ቀደምት ጽሑፎች

25/73

24—ቤተ ክርስቲያናዊው ተስፋ

የየሱስ ተከታዮችን ትሁት፣ የዋህና ገር ማንነት ቆየት ብዬ ዳግመኛ ስመለከት አእምሮዬ ብዙ ነገሮችን አስተዋለ፡፡ በቅርብ እውን የሚሆነውን የሱስን ዳግም ምጽ>ት አጥብቀው የሚከታተሉ ይመስሉ የነበሩ ብዙዎች ከአምላካዊው አመለካከት ይልቅ ከዚህ ዓለም ጋር በመስማማት በዙሪያቸው የነበሩትን ውዳሴ አጥብቀው ይሹ ነበር፡፡ ቀደም ብለው በነበሩባቸው አብያተክርስቲያናት ይስተዋል እንደነበረው ዓይነት ቀዝቃዛና ሥርዓት ብቻ የሚከተሉ ናቸው፡፡ ለላውዶቂያ ቤተክርስቲያን የተነገሩት ቃላት አሁን ያሉበትን ሁናቴ ፍጹም በሆነ መልኩ ይገልጸዋል «ለብ ያልክ ብቻ እንጂ ትኩስ ወይም ቀዝቃዛ ስላልሆንህ» (ራእ. 3:14:20)፡፡ እነዚህ ሰዎች «ታማኝና እውነተኛ ምስክር» በመሆን በጋለ መንፈስ ንስሐ በመግባት ‹‹በእሳት የነጠረ ወርቅ»፣ «ነጭ ልብስ” እና ማየት ይችሉ ዘንድ ዓይኖቻቸውን እንዲኳሉ ይጠይቃቸዋል፡፡ ያለበለዚያ ግን ከአፉ አውጥቶ ይተፋቸዋል:: EWAmh 79.2

በአንድ ወቅት በቅርብ ዕውን የሚሆነውን የጌታን ዳግም ምጽአት በመመልከት በደስታ ፈንድቀውና ድምጾቻቸውን ከፍ አድርገው የጮኹ ወገኖች አሁን የቤተክርስቲያን መሰረት የሚሆኑበት ጊዜ መጥቶአል፡፡ እነዚህ ሰዎች በየሱስ ዳግም ምጽአት በማመናቸው ዓለም በእነርሱ ላይ እንዲሳለቅ ለማድረግና ተጽእኖአቸውን ለማጥፋት ሁሉንም ዓይነት የሐሰት ተግባራት ተነዝቶባቸዋል:: ነገር ግን አሁን ማንም ሕያው አምላክን በመናፈቅ ጽድቅን ቢራብና ቢጠማ--እግዚአብሔር ፍቅሩን በልቡ ውስጥ በማፍሰስ ኃይሉን ያድስለታል፣ የነፍሱንም መናፈቅ ያረካለታል፡፡ ደግሞም ለእግዚአብሔር ምስጋና በማቅረብ ክብርን ለእርሱ ቢሰጥ--በእነዚህ በክርስቶስ ዳግም ምጽአት ላይ በተሳለቁ አስመሳይ አማኞች--ከመስመር የወጣ አማኝ ተደርጎ በመፈረጅ ማሾፊያቸው ይሆናል፡፡ EWAmh 80.1

አብዛኞቹ እነዚህ ኣስመሳይ ክርስቲያኖች አለባበሳቸው፣ አነጋገራቸውና ድርጊታቸው እንደ ዓለም በመሆኑ አማኝ መሆናቸው በብቸኝነት ሊታወቅ የሚችልበት መንገድ ሥራቸው መሆኑ ነው፡፡ ምንም እንኳ ክርስቶስን እንደሚመስሉ ሲናገሩ ቢደመጡም ነገር ግን አነጋገራቸው በዓለማዊው ነገሮች እንጂ በሰማይ የሉም፡፡ ታዲያ «እንዴት ዓይነት ሰዎች” ሊሆኑ ይገባል? «በቅድስናና በእውነተኛ መንፈሳዊነት” ሊኖሩ ይገባል፡፡ «ደግሞም የግዚአብሔርን ቀን» እየተጠባበቁ «መምጫውን» ሊያፋጥኑ «ይገባል” (2ኛ ጴጥ. 3፡፡11-12)፡፡ «በርሱ ይህን ተስፋ የሚያደርግ ሁሉ እርሱ ንጹህ እንደሆነ እራሱን ያነጻል» (1ኛ ዮሐ, 3:3)፡፡ ነገር ግን አብዛኞቹ የአድቬንቲስትን ስም ያያዙ ሰዎች ጊዜአቸውን የሚያባክኑት የአግዚአብሔ ርን ቃል በማጥናትና በፊቱ ድጋፍ ለማግኘት በመጣር ሳይሆን ነገር ግን አካላቸውን በማስጌጥና በዓለም ዐይን መልካም ሆነው ለመታየት ጥረት በማድረግ መሆኑ በማስረጃ የተደገፈ ነው፡፡ EWAmh 80.2

ምሳሌያችን የሆነው ተወዳጁ የሱስ ልክ እንደ መጀመሪያው ምጽአቱ በእነርሱና በአጠቃላይ በሥነ መለኮት ፕሮፌሰሮች በመካከል እራሱን ቢገልጥስ? እርሱ የተወለደው በከብቶች በረት ውስጥ ነበር፡፡ መላውን የእርሱን ህይወትና አገልግሎት ስንመለከት የሐዘን ሰው ነበር፡፡ በመሆኑም Áነዚህ ክርስቲያን ነን ባዮች--ቀላል፣ ትሑት፣ ማንነቱን ዝቅ ባደረገውና እራሱን የሚያስጠጋበት እንኳ ባልነበረው አዳኝ ማንነት ኃፍረት በተሰማቸው ነበር፤ የእርሱ እንከን ዐልባና እራስን የመካድ ህይወት በኮነናቸው ነበር፡፡ የተረጋጋውና ሞገስ የተላበስ ቅድስናው የእነርሱን ቅለትና ከንቱ ስላቅ በመገደብ ቀጥተኛና ግልጽ ንግግሩ ዓለማዊና ድብቅ ቋንቋቸውን በመረመ ረ ነበር የሱስ የማይጠፋውን እውነት በማብሰርና የተባ ስለት ያለውን እውነት ይፋ በማድረግ እውነተኛውን ባህሪያቸውን ስለሚገልጸው--እርሱን ከንግግሩ ለማጥመድ ከሚሞክሩት መሃል እንደ አንዱ በመሆን ስቀለው ስቀለው!” ለማለት የመጀመሪያዎቹ ይሆናሉ EWAmh 80.3

የየሱስ በትህትና ወደ የሩሳሌም ሲገባ የነበረውን ሁናቴ እንከታተል «ቁጥራቸው እጅግ ብዙ የሆነ ደቀ መዛሙርት ስላዩት ተአምራት ሁሉ ደስ እያላቸው ድምጻቸውን ከፍ በማድረግ. . . በጌታ ስም የሚመጣ ንጉሥ የተባ ረh ነው! በሰማይ ሰላም በአርያም ክብር ይሁን! በሕዝቡ መካከል የነበሩ አንዳንድ ፈሪሳውያን የሱስን መምህር ሆይ ደቀ መዛሙርትህን ገስጻቸው እንጂ’ አሉት፡፡ እርሱም እላችኋለሁ ፧ እነርሱ ዝም ቢሉ ድንጋዮች ይጮኻሉ’ አላቸው:፡፡” ክርስቶስን ለመፈለግ ወጥተናል ከሚሉ ውስጥ አብዛኞቹ ልክ ደቀ መዛሙርቱን ዝም አሰኝ እንዳሉት ፈሪሳውያን ያለ ምንም ጥርጥር «አክራሪነት! ሐሰተኛ ራእይ! ሐሰተኛ ራእይ! እያሉ መጮኻቸው አይቀሬ ነው፡፡ ዘርፋፋ ቀሚስ የለበሱትንና የዘንባባ ዝንጣፊ የያዙትን ደቀ መዛሙርት ደግሞ አባካኝና ያልሠለጠኑ ብለው ሊዘልፏቸው ይችላሉ፡፡ እግዚአብሔር ግን ከእነዚህ ቀዝቃዛ ሰዎች በተቃራኒ እርሱን የሚያመሰግኑና ክብር የሚሰጡት ሐዝቦች ይኖሩታል፡፡ እርሱ ምርጫው ከሆኑና ትእዛዛቱን ከሚጠብቁ ወገኖች ክብርን ይቀበላል፡፡ የሱስ ዳግም የሚገለጽ ቢሆንም ነገር ግን አመጣጡ በቤተልሔም እንደተወለደው ህጻን ዓይነት አይሆንም:: በአህያ ውርንጭላ ወደ የሩሳሌም ሲገባ ደቀ መዛሙርቱ «ሆሳእና” በማለት እግዚአብሔርን በማመስገን እንደጮኹትም አይደለም:፡፡ ነገር ግን አመጣጡ በአባቱ ክብርና በሰማይ መላእክት ታጅቦ ይሆናል፡፡ በሰማይ ያሉ መላእክት በሙሉ ሰማይን ባዶ አድርገው እርሱን ሲያጅቡት ፤ በምድር የሚጠባበቁት ቅዱሳን ደግሞ የገሊላ ሰዎች ከደብረዘይት ተራራ ላይ ሲያርግ እንደተመለከቱት ወደ ሰማይ ቀና ብለው ያዩታል፡፡ ከዚያም ትሁት የሆነውን ምሳሌ ሙሉ ለሙሉ የተከተሉ ቅዱሳን ብቻ በደስታ በመነጠቅ እርሱን ሲመለከቱ እንዲህ ብለው ይጮኻሉ «እነሆ አምላካችን ይህ ነው በእርሱ ታመንን፧ እርሱም አዳነን፡፡» ከዚያም ይለወጣሉ «ይህም የሚሆነው የመጨረሻው መለከት ሲነፋ ድንገት በቅጽበተዓይን ነው፡፡» ያ ቅዱሳን ካንቀላፉበት የትቢያ መኝታቸው የሚቀሰቅሳቸውና በክብር የተሞላውን የማይበሰብስ ማንነት የሚያለብሳቸው የመለከት ድምጽ ሲሰማ «ድል! በሞት ላይ ድል! በመቃብር ላይ ድል! በማለት ይጮኻሉ፡፡ የተለወጡት ቅዱሳን ጌታን በአየር ለመገናኘት በአንድ ላይ ይነጠቃሉ፡፡ ከዚህ በኋላ ከሚወዷቸው ጋር ፈጽሞ አይለያዩም፡፡ EWAmh 81.1

ይህን ከፊታችን የተቀመጠ በክብር የተሞላ ተስፋ እንደያዝን ክርስቶስ በደሙ የገዛልንን ደኅንነት---ሰላማችንን ይዘን መቀመጥ ነው ያለብን? የሱስ ወደ የሩሳሌም ሲገባ ደቀ መዛሙርቱ እንዳደረጉት እኛም ድምጻችንን ከፍ አድርገን እግዚአብሔርን ማመስገን አይገባንም? የእኛ ተስፋ እነርሱ ከነበራቸው ይልቅ የራቀ ግርማ የተላበሰ ነው? ይህ ህያውና በክብር የተሞላ ተስፋ እያለን ነገር ግን ድምጻችንን ከፍ አድርገን እግዚአብሔርን እንዳናከብረው የሚከለክለን ማን ነው? ወደፊት የሚመጣውን ገናና ዓለም በመቅመሳችን ከዚህ በላይ እንናፍቃለን፡፡ መላው አኔነቴ ሕያው አምላክን ተከትሎ ይጮኻል፤ በእርሱ ሙላት እስክጥለቀለቅ ድረስ ድረስ ፈጽሞ አልረካም፡፡ EWAmh 81.2