ቀደምት ጽሑፎች

10/73

9—ለታናሹ መንጋ

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፡፡ ጥር 26/1850 ዓ.ም. ላይ ጌታ የሚከተለውን ራእይ ሰጥቶኝ ነበር አንዳንዶቹ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ደካማ አስተሳሰብ ያላቸውና በግማሽ ልብ በቻ የነቁ እንደሆኑ ተመልእቼአለሁ፡፡: እነዚህ ሕዝቦች አሁን እየኖርን ያለንበትን ዘመን የሚገነዘቡ አይመስልም፡፡ ይህን ተከትሎ አንዳንዶች በስህተት ተጠራርገው የመወሰድ አደጋ ላይ ናቸው፡፡ እነዚህን ሰዎች የሱስ እንዲያድናቸው---ያሉበትን አስፈሪ አደጋ በመመልከት ጥፋቱ ዘላለማዊ ከመሆኑ አስቀድሞ ከወዲሁ ይዘጋጁ ዘንድ ለጥቂት ተጨማሪ ጊዜያት እንዲታደጋቸው ልመናዬን አቅርቤአለሁ፡፡ «ጥፋት ልክ እንደ ሚጠቀለል ከባድ ዐውሎ ነፋስ እየመጣ ነው» በማለት መልአኩ በነገ ረኝ ጊዜ ይህን ዓለም የወደዱትን፣ ከሐብትና ንብረቶቻቸው ጋር የተጣበቁትንና ከእነዚህ ነገሮች ጋር ያላቸው ጠንካራ ግንኙነት ላልቶ ከእነርሱ እንዲበጠስ ለማይፈልጉትና መንፈሳዊውን ምግብ አጥተው የሚጠፉትን የተራቡ ጠቦቶችን ለመመገብ የሚንቀሳቀሱትን መልእክትኞች በመደገፍ መስዋዕ ትነት ለመክፈል ፈቃደኞች ላልሆኑት ለእነዚህ ሕዝቦች ያዝንላቸውና ያድናቸው ዘንድ መልአኩን ለመንኩት፡፡ EWAmh 32.1

ወቅታዊውን እውነት በመሻት እየሞቱ ወደ ነበሩት ምስኪን ነፍሳት ስመለከት እውነት አላቸው የተባሉ አንዳንዶች ለእነዚህ ሕዝቦች በማስተላለፍ ፋንታ አምቀው በመያዝ ይሞቱ ዘንድ በመፍቀድ የእግዚአብሔር ሥራ ወደፊት እንዳይገሰግስ ሲያደርጉ መመልከት በእጅጉ ህመም ያለው ነበር፡፡ በመሆኑም መልአኩ ይህን ትዕይንት ከእኔ ይወስደው ዘንድ ለመንኩት፡፡ አምላካዊውን ሥራ ወደፊት ለማስኬድ ንብረታቸውን በመሸጥ ነፍሳትን ለማዳን ሥራ እንዲያውሉ ሲጠየቁ ወደ የሱስ መጥቶ እንደነበረው ሐብታም ወጣት (ማቴ. 19:16-22) በአዘኔታ ሲሄዱ ተመልክቼአለሁ:: ሆኖም ከዚህ በኋላ ብዙም ሳይቆይ የሚወርደው መቅሰፍት ሐብትና ንብረታቸውን በሙሉ ጠራርጎ ያጠፋዋል፡፡ ያን ጊዜ ምድራዊውን ንብረት መስዋዕት አድርጎ ለማቅ ረብና በሰማያዊው መዝገብ ለማስቀመጥ የዘገዩ ይሆናሉ፡፡ EWAmh 32.2

ከዚያም ውብና ተወዳጅ የሆነውን በክብር የተሞላ አዳኝ ተመለከትኩ፡፡ እርሱ ግርማ የተሞላውን 7ዛት ትቶ ጻድቅና የከበረውን ህይወቱን ጻድቅ ላልሆኑት ሊሰጥና ሊሞት ወደዚህ ጨለማና ብቸኛ ዓለም መጣ:: ጨካኞችንና ዘባቾችን ተቋቁሞ በማለፍ የእሾህ አክሊል ጉንጉን አደረገ፡፡ የዓለም ኃጢአት ሸክም በሙሉ በእርሱ ላይ ስለነበር በጌተሰማኔ ትላልቅ የደም ጠብታ ላቦች ተንጠባጠቡ፡፡ «ይህ ለምን ሆነ?” ሲል መልአኩ ጠየቀኝ፡፡ እኔም እንደተመለከትኩ ለእኛ የሆነውን ነገር ወዲያውኑ አወቅኩበከበረው በእርሱ ደም ለእግዚአብሔር ይዋጀን ዘንድ ለእኛ ኃጢአት ሲል እርሱ ይህን ሁሉ ሥቃይ ተቀብሏልና! EWAmh 32.3

ከዚያም የሱስ ደሙን፣ ሥቃዩንና ሞቱን ይዞ በአብ ፊት በመቅረብ ስለ እነርሱ ተማጽኖውን እያቀረበና እነዚህ ሕዝቦች በአምላካዊው ማኀተም ይታተሙ ዘንድ የእግዚአብሔር መልእክትኞች የሚያድነውን እውነት ወደ እነርሱ ለማድረስ እየተጠባበቁ ባሉበት በዚህ ወቅት የዚህን ዓለም ንብረቶቻ ቸውን ሸጠው እውነትን ያሰራጩ ዘንድ እየጠፉ ያሉትን ነፍሳት ለማዳን ፈቃደኛ ያልነበሩትን በድጋሚ ተመለከትኩ፡፡ በወቅታዊው እውነት እናምናለን የሚሉ አንዳንዶች---በመጋቢነት ያገለግሉት ዘንድ አግዚአብሔር በራሱ ገንዘብ ላይ ሾሞአቸው ሳለ ነገር ግን ይህን ገንዘብ ለመልእክትኞቹ ለመስጠት ከባድ ይሆንባቸዋል፡፡ EWAmh 33.1

እጅግ ጥልቅ የሆነው ፍቅሩ ህይወቱን ለሰዎች እንዲሰጥ ያደረገውን የየሱስን ስቃይ እንዲሁም የዚህ ዓለም ንብረት የነበራቸውንና ይህን ገንዘባቸውን በደኅንነት ሥራ ላይ ለማዋል እንደ ትልቅ ነገር ቆጥረውት የነበሩ---የእርሱ ተhታዮቹ ነን የሚሉትን ህይወት ዳግመኛ በራእይ ተመለከትኩ፡፡ ‹‹እንደነዚህ ዓይነቶቹ ሰማይ መግባት ይችላሉ?” በማለት መልአኩ ሲጠይቅ ሌላው ቀበል አደረገና «በፍጹም አይችሉም:: በምድራዊው የእግዚአብሔር ሥራ ፍላጎት የሌላቸው-የሚዋጀውን ፍቅር የሚገልጸውን ሰማያዊ ዝማሬ መዘመር አይችሉም” በማለት መለሰ፡፡ እግዚአብሔር በምድር ላይ እየሠራ የነበረው ፈጣን ሥራ ጊዜ ሳይወስድ በጽድቅ እንደሚያጥርና መልእክትኞች ተበታትነው የነበሩ መንጋዎችን ፍለጋ በፍጥነት መሰማራት እንዳለባቸው ተመለከትኩ፡፡ «እነዚህ ሁሉ መልእክትኞች ናቸው?» በማለት መልአኩ ሲጠይቅ ሌላው «አይደሉም፡፡ የእግዚአብሔር መልእክትኞች መልእክት አላቸው» በማለት መለሰ፡፡ EWAmh 33.2

የእግዚአብሔር ሥራ ከእግዚአብሔር መልእክት በሌላቸው ሰዎች ሲጓተትና ክብር ሲነፈገው ተመለከትኩ፡፡ እንደነዚህ ዓይነቶቹ ሰዎች ወደ ማይመለከቷቸው ስፍራዎች ጉዞ በማድረግ ላባከነት እያንዳንዱ ብር በአግዚአብሔር ፊት ተጠያቂነት ይኖርባቸዋል:: ምክንያቱም ዕድሉ ቢኖር ኖሮ ያ ገንብ በእርሱ በተጠሩና በተመረጡ መልእክትኞች አማካኝነት ለግዚአብሔር ሥራ እንዲሁም መንፈሳዊውን ምግብ አጥተው ለተራቡተና ለሞቱት ነፍሳት ይውል ነበር። በእጆታቸው አገልግሎት ለመስጠትና ሥራውን ደግፈው ለመያዝ ብርታት የነበራቸውም እንዲሁ— በንባቸው ተጠያቂ እንደነበሩት እነደነያእነዚህም በብርታታቸው ተጠያቂነት እንደነበረባቸው ተመልክቼአለሁ:: EWAmh 33.3

ብርቱ የሆነው ብጠራ ተጀምሮአል—በዚሁ ይቀጥላል። ለእውነት፣ ለእግዚአብሔርና ለሥራው ደፋርና የማያወላውል አቋም ለመውሰድ ፈቃደኞች ያልሆኑ ሁሉ ተበጥረው ይወጣሉ፡፡ ‹‹ማናቸውም መስዋዕት ይሆኑ ዘንድ ግፊት ይደረግባቸዋል? በጭራሽ ይህ በፈቃደኝነት የሚደረግ መስዋዕት መሆን ነው ያለበት» በማለት መልአኩ ተናገረ። እጅግ በመዛል እራሳቸውን እየሳቱና እየሞቱ የነበሩትን ሕዝቦቹን እግዚአብሐር ይታደግ ዘንድ ጩኸቴን ወደ እርሱ አሰማሁ:: ከዚያም የኃያሉ አምላክ ፍርድ በፍጥነት እየመጣ መሆኑን በመመልከቴ መልአኩ ሕዝቡን በቋንቋው ያናግር ዘንድ ለመንኩት እርሱም ግልጽ በሆነው የእግዚአብሔር ቃል እውነት ልባቸው ያልተነውን ሰዎች በሲና ተራራ ላይ ወርዶ የነበረው ያ ሁሉ መበረቅና ነጎድጓድ ሊነካው አይችልም›› በማለት ተናገረ: EWAmh 34.1

ከዚያም የየሱስን ውብነትና ተፈቃሪነት ተመለከትኩ፡፡ የለበሰው መጎናጸፊያ ከነጭ ሁሉ የላቀ ንጣት ነበረው፡፡ የእርሱን ክብርና ተወዳጅነት የትኛውም ቋንቋ ሊገልጸው አይችልም ነበር፡፡ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁ ሁሉ በከተማዋ በር አልፈው ይገባሉ የህይወት ዛፍም ባለመብት ናቸው፡፡ እነዚህ ገጽታቸው ከቀትር ጸሐይ በላይ የሚያንጸባርቅ ሕዝቦች ከቅዱሱ የሱስ አብሮነት ውጪ አይሆኑም:: EWAmh 34.2

በኤደን ገነት ወደነበሩት አዳምና ሔዋን እንድመለከት ሆነ፡፡ እነርሱ ከተከለከለው ፍሬ በመብላታቸው ከኤደን ገነት እንዲባረሩ በተደረጉ ጊዜ ዳግመኛ እጃቸውን ዘርግተው ከህይወት ዛፍ እንዳይበሉና የማይሞቱ ኃጢአተኞች እንዳይሆኑ በየአቅጣጫው የሚገለባበጥ ነበልባላዊ ሰይፍ በህይወት ዛፍ ዙሪያ ተቀመጠ፡፡ የህይወት ዛፍ ዘላለማዊነት እንዲቀጥል የምታደርግ ነበረች፡፡ መልአኩ «ከአዳም ቤተሰብ ውስጥ ነበልባላዊቱን ሰይፍ አልፎ የህይወትን ዛፍ የበላ ማን ነው?” በማለት ሲጠይቅ ሰማሁ፡፡ ከዚያም ሌላ መልአክ እንዲህ ሲል መለሰለት «ነበልባላዊቷን ሰይፍ አልፎ ከፍሬዋ የበላ አንድም የአዳም ቤተሰብ የለም:: ስለዚህ አንድም የማይሞት ኃጢአተኛ የለም:፡፡ ኃጢአት የሠራችን ነፍስ የትንሳኤ ተስፋ የሌለው ዘላለማዊ ሞት ትሞታለች፡፡ ከዚያም ቁጣ በላይዋ ይሆናል፡፡ EWAmh 34.3

«ቅዱሳን በቅድስቲቱ ከተማ በማረፍ እንደ ነገሥታትና ካኅናት ለአንድ ሺህ ዓመት ይነግሣሉ ከዚያም የሱስ ከእነዚህ ቅዱሳን ጋር በመሆን ደብረዘይት ተራራ ላይ ይወርዳል፧ ተራራውም ተለይቶ የእግዚአብሔር ገነት የሚያርፍበት ኃያልና ግዙፍ መስክ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ቀሪው የምድር ክፍል ኃጥአን ከሞት ተነስተው ከተማዋን እስከሚከቡበት እስከ አንድ ሺሁ ዓመት መጨረሻ አይነጻም፡፡ የኃጥአን እግሮች አዲሲቱን ምድር ፈጽሞ አያ ረክሱም፡፡ እሳት ከእግዚብሔር ዘንድ ከሰማይ ይወርድና ይበላቸዋል--ሥርና ቅርንጫፍም አይተውላቸውም: ሰይጣን ሥር ሲሆን ልጆቹ ደግሞ ቅርንጫፎቹ ናቸው ኃጥአንን የሚበላው ያው እሳት ምድርን ያነጻል፡፡» EWAmh 34.4