ቀደምት ጽሑፎች
46—አይሁድ ጳውሎስን ለመግደል መወሰናቸው
የካኅናት አለቆችና ገዢዎች የጳውሎስ ተሞክሮ ያስከተለውን ውጤት በተመለከቱ ጊዜ በእርሱ ላይ የመረረ ጥላቻ አሳዩ፡፡ ጳውሎስ በድፍረት በየሰስ ስም በመስበኩና በስሙ ተአምራት በማድረጉ ብዛት ያለው ሕዝብ ፊቱን ከወግና ልማድ እየመለሰ፤ እርሱን በማድመጥ የአይሁድ ኃይማኖት መሪዎች የየሱስ ገዳዮች እንደሆነ መመልከት መጀመራቸውን አስተዋሉ፡፡ መሪዎቹ ቁጣቸው ገንፍሎ በዙሪያቸው እየተስተዋለ ያለውን ከፍ ያለ የሕዝብ ስሜት ለማረጋጋት ምን ማድረግ እንዳለባቸው ለመምከር ተሰበሰቡ፡፡ በስብሰባቸው እንደ ብቸኛ አማራጭ ያገኙት ጳውሎስን መግደል ስለነበር በዚሁ ተስማሙ፡፡ ሆኖም ጳውሎስ ተልዕኮውን ከግብ እስኪያደርስ መኖር ስለነበረበት እርሱን ይጠብቀው ዘንድ እግዚአብሔር መልአክ ላከ፡፡ EWAmh 143.2
በሰይጣን የሚመሩት አማኝ ያልሆኑ አይሁዶች ጳውሎስ ከደማስቆ ሲወጣ ሊገድሉት የከተማዋን በር ቀንና ሌት መጠበቃቸውን ተያያዙት፡፡ ነገር ግን አይሁድ ህይወቱን እንደሚሹ ጳውሎስ አውቆ ስለነበር የእርሱ ተከታዮች በሌሊት በከተማዋ ቅጥር ቀዳዳ አሹልከው በቅርጫት አወረዱት፡፡ በዚህ መልኩ አይሁድ ያቀዱትን መተግበር ባለመቻላቸው አፈሩ፤ ንዴትም ያዛቸው: የሰይጣን ዓላማም ተሰናከለ፡፡ EWAmh 143.3
ከዚህ በኋላ ጳውሎስ አራሱን በየሩሳሌም ካሉ ደቀ መዝሙሮች ጋር ለማቀላቀል ወደዚያው ቢያመራም እነርሱ ግን በእርግጥ ደቀ መዝሙር መሆኑን ስላላመኑ ሁሉም ፈሩት፡፡ ጳውሎስ በደማስቆ በአይሁድ ሲታደን ነበር አሁን ደግሞ የገዛ ወንድሞቹ የሚቀበሉት ዓይነት አልሆኑም፡፡ ሆኖም በርናባስ ጳውሎስን ወደ ሐዋርያተበማምጣት በደማስቆ ጉዞው ጌታን Åንዴት እንዳየው፤ ጌታም እንዴት እንደተናገረው እንዲሁም በደማስቆ የጌታን ስም እንዴት በድፍረት እንደሰበከ ነገራቸው፡፡ EWAmh 143.4
ነገር ግን አይሁድ ጳውሎስን ያጠፉት ዘንድ ሰይጣን ያምሳቸው ስለነበር የሩሳሌምን ለቅቆ እንዲወጣ ጌታ ተናገረው፡፡ ጳውሎስ ከበርናባስ ጋር አብሮ በመሆን የሱስን እየሰበከና ተአምራት እያደረገ ወደ ሌሎችም ከተሞች ባደ ረገው ጉዞ ብዙዎች ተለወጡ፡፡ ጳውሎስ እግሩ አንካሳ የነበረና ከተወለደ ጀምሮ ፈጽሞ በእግሩ ሄዶ የማያውቅን ሽባ ሰው ሲፈውስ ጣኦት አምላኪ የነበረው ሕዝብ በተመለከተጊዜ እንደ አማልክት በመቁጠር መስዋዕት ሊሰውላቸው ፈለጉ፡፡ ጳውሎስ በሁኔታው በእጅጉ በማዘን እርሱና አብሮት ያለው አገልጋይ ሰዎች መሆናቸውን በመንገር ሰማይንና ምድርን፣ ባህርንም በውስጣውም የሚኖሩትን ሁሉ የፈጠረ ብቻ ሊመለክ እንደሚገባው ነገራቸው፡፡ ጳውሎስ እግዚአብሔርን በፊታቸው ከፍ ከፍ ቢያደርግም ነገር ግን ሕዝቡ እንዳይሰዋላቸው ያስተወው በብዙ ችግር ነበር ጳውሎስ በመልእክቱ ስለ እወነተኛው አምላክ ማንነት፣ እርሱን ስለ ማምለክና ለእርሱ ክብር ስለ መስጠት ሲናገርና ሕዝቡም ሲያደምጠው፤ ነገር ግን ሰይጣን አማኝ ያልሆኑ የሌሎች ከተሞች አይሁዶች ተከታትለው የእርሱን መልካም ሥራ እንዲያጠፉ አነሳሳ፡፡ እነዚህ አይሁዶች የጣኦት አምላኪዎቹን አእምሮ በማመስ ስለ ጳውሎስ ሐሰተኛ መረጃዎችን አቀረቡላቸው:: በዚህን ጊዜ በጳውሎስ ሥራ ተደንቀው አድናቆታቸውን ሲቸሩ የነበሩ ሕዝቦች ስሜት አሁን ወደ ጥላቻ በመለወጡ ከጥቂት ጊዜያት በፊት ደቀ መዛሙርቱን ለማምለክ ዝግጁ እንዳልነበሩ ሁሉ ጳውሎስን በድንጋይ ከወገሩት በኋላ የሞተመስሎአቸው ጎትተው ከከተማው ወደ ውጭ አወጡት፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ለማልቀስ ከበውት እያሉ በመነሳቱ ልባቸው ደስ ተሰኝቶ አብሯቸው ወደ ከተማ ገባ፡፡ EWAmh 144.1
አሁንም ጳውሎስና ሲላስ የሱስን እየሰበኩ አንዲት በጥንቆላ መንፈስ የምትናገር ሴት ‹‹እነዚህ ሰዎች የመዳንን መንገድ የሚነግሯችሁ የልዑል እግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸው” በማለት ለብዙ ቀን እየጮኸች ደቀ መዛሙርቱን ትከተል ነበር፡፡ ጳውሎስ በሴትየዋ ሁኔታ ታውኮአል:: ይህች ሴት እየተከተለቻቸው መጮኋ የሰዉ አእምሮ ከእውነት እንዲርቅ አደ ረገው፡፡ ሰይጣን ይህችን ሴት የተጠቀመበት ዓላማ ሕዝቡን ለማስጠየፍና የደቀ መዛሙርቱን ተጽእኖ ለማጥፋት ነበር፡፡ ጳውሎስ ውስጡ በመታወኩ «ዘወር ብሎ ያን መንፈስ ከእርሷ እንድትወጣ በጌታ በየሱስ ክርስቶስ ስም አዝሃለሁ! አለው” የተገሰጸውም ክፉ መንፈስ ወዲያው ለቅቋት ሄደ፡፡ EWAmh 144.2
ሴቲቱ ደቀ መዛሙርቱን እየተከታተለች በመጮኋ አሳዳሪዎቿ ደስተኞች ነበሩ፡፡ ነገር ግን ክፉው መንፈስ ጥሏት ሄዶና እርሷም ትሁት የክርስቶስ ደቀ መዝሙር ሆና ሲመለከቷት ተቆጡ: ከዚህ በፊት በእርሷ የጥንቆላ ሥራ አሳዳሪዎቿ ብዙ ገንዘብ መሰብሰብ ችለው ነበር፡፡ አሁን ግን ያ የገንዘብ ማግኛ ተስፋቸው ሄደ፡፡ የሰይጣን ዓላማ ቢከሽፍም ነገር ግን የእርሱ አገልጋዮች ጳውሎስንና ሲላስን ይዘው እየጎተቱ ባለ ሥልጣኖች ወዳሉበት ወደ ገበያ ቦታ በማምጣት ‹‹እነዚህ ሰዎች አይሁድ ሆነው ሳሉ ከተማችንን አውከዋል” በማለት ከሰሷቸው፡፡ ሕዝቡም ተባብረው በጳውሎስና በሲላስ ላይ ተነሳሱባቸው ገዦቹም ልብሳቸው ተገፍፎ በበትር እንዲደበደቡ አዘዙ:፡፡ ክፉኛ ከደበደቧቸውም በኋላ ወደ ወህኒ ቤት አስገቧቸው፤ የወህኒ ቤ ት ጠባቂውም ተጠንቅቆ እንዲጠብቃቸው ኣዘዙት እርሱም ይህን የመሰለ ትእዛዝ ከተቀበለ በኋላ ወደ ወህኒ ቤቱ ውስጠኛ ክፍል አስገብቶ እግራቸውን ከግንድ ጋር አጣብቆ አሰረው፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔር መልአክ እነርሱ ወደነበሩበት የውስጠኛው ክፍል አብሮአቸው በመሆን እስራታቸው ለእግዚአብሔር ክብር እንዲውል አደረገ፡፡ እግዚአብሔር ከተመረጡ አገልጋዮቹ ጋር በሥራ ላይ እንደነበርም ለሕዝቡ አሳየ፡፡ EWAmh 144.3
እኩለ ሌሊት አካባቢ ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩና እየዘመሩ እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ ነበር፡፡ ድንገትም የወህኒ ቤቱን መሰረት የሚያናውጥ ታላቅ የመሬት መንቀጥቀጥ ሆነ፡፡ ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መልአክ የእያንዳንዱን እስራት ሲፈታ ተመለከትኩ፡፡ የወህኒ ቤቱም ጠባቂ ከእንቅልፉ ነቅቶ የወህኒ ቤቱ በሮች ተከፍተው ባየ ጊዜ ደነገጠ፡፡ እስረኞቹ እንዳመለጡ በማሰብ እራሱን በማጥፋት ቅጣቱን መቀበሉ የግድ እንደሆነ ወሰነ፡፡ ነገር ግን እራሱን ሊገድል ሲል ጳውሎስ ድምጹን ከፍ አድርጎ «እኛ ሁላችን እዚሁ ስላለን በራስህ ላይ ክፉ ነገር አታድርስ!» በማለት ጮኸ፡፡ EWAmh 145.1
አምላካዊው ኃይል የእስር ቤቱን ጠባቂ ተገናኘው፡፡ ጠባቂው መብራት ለምኖ ወደ ውስጥ ከገባ በኋላ ተንቀጥቅጦ በጳውሎስና ሲላስ እግር ላይ ወደቀ ይዞአቸውም ከወጣ በኋላ «እናንት ሰዎች እድን ዘንድ ምን ላድርግ?” አላቸው፡፡ እነርሱም «በጌታ በየሱስ እመን አንተም ቤተሰዎችህም ትድናላችሁ» በማለት መለሱለት፡፡ ከዚያም የእስር ቤቱ ጠባቂ ቤተሰቡን በሙሉ ከሰበሰበ በኋላ ጳውሎስ የሱስን ሰበከላቸው፡፡ በዚህም የእስር ቤቱ ጠባቂ ልብ ከወንድሞች ጋር ሐብረት በመፍጠር ቁስላቸውን አጠበላቸው ወዲያውም እርሱና ቤተሰቡ ሁሉ ተጠመቁ፡፡ ማዕድ አቀረበላቸው፤ ከቤተሰቡም ሁሉ ጋር በእግዚአብሔር በማመኑ በደስታ ተሞላ፡፡ EWAmh 145.2
አስደናቂው የእግዚአብሔር ኃይል የወህኒ ቤቱን በሮች በመክፈት መገለጡና የጠባቂውና የቤተሰቡ መለወጥ ወሬ ወዲያውኑ በአካባቢው ሁሉ ተዛመተ፡፡ ጉዳዩን የሰሙት ገዢዎች ሁኔታው ስላስፈራቸው የወህኒ ቤ ቱ ጠባቂ ጳውሎስንና ሲላስን እንዲለቃቸው ትእዛዝ ሰጡት፡፡ ነገር ግን ጳውሎስ የእግዚብሔር ኃይል መገለጥ ተሸፋፍኖ እንዲቀር ባለመፈለጉ በስውር ወህኒ ቤቱን መልቀቅ ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ በመሆኑም እንዲህ አላቸው «እኛ የሮም ዜጎች ሆነን ሳለን በሕዝብ ፊት ያለ ፍርድ ደብድበው ወደ እስር ቤት ወረወሩን፤ ታዲያ አሁን በስውር ሊያስወጡን ይፈልጋሉ? ይህማ አይሆንም፤ እነርሱ እራሳቸው መጥተው ያስወጡን! አላቸው፡፡» መኮንኖቹ እዚህን ቃላት ለገዢዎቹ ሲነገሯቸውና ጳውሎስና ሲላስ የሮም ዜ ግነት እንዳላቸው ደነገጡ፡፡ እነርሱ ራሳቸው መጥተው ይቅርታ ጠይቀው ከወህኒ ቤቱ አስወጧቸው፡፡ ከተማውንም ለቅቀው እንዴሄዱ ለመኗቸው፡፡ EWAmh 145.3