይሁዶችን እንደ ሕዝብ መመልከቱን የተወ መሆኑን የተመለከትኩ ሲሆን ነገር ግን ግለሰቦች በልባቸው ያለውን መጋረጃ ቀድደው ትንቢቱ መፈጸሙን በመመልከት ከተለወጡ የሱስን እንደ ዓለም አዳኝ አድርገው እንደሚቀበሉና ሕዝባቸው እርሱን በመቃወምና በመስቀል የሠራውን ታላቅ ኃጢአት እንደሚመለከቱ አይቻለሁ፡፡ EWAmh 152.1