ቀደምት ጽሑፎች
26—በቤተክርስቲያን ስብሰባዎች ታማኝ መሆን
ሰንበት ጠባቂዎች የሚያደርጓቸውን ስብሰባዎች በአግባቡ ጠብቀው ለመያዝና መስህብነት ያላቸው ለማድረግ ታላቅ ፍላጎት ሊኖር እንደሚገባ ተመልክቻለሁ:: በዚህ አቅጣጫ ከፍ ያለ ፍላጎትና ጉልበት መታየት የሚችልበት አስፈላጊ ነገር አለ፡፡ በስብሰባው ወቅት ሁሉም ለጌታ የሚሉት ነገር ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ይህን በማድረጋቸው በረከት ያገኛሉ፡፡ ትሩፋኑ በበጉ ደምና በምስክርነታቸው ቃል ያሸንፋሉ፡፡ አንዳንዶች ምንም ዓይነት የራሳቸውን ልዩ ጥረት ሳያደርጉ በበጉ ደም ብቻ ለማሸነፍ ይጠብቃሉ፡፡ እግዚአብሔር የመናገር ኃይል በመስጠት መሐሪነቱን ተመልክቻለሁ፡፡ እርሱ አንደበት የሰጠን ሲሆን እኛ ደግሞ ከአንደበቶቻችን ለሚወጡት ቃላት የአጠቃቀም ኃላፊነት አለብን፡፡ በአንደበታችን እውነት በመናገርና ወሰን ለሌ ለው ምህረቱ እርሱን በማሞገስ በበጉ ደም አማካኝነት በምስክርነታችን ቃል ድል ማድረግ hለብን፡፡ EWAmh 85.1
በአንድነት የምንሰባሰበው አንዳችም ቃል ሳንተነፍስ እንድንለያይ አይደለም፡፡ በስብሰባ ወቅት ስለ እግዚአብሔር ክብር፣ ግርማና ብርታት የሚናገሩ በጌታ ዘንድ ይታወሳሉ---አምላካዊው በረከት በእነርሱ ላይ ያርፋል መታደስንም ያገኛሉ፡፡ ሁሉም እንደሚገባቸው ከተንቀሳቀሱ አንዳችም የሚባክን የከበረ ጊዜ አይኖርም፧ ረዘም ባሉ ጸሎቶች ዙሪያ የሚቀርብ ወቀሳም አይስተዋልም፡፡ ሁሉም ጊዜያት አጠር ባሉና ቀጥተኛነት ባላቸው ምስክርነትና ጸሎቶች የተያዙ ይሆናሉ፡፡ ጠይቅ፣ እመን፣ ተቀበል፡፡ ነገር ግን የተንዛዛ፣ ከንቱና ተርጉም የለሽ ጸሎት መላእክትን የሚያሰለችና እግዚ ብሔ ርን የማያስደስት ከመሆኑ ባሻገር በጌታ ላይ እንደ መሳለቅ ይቆጠራል፡፡ ከመጸለያችን አስቀድመን በመጀመሪያ መጸለይ እንዳለብን ሊሰማን ይገባል፡፡ በመቀጠል የሚያስፈልጉንን ነገሮች እግዚአብሔርን እንጠይቀው፡፡ እየለመንነው እያለንም ቢሆን የለመንነውን ነገር እንደሰጠን እንመን፡፡ ይህ ሲሆን እምነታችን ያድጋል፣ መታነጽ ይመጣል፣ ደካሞች ይጠነክራሉ፣ ተስፋ የቆረጡ ወደላይ በመመልከት እርሱን በጥንቃቄ ለሚፈልጉት ሁሉ እግዚአብሔር ሽልማት ሰጪ መሆኑን ያምናሉ፡፡ EWAmh 85.2
አንዳንዶች በስብሰባዎች ወቅት የሚናገሩት አዲስ ነገር ስለሌላቸውና መናገር ካለባቸው የሚናገሩት ያንኑ ባለፈው ጊዜ የተናገሩትን በመድገም በመሆኑ በስብሰባ ላለመሳተፍ ሲመርጡ ይስተዋላሉ፡፡ እግዚአብሔርና መላእክቱ በቅዱሳኑ ምስክርነት ላይ በመሳተፍ በየሳምንቱ ተደጋግመው በሚነገሩት ቃላት በእጅጉ ደስ ተሰኝተዋል-ከብረዋል፡፡ ጌታ ውስብስብነት የሌለውንና ትህትና የሞላውን አሠራር የሚወድ ሲሆን ነገር ግን የእግዚአብሔር መንግሥት ወራሾች ነን እያሉ የከበሩትን የስብሰባ ጊዜያቶቻ ቸውን በከንቱ በሚያባክኑት አይደሰትም፡፡ EWAmh 85.3
ወንድሞችና እህቶች መሆን ባሉባቸው ቦታዎች ቢሆኑ ኖሮ ለኃጢአታቸው ሲል በቀራንዮ መስቀል ላይ ለተሰቀለው የሱስ ክብር የሚሆን አንዳች ነገር ለመናገር ባልተቸገሩ ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች በደለኛው ሰው ከኃጢአት መቀጮ አምልጦና ይቅርታ አግኝቶ በህይወት ይኖር ዘንድ የሱስ ሥቃይና መንገላታትን መቀበሉንና እግዚአብሔር አንድ ልጁን ለኃጢአታችንና መተላለፋችን መስዋዕት ሆኖ እንዲሞት በመስጠት ምን ያህል እራሱን ዝቅ እንዳረገ በጥልቀት ቢገነዘቡ ኖሮ የሱስን ለማመስገንና ከፍ ከፍ ለማድረግ አብልጠው ዝግጁ ይሆኑ ነበር EWAmh 86.1
ሰላማቸውን እንደያዙ መቆየት ስለማይሆንላቸው በምስጋናና በአድናቆት ስለ ክብሩና ገናናነቱ ይናገሩ ነበር: ይህን በማድረጋቸው ከእግዚአብሔር የተላከ በረከት በላያቸው ባረፈ ነበር፡፡ ተመሳሳይ ታሪክ እንኳ ተደጋግመው ተነግረው ቢሆን ኖሮ እግዚአብሔር ግን በከበረበት ነበር፡፡ መልእኩ ያለማቋረጥ ቀንና ሌት «ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ጌታ እግዚአብሔር ኃያል” የሚሉትን በማሳየት «እነርሱ በተደጋጋሚ ቃላት ማወደሳቸውን ቢቀጥሉም እግዚአብሔር ግን ይከብርበታል” አለኝ፡፡ ምንም እንኳእኛም ተመሳሳይ ታሪኮችን በተደጋጋሚ ብንናገርም እግዚአብሔር ግን ይከብርበታል፡፡ እኛም የእርሱን መልካምነትና መሃሪነት ልብ እንዳላልን ተደርጎ አያስቆጥርብንም:: EWAmh 86.2
ለይስሙላ የቆሙ ቤተክርስቲያናት ቅዝቃዜና ሞት በላያቸው ነግሶ ሲወድቁ ተመልክቻለሁ፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል ተከትለው ቢሆን ኖሮ ትሁታን ባረጋቸው ነበር፡፡ ነገር ግን እነርሱ ከጌታ ሥራ በላይ አልፈው ሄደው ነበር፡፡ በአንድ ላይ ሲገናኙ ስለ ጌታ በጎነት የሚያወሱ ቀላልና አንድ ዓይነት ታሪኮችን ደጋግሞ ማቅረብ ለእነርሱ በእጅጉ እንደ ውርደት ይቆጠር ነበር፡፡ እነርሱ ያጠኑ የነበረው አዲስና ታላቅ ነገር በማግኘት ከአንደበቶቻ ቸው የሚወጡት ቃላት ጆሮን መኮርኮር የሚችሉና ሰውን የሚያስደስቱ እንዲሆኑ ስለነበር የእግዚአብሔር መንፈስ ይተዋቸዋል፡፡ ትሁት ሆኖ የቀ ረበውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ አካሄድ ስንከተል በእግዚአብሔር መንፈስ እንነካለን፡፡ በእግዚአብሔር ላይ ሙሉ ለሙሉ በመተማመን ትሁት የሆነውን የእውነት መንገድ የምንከተል ከሆነ ሁሉም ነገር በጣፋጭ ውህደት ውስጥ ከመሆን ውጪ በክፉ መላእክት የመታወክ አደጋ አይኖርም፡፡ ነፍሳት በራሳቸው ብርታትና ጥንካሬ በመንቀሳቀስ ከእግዚአብሔር መንፈስ በላይ ሲሆኑ መላእክት እነርሱን መመልከት ስለሚያቆሙ በሰይጣን እንግልት ውስጥ ይተዋሉ የእግዚአብሔርን ሕዝቦች ትሁት አድርጎ በመጠበቅ ከዓለምና ከውድቀት የሚታደጉ ተግባራት በእግዚአብሔር ቃል ላይ ሰፍረው ይገኛሉ፡፡ የእግር ጥበትና የጌታ እራት ፕሮግራም በተደጋጋሚ በቤተክርስቲያን ሊዘወተር ይገባል፡፡ የሱስ ያደረገውን እንድንከተል ምሳሌ ትቶልን አልፏል፡፡ የእርሱ ምሳሌ በትክክል በቀረበው መሰረት ሊደረግ እንደሚገባ የተመdከትኩ ቢሆንም ነገር ግን ሁል ጊዜም ቢሆን ወንድም እና እህቶች የእግር እጥበት መካሄድ ባለበት ሥርዓት መሰረት በጥንቃቄ እየተንቀሳቀሱ ባለመሆናቸው ግራ መጋባት ሲፈጠር ይስተዋላል፡፡ ይህ ሥርዓት በአዳዲስ ስፍራዎች በጥንቃቄና በጥበብ ሊተዋወቅ ይገባል፡፡ በተለይ በዚህ ጌታችን በተወው ምሳሌና አስተምህሮ ዙሪያ ብዙዎች ዕውቀቱ እንዲኖራቸው ባለመደረጉ የተሳሳተግምት እንዲኖራቸው ሆኗል፡፡ አያሌ ታማኝ ነፍሳት ቀደም ብለው ይተማመኑባቸው የነበሩ መምህራኖቻቸው ባሳደሩባቸው ተጽእኖ ሳቢያ በዚህ ሥርዓት ዙሪያ በእጅጉ የተሳሳተግምት በመያዛቸው አግባብ ባለው ጊዜና ሁናቴ አስተምህሮውን እንዲተዋወቁ ሊደረግ ይገባል፡፡ EWAmh 86.3
ወንድሞች የእህቶችን እግር እንዲያጥቡ በቃሉ የተተወ ምሳሌ ባይኖርም ነገር ግን እህቶች የወንድሞችን እግር ያጠቡበትን አንድ ምሳሌ እናገኛለን:: ማርያም የየሱስን እግሮች በእንባዎቿ አጥባ ስታበቃ በጸጉሮቿ አብሳለት ነበር (በተጨማሪ 1ኛ ጢሞቴ. 5:10 ይመልከቱ)፡፡ እህቶች የወንድሞችን እግሮች ያጥቡ ዘንድ ጌታ ልቦቻቸውን እንደነካ የተመለከትኩ ሲሆን ይህ የሆነው በወንጌል ትእዛዝ መሰረት ነው፡፡ ሁሉም ይህን ተግባር ሲያከናውኑ በማስተዋል እንጂ እንደ አሰልቺ ሥርዓት ሊቆጥሩት አይገባም፡፡ EWAmh 87.1
በየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ላይ በሐዋርያው ጳውሎስ ስለ ሰላምታ የተጠቀሰው የተቀደሰ አሳሳም ምን ጊዜም ቢሆን ሊስተዋል የሚገባው ከእውነተኛ ባህሪው አኳያ ነው፡፡ ክርስቲያን ወዳጆች በሳምንትም ሆነ በወር ሲገናኙና ተሰባስበው ሲለያዩ የተቀደሰ አሳሳም እንደ ህብረታቸው ምልክት ሆኖ ሊስተዋል ይገባል፡፡ ጳውሎስ በ1ኛ ተሰ. 5:26 «ወንድሞችን ሁሉ በተቀደሰ አሳሳም ሰላም በሏቸው» በማለት የሚናገር ሲሆን በዚሁ ምዕራፍ ላይ «ከማናቸውም ዓይነት ክፉ ነገር ራቁ» በማለት ይነግረናል፡፡ የተቀደሰ አሳሳም አግባብ ባለው ጊዜና ቦታ ከተደረገ የክፉ መገኘት ሊኖር አይችልም:: EWAmh 87.2
የጠላት ጠንካራ እጅ ከእግዚአብሔር ሥራ በተቃራኒ እንደነበርና የእውነትን መሰረት የሚወድ እያንዳንዱ ሰው በብርታት እርዳታውን ለመለገስ መመልመልና መቀላቀል እንደነበረበት ተመልክቻለሁ፡፡ እውነትን የሚያሰራጩ ወገኖችን በመደገፉ ረገድ ታላቅ ፍላጎት በማሳየት ያለ ማሰለስ በሚያደርጉት ተኩረት የተሞላው ጥንቃቄ ጠላትን መገርሰስ ይችላሉ፡፡ ሁሉም በሥራው በመተባበር እንደ አንድ ሰው መም ይኖርባቸዋል:: መደረግ ያለበት ነገር ሁሉ በፍጥነት ሊደረግ ስለሚገባ እያንዳንዱ ኃይል በንቃት መጠባበቅ ይኖርበታል፡፡ EWAmh 87.3
ከዚያም ሦስተኛውን መልአክ አየሁ: አብሮኝ በመሆን የሚረዳኝ መልአክ እንዲህ አለኝ «ሥራውም ሆነ ተልዕኮው አስፈሪ ነው፡፡ ስንዴን ከእንክርዳድ የሚለየውና ምርቱን በአንድ የሚያስረው ይኸው መልአክ ነው፡፡ እነዚህ ነገሮች መላውን ትኩረት ሊስቡ ይገባል፡፡» EWAmh 88.1