ቀደምት ጽሑፎች

39/73

38—በክርስቶስ ላይ የተፈጸመው ክህደት

የሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር የጌታ እራት ይበላ ወደነበረበት ጊዜ ተ ወሰድኩ፡፡ ከክርስቶስ ደቀ መዛሙርት መሃል ይሁዳ እውነተኛው እንደሆነ አድርጎ እንዲያስብ (ይጣን አታሎታል፡፡ ነገር ግን የእርሱ ልብ ምንጊዜም ሥጋዊ ነበር፡፡ ይሁዳ አስደናቂዎቹን የየሱስ ሥራዎች ተመልክቶአል፣ በአገልግሎቱ ወቅት በነበረው አብሮነት የሱስ መሲህ መሆኑን የሚየሳዩ ጠንካራ መረጃዎችን አይቶhል፡፡ ነገር ግን የተዘጋና ድብቅ የነበረው ይሁዳ ገንዘብ ወዳ ነበር፡፡ ማሪያም በየሱስ ላይ ያፈሰስችው ውድ ሽቶ ተሸጦ ለምንድን ነው ገንዘቡ ለድኾች የማይመጸወተው በማለት በቁጣ ተናግሮ ነበር፡፡ ማርያም ጌታዋን ትወድ ነበር፡፡ እርሱ በዛት ያለውን ኃጢአቷን ይቅር ብሎአልº በእጅጉ የምትወደውን ወንድሟን ከሞት አስነስቷል: በዚህ የተነሳ ለየሱስ የምታደርገው ማንኛወም የከበረ ነገር ያንስ እንደሆን እንጂ ሊበዛበት አይችልም:: በእርሱ ላይ ያፈሰሰችው ዘይት እጅግ ወድ በሆነ መጠን፤ ለአዳኘ ያላትን ምስጋና በተሻለ መግለጽ ያስችላታል፡፡ ይሁዳ በውስጡ የነበረውን ስስት መሸፈኛ ዘዴ በመፈለግ ሽቶው ተሸጦ ገንዘቡ ለድኾች መዋል ይችል እንደነበር በአጽንኦት ለመናገር ሞከረ፡፡ ነገር ግን እርሱ ለድኾች ፈጽሞ ደንታ ያልነበረው እንደመሆኑ ጉዳዩ እንደሚለው አልነበረም ምክንያቱም ይሁዳ እራስ ወዳድ በመሆኑ ብዙውን ጊዜ ለድኾች እንዲሰጥ በአደራ የተረከበውን ለግል ጥቅሙ ያውለው ነበር ይሁዳ ለየሱስ ምቾትም ሆነ ፍላጎት ደንታ የማይሰጠው ሰው ስለነበር ብዙውን ጊዜ ለግል ጥቅሙ ለሚያውላቸው ነገሮች እንደ ከለላ ይጠቀም የነበረው ድኾችን ነው:፡፡ ይህ የማሪያም ለጋስነት የእርሱን እራስ ወዳድ ተፈጥሮ አብልጦ የሚገስጽ ድርጊት ነበር:: EWAmh 113.3

የአይሁድ ቀሳውስትና የኃይማኖት መሪዎች የሱስን ቢጠሉትም ሕዝቡ ግን ከየሱስ አንደበት ለሚወጡት የጥበብ ቃላትና ለአስደናቂ ሥራዎቹ ምስክር በመሆን በብዙ ግፊያና መጨናነቅ ያደምጡት ነበር፡፡ ከመሪዎቹ አብዛኞቹ በየሱስ አምነው የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ምስክርነታቸውን ቢሰጡ ቢያንስ ከአይሁድ ቤተአምልኮ ሊባረሩ እንደሚችሉ በመሥጋታቸው ደፍ ረው መውጣት አልቻሉም፡፡ የሕዝቡን አትኩሮት ከየሱስ ለመሳብ አንድ ነገር መደረግ እንዳለበት ቀሳውስቱና መሪዎቹ ከውሳኔ ደረሱ መሪዎቹ ሰው ሁሉ ግልብጥ ብሎ እርሱን ወደ ማመን ይሄዳል የሚል ፍራቻ ገብቷቸው ስለ ነበር ለራሳቸው ደኅንነት አስተማማኝ ያሉትን አንዳችም ነገር መመልከት አልቻሉም በመሆኑም ሥልጣናቸውን መልቀቅ ወይም የሱስን መግደል ነበረባቸው፡፡ ደግሞም እርሱን ከገደሉ በኋላም እንኳ የእርሱ ኃይል ቅርስ የሆኑ ሕያዋን ሊኖሩ ነው:፡፡ የሱስ አልአዛርን ከሞት አስነስቷል፤ በመሆኑም እነርሱ የሱስን ቢገድሉ አልአዛር የርሱን ገናናነት ሊመሰክር ነው፡፡ ሕዝቡ ከሞት የተነሳውን ሰው ለመመልከት ይተም ነበር፡፡ መሪዎቹ አልአዛርን ጭምር በመግደል የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ ቆረጡ፡፡ ይህን ካደረጉ በኋላ ሕዝቡን ወደ ሰው ባህልና አስተምህሮ በመመለስ ከአዝሙድና ከጤና አዳም አስራት እንዲያወጡ እያደረጉ ዳግመኛ በእነርሱ ላይ ተጽእኖአቸውን ማሳደራቸውን ይቀጥላሉ፡፡ የሱስን ከሕዝብ መሃል ለመውሰድ ቢሞክሩ ስው ሁሉ በእርሱ አስተምህሮ በመመሰጡ በድንጋይ ሊወግራቸው እንደሚችል በመፍራት ብቻውን የሚሆንበትን ጊዜ መርጠው ሊይዙት ተስማሙ፡፡ EWAmh 114.1

ቀሳውስቱና የቀሳውስቱ አለቆች የሱስን ለመያዝ ምን ያህል ጉጉት እንደነበራቸው የተረዳው ይሁዳ ጥቂት ገንዘብ በመቀበል የሱስን አሳልፎ ለመስጠት ወሰነ፡፡ ይሁዳ ለገንዘብ የነበረው ፍቅር የሱስን በብርቱ ጠላቶቹ እጅ አሳልፎ እንዲሰጠው አደረገው፡፡ በዚህን ወቅት ሰይጣን በይሁዳ በኩል በቀጥታ እየሠራ ነበር አስደሳችና ማራኪ በነበረው በጌታ ራት ሥነ ሥርዓት አጋማሽ ላይ ከዳተኛው ጌታውን አሳልፎ የሚሰጥባቸውን ዘዴዎች ያውጠነጥን ጀመር፡፡ የሱስ ኃዘን በተሞላው አኳኋን «ሁላችሁም በዚህች ሌ ሊት በእኔ ትሰናከላላችሁ» በማለት ለደቀ መዛሙርቱ ነገራቸው:፡፡ ነገር ግን ጴጥሮስ ጥልቅ በሆነ ስሜት «ሌሎች በሙሉ በአንተምክንያት ቢሰናከሉ እንኳ እኔ በፍጹም አልሰናከልም!» አለው:፡፡ የሱስ ጴጥሮስን እንዲህ አለው «ስምዖን ስምዖን ሆይ፧ እነሆ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተጸለይሁ፤ አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አበርታ» (ሉቃ. 22:31-32): EWAmh 115.1

የሱስን ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በጌተሰማኔ ተመለከትኩት፡፡ የሱስ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ፈተና እንዳይገቡ ተግተው እንዲጸልዩና እንዲጠባበቁ ጥልቅ በሆነ ኃዘን ነገራቸው፡፡ እምነታቸው ሊፈተንና ተስፋቸው አደጋ ሊገጥመው እንደሆነ አውቆአል፡፡ በመሆም ብርታትና ጥንካሬ ማግኘት የሚችሉት ተግተው በመጸለየና ያለውን ሁናቴ በንቃት በመከታተል ነው፡፡ በብዙ ለቅሶና ማንባት «አባት ሆይ ፈቃድህ ከሆነ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፧ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ ሳይሆን የአንተፈቃድ ይፈጸም» በማለት በታላቅ ህማም የእግዚአብሔር ልጅ ጸለየ፡፡ ታላላቅ የደም ነጠብጣብ በፊቱ ላይ በመታየት ወደምድር ይፈስ ነበር፡፡ መላእክት በስፍራው በመገኘት ሁናቴውን በአንክሮ ቢመለከቱም ነገር ግን ከመካከላቸው አንዱ ብቻ የእግዚአብሔርን ልጅ ከህማሙ ያበረታው ዘንድ ወደ እርሱ ተልኮ ነበር፡፡ በወቅቱ በሰማይ ደስታ አልነበረም፡፡ የሰማይ መላእክት አክሊሎቻቸውንና በገናዎቻቸውን ጥለው ጥልቅ በሆነ ስሜት የሱስን በጸጥታ ይመለከቱ ነበር፡፡ እነዚህ መላእክት በእግዚአብሔር ልጅ ላይ የደረሰውን ክህደት ሲመለከቱ ሊከቡት ቢመኙም ነገር ግን አዛዥ መላእክተበእንዲህ ለው ድርጊት ውስጥ ያልፉ ዘንድ አልፈቀዱላቸውም:: ምክንያቱም የደረሰበትን ክህደት ሲመለከቱ ቢያንስ ሊያድኑት ቢገባም ነገር ግን የተዘረጋው ዘላለማዊ ዕቅድ በታቀደው መሰረት ክንውን ማግኘት ነበረበት፡፡ EWAmh 115.2

የሱስ ከጸለየ በኋላ ወደ ደቀ መመርቱ ሲመጣ ተኝተው አገኛቸው፡፡ በዚያ አስፈሪ ሰዓት የደቀ መዛሙርቱ ማጽናናትና ጸሎት እንኳ አልተቸረውም ነበር፡፡ ከጥቂት ጊዜያት ቀደም ብሎ የጋለ ፍላጎት ይታይበት የነበረው ጴጥሮስም እንዲሁ በከባድ እንቅልፍ ወድቆ ነበር፡፡ የሱስ ጴጥሮስ ተናግሮአቸው የነበሩትን አዎንታዊ ቃላት እያስታወሰው «ከእኔ ጋር ለአንድ ሰዓት እንኳ ተግተህ መጠባበቅ አትችልም?» አለው፡፡ የእግዚኣብሔር ልጅ ሦስት ጊዜ ያህል በከባድ ህመም ጸለየ ከዚያም ይሁዳ ከታጠቁ ጭፍራዎች ጋር በመሆን የሱስ ወዳለበት ስፍራ ብቅ hለ፡፡ ይሁዳ እንደተለመደው ጌታ ሆይ ብሎ ጠራውና ሰላምታ ሰጠው፡፡ ጭፍሮቹ የሱስን ሲከቡት መለኮታዊ ኃይሉን ገልጦ አሳየ፡፡ «የምትፈልጉት ማንን ነው?” ብሎ ከጠየቃቸው በኋላ «እርሱ እኔ ነኝ» ባለጊዜ ወደ ኋላ አፈግፍገው መሬት ላይ ወደቁ፡፡ የሱስ ኃይል እንዳለው ምስክር እንዲሆኑና ቢፈልግ ኖሮ እራሱን ከእነርሱ እጅ ማዳን ይችል እንደነበር በተጨባጭ ለማሳየት ጥያቄውን አቀረበ፡፡ EWAmh 115.3

ጭፍሮቹ ሠይፍና ቆመጥ ይዘው የእግዚአብሔርን ልጅ በፍጥነት ሲከቡት ከተመለከቱት ደቀ መዛሙርት መሃል ሠይፍ ይዞ የነበረው ጴጥሮስ ሠይፉን መዞ የሊቀ ካኅናቱን አገልጋይ ጆሮ ቆረጠ፡፡ የሱስ ጴጥሮስ ሠይፉን ወደ ሰገባው አንዲመልስ በመንገር «ካስፈለገ አባቴን ብጠይቀው ከዐሥራ ሁለት ክፍለ ሠራዊት የሚበልጡ መላእክት የማይሰድልኝ ይመስልሃል?” አለው፡፡ እነዚህ ቃላት ሲነገሩ የመላእክቱ ገጽታ በተስፋ በመሞላት አዛዣቸውን ከብበው ያንን በቁጣ የተሞላ ጭፍራ ለመበተን ተመኙ፡፡ ነገር ግን የሱስ በመቀጠል «ይህ ቢሆን ኖሮ ቅዱሳት መጻሕፍት ይሆናል ያሉት ነገር እንዴት ይፈጸማል” ብሎ በተናገረ ጊዜ ዳግመኛ የሐዘን ጥላ አጠላባቸው፡፡ የሱስ በጠላቶቹ እጅ እንዲወድቅ ሲፈቅድ የተመለከቱት ደቀ መዛሙርት ልብም እንዲሁ በመራራ ተስፋ በመቁረጥ ተሞልቶ ነበር፡፡ EWAmh 116.1

ደቀ መዛሙርቱ ለገዛራሳቸው ህይወት ፈርተው ስለነበር ሁሉም ትተውት ሸሹ፡፡ በመሆኑም በዚያ የነበረው በጭፍሮቹ እጅ የወደቀው የሱስ ብቻ ነበር: በወቅቱ ሰይጣን ምንኛ ባለ ድል ሆነ! የእግዚአብሔር መላእክት ደግሞ እንዴት ያዝኑ! እያንዳንዳቸው ረጃጅም ቁመና ባላቸው የቡድን መሪ መላእክት የታጀቡ ብዛት ያላቸው ቅዱሳን መላእክት ትዕይንቱን ለመታዘብ ተላኩ፡፡ በዚህ አስፈሪ ትዕይነት ተካፋይ የነበረ እያንዳንዱ ሰው ዳግመኛ ይመለከተው ዘንድ እነዚህ መሳእክት እያንዳንዱን በእግዚአብሔር ልጅ ላይ የሚደርስ ስድብና የጭካኔ ተግባር እንዲሁም የእርሱን ሥቃይና ህመም መዝግበው ይይዙ ነበር:: EWAmh 116.2