አእምሮ፣ባሕርይና ማንነት፣ክፍል 1
ምዕራፍ 21—ክርስቶስ አእምሮዎችን ይመረምራል
የክርስቶስ ትምህርት መሪ መሆን አለበት።--የክርስቶስ ትምህርት፣ ልክ እንደ ርኅራኄው፣ ዓለምን አቅፏል። በእርሱ ትምህርት ውስጥ አስቀድሞ ያልተነገረና ስለ መርሆዎቹ ትምህርት ያልሰጡበት የሕይወት ሁኔታ፣ የሰብአዊ ልምምድ ችግር፣ በፍጹም ሊኖር አይችልም። የመምህራን አለቃ ቃላት፣ አብረውት ለሚሰሩ ሰዎች እስከ ዘመን ፍጻሜ ድረስ መሪ ይሆኑአቸዋል። --Ed 81, 82 (1903). {1MCP 181.1} 1MCPAmh 149.1
እርሱ ራሱን ከአድማጮቹ ፍላጎቶች ጋር አገናኘ።--እርሱ ያስተማረው ራሱን ከእነርሱ ፍላጎቶችና ደስታ ጋር የማገናኘቱ ሙሉነት ሊሰማቸው በሚችልበት መንገድ ነበር። ትምህርቱ ቀጥተኛ፣ በምሳሌ የሚሰጣቸው ገለጻዎች ተገቢ፣ ቃላቱም በርኅራኄና በደስታ የተሞሉ ስለነበር አድማጮቹ ተማርከው ነበር።--MH 24 (1905). {1MCP 181.2} 1MCPAmh 149.2
የሰብአዊ አእምሮን ድብቅ አሰራር ይረዳል።--ሰዎችን ለማዳን ገደብ የለሽ ዋጋን የከፈለው የሰብአዊ አእምሮን ድብቅ አሰራሮችን ሁሉ በማይሳሳት ትክክለኛነት ስለሚያነብ እያንዳንዱን ነፍስ እንዴት እንደሚመረምር ያውቃል። ከሰዎች ጋር በሚሰራበት ጊዜ እነዚያኑ በተፈጥሮ ዓለም ውስጥ የተገለጡ መርሆዎችን ያሳያል።--SpT Series A, No. 3, p 17, 1895. (TM 189, 190.) {1MCP 181.3} 1MCPAmh 149.3
እርሱ የሚሰራው በተረጋጋ፣ መደበኛ በሆነ የህጎች አሰራር ነው።--እግዚአብሔር ራሱ ባስቀመጣቸው በተረጋጉና መደበኛ በሆኑ የሕጎች አሰራር ይሰራል። በመንፈሳዊ ነገሮችም እንደዚሁ ነው። ሰይጣን በጥባጭና ኃይለኛ በሆኑ የማስገደጃ መንገዶች አማካይነት ተጽእኖ ለማሳደር ያለማቋረጥ ይሻል፣ ነገር ግን ኢየሱስ አእምሮዎችን እጅግ ታዋቂ በሆኑ ግንኙነቶች አማካይነት መድረስ ችሏል። በተቻለ መጠን በተለምዶ ተያያዥነት ያለውን ሀሳባቸውን በድንገተኛ ተግባሮች ወይም በትዕዛዝ በተቀመጡ ደንቦች አልረበሸም። በራሱ እምነት ሰውን ስላከበረ በእርሱ ክብር አስቀመጠው። አሮጌ እውነቶችን በአዲስና ክቡር ብርሃን አስተዋወቀ። በመሆኑም ገና የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ሳለ በመቅደስ ውስጥ በጠየቃቸው ጥያቄዎቹ የህግ ዶክተሮችን አስደመመ። --MS 44, 1894. (Ev 139, 140.) {1MCP 182.1} 1MCPAmh 149.4
ሁል ጊዜ በሰላም መከበብ።--የእርሱ ገርነት ያለበት ርኅራኄ በደከሙና በተረበሹ ልቦች ላይ በሚፈውስ ንካት አረፈ። በቁጡ ጠላቶች ረብሻ መካከል እንኳን በሰላም ከባቢ አየር ተከቦ ነበር። የፊቱ ውበት፣ የባሕርዩ ተወዳጅነት፣ ከሁሉም በላይ፣ በእይታና በዜማ የተገለጸ ፍቅር፣ ባለማመን ልባቸው ያልጠነከረውን ሁሉ ወደ እርሱ ስቧል። በእያንዳንዱ እይታና ቃል በርቶ የታየው ጣፋጭ፣ የርኅራኄ መንፈስ ባይኖርበት ኖሮ ያኔ ስቦ የነበረውን ታላቅ ጉባኤ ወደ ራሱ መሳብ አይችልም ነበር። ወደ እርሱ የመጡ ችግረኞች እርሱ እንደ ታማኝና ገር ጓደኛ የራሱን ፍላጎት ከእነርሱ ፍላጎት ጋር እንዳገናኘ ስለተሰማቸው ስለሚያስተምራቸው እውነቶች የበለጠ ማወቅ ፈለጉ። ሰማይ ቀርቦአቸው ነበር። የእርሱ የፍቅር መጽናናት ሁል ጊዜ አብሮአቸው መሆን እንዲችል በእርሱ ፊት ለመሆን ፈለጉ።--DA 254, 255 (1898). {1MCP 182.2} 1MCPAmh 149.5
የእርሱ ሕይወት የተጣጣመ ነበር።--የናዝሬቱ ኢየሱስ በሕይወቱ ከሰዎቹ ሁሉ የተለየ ነበር። መላው ሕይወቱ አድልዎ በሌለው ልግስናና በቅድስና ውበት የሚታወቅ ነበር። በልቡ ውስጥ ከእያንዳንዱ የራስ ወዳድነትና የኃጢአት ብክለት ነጻ የሆነ ንጹህ ፍቅር አለ። ሕይወቱ በፍጹም የተጣጣመ ነበር። የመልካምነትና የፍጽምና እውነተኛ ምሳሌ እርሱ ብቻ ነው። ከአገልግሎቱ ጅምር ጀምረው ሰዎች የእግዚአብሔርን ባሕርይ የበለጠ በግልጽ መገንዘብ ጀምረው ነበር። {1MCP 182.3} 1MCPAmh 150.1
እስከ ክርስቶስ የመጀመሪያው ምጻት ድረስ ሰዎች ጨካኝና አምባገነን አምላኮችን ያመልኩ ነበር። የአይሁዶች አእምሮ እንኳን ይደረስ የነበረው በፍቅር ሳይሆን በፍርሃት ነበር። በምድር ላይ የክርስቶስ ተልዕኮ እግዚአብሔር አምባገነን ሳይሆን ለልጆቹ በፍቅርና በምህረት የተሞላ ሰማያዊ አባት መሆኑን ለሰዎች ማሳየት ነበር።--MS 132, 1902. {1MCP 183.1} 1MCPAmh 150.2
ግለትና ብርሃን የራቀው አልነበረም።--ስለ ክርስቶስ ሕይወትና ባሕርይ የተሳሳተ አመለካከት ያላቸው ብዙ ሰዎች አሉ። ሙቀትና ብርሃን የሌለው ኃይለኛ፣ ጨካኝና ደስታ የሌለው እንደነበር ያስባሉ። በብዙ አጋጣሚዎች መላው ኃይማኖታዊ ልምምድ በእነዚህ ጨለምተኛ አመለካከቶች የተቀባ ነው። --SC 120 (1892). {1MCP 183.2} 1MCPAmh 150.3
በእያንዳንዱ ሰብአዊ ፍጡር ውስጥ ገደብ የለሽ የመሻሸል ችሎታዎች አሉ።--እርሱ ሰዎችን ሊሆኑ በሚችሉበት ሁኔታ፣ በጸጋው ተለውጠው--‹‹በአምላካችን በእግዚአብሔር ውበት›› (መዝ. 90፡ 17) ሆነው ተመለከታቸው። በተስፋ እየተመለከታቸው ተስፋን አነሳሳ፣ በመተማመን ተገናኝቶአቸው መታመንን አነሳሳ። በራሱ ሰው ሊሆን የሚገባውን እውነተኛ ምሳሌ በመስጠት በውስጣቸው ያንን የማግኘትን ፍላጎትና እምነት ቀሰቀሰ። የተጣሉና የተናቁ ነፍሳት በእርሱ ፊት አሁንም ሰዎች መሆናቸውን በመገንዘብ የእርሱ ክብር የተገባቸው መሆናቸውን ለማረጋገጥ ተመኙ። ቅዱስ ለሆኑ ነገሮች ሁሉ የሞቱ በሚመስሉ በብዙዎች ልብ ውስጥ አዳዲስ ትርታዎች ተቀሰቀሱ። ተስፋ ለቆረጡ ለብዙዎች አዲስ ሕይወት የማግኘት ዕድል ተከፈተላቸው። --Ed 80 (1903). {1MCP 183.3} 1MCPAmh 150.4
የእርሱ ልብ የሕይወት ውኃ ምንጭ ነው።--ብዙ ጊዜ ኢየሱስ አለቀሰ ይባላል፣ ነገር ግን በፍጹም ፈገግታ አሳይቶ እንደማያውቅ ይገመታል። አዳኛችን ለሰዎች ዋይታ ሁሉ ልቡን ስለከፈተ በርግጥም የሀዘን ሰውና ከሀዘን ጋር የሚተዋወቅ ነበር። ነገር ግን ሕይወቱ ራስን የመካድ እና በሕመምና በጭንቀት የተጋረደ ቢሆንም መንፈሱ የተሰበረ አልነበረም። ፊቱ ሀዘንና ጭንቀት ታይቶበት የማያውቅ ሲሆን ሁል ጊዜ ሰላማዊ የመንፈስ እርካታ ይታይበት ነበር። ልቡ የሕይወት ውኃ ምንጭ ስለነበር ወደ ሄደበት ሁሉ እረፍትንና ሰላምን፣ ደስታንና ፍስሃን ይዞ ሄደ። --SC 120 (1892). {1MCP 183.4} 1MCPAmh 151.1
ክርስቶስ በፍጹም በጠንካራ ስሜት የሚሸነፍ አልነበረም።--ክርስቶስ በሕይወቱ የራሱን መለኮታዊ ትምህርቶች ፈጽሞአል። ቅናቱ በጠንካራ ስሜት ወደ መሸነፍ በፍጹም አልመራውም። ያለ ግትርነት አለመለዋወጥን፣ ያለ ድክመት ቸርነትን፣ ያለ ይሉኝታ ደግነትንና ርኅራኄን አሳየ። በከፍተኛ ሁኔታ ማህበራዊ ግንኙነት ነበረው፤ ሆኖም ተገቢ ያልሆነ ትውውቅን የማያደፋፍር ቁጥብነትና ክብሩን የመጠበቅ ባሕርይ ነበረው። መሻቱን መግዛቱ ወደ አክራርነትና ወደ ኮምጫጫነት በፍጹም አልመራውም። ይህን ዓለም የሚመስል አልነበረም፤ ሆኖም ከሰዎች መካከል ከሁሉ ለሚያንሰው ሰው ፍላጎት እንኳን ግድ የለሽ አልነበረም። የሁሉንም ፍላጎት ለማሟላት ንቁ ነበር። --MS 132, 1902. (Ev 636.) {1MCP 184.1} 1MCPAmh 151.2
ምክንያታዊ ባልሆነ ጥላቻ የተሞሉ አእምሮዎችን የመጋፈጥ ስልት።--የእርሱ የምህረት መልእክቶች ለአድማጮቹ ገጣሚ ሊሆኑ በሚችሉበት ሁኔታ የተለያዩ ነበሩ። ‹‹የደከመውን በቃል እንዴት እንደሚደግፍ›› ያውቅ ነበር (ኢሳ. 50፡ 4)፤ ለሰዎች እጅግ ሊስብ በሚችል መልኩ የእውነትን ሀብቶች ማስተላለፍ እንዲችል ጸጋ በከናፍሩ ላይ ፈሶ ነበር። ያለ ምክንያት በጥላቻ የተሞሉ አእምሮዎችን የሚገናኝበትና ትኩረታቸውን የሳቡትን መግለጫዎች በመስጠት የሚያስደንቅበት ብልሃት ነበረው።--DA 254 (1898). {1MCP 184.2} 1MCPAmh 151.3
ወደ ሰብአዊ ዋይታ ጥልቆች ደርሶ ነበር።--ነፍሳት እየጠፉ የነበሩበትን እያንዳንዱን መንገድ አቋርጦ ሄደ። ሰብአዊ ዘር እየተለማመደ የነበረውን የዋይታና የስቃይ ጥልቆችን ደረሰ። --Lt 50, 1897. {1MCP 184.3} 1MCPAmh 151.4
ሰይጣን በአእምሮ ላይ ያለውን ኃይል ይከላከላል።--እርሱ [ክርስቶስ] ሰይጣን በሰብአዊ አእምሮች ላይ ያለውን ኃይል--የማታለል ኃይል--ስለተመለከተ ወደዚህ ምድር ለመምጣት ተዘጋጀ [ራሱን በቃለ መሃላ አሰረ]። የንጉሥነት ልብሱን አስቀመጠ፣ የንጉስነት ዘውዱን አወለቀ፣ ከፍተኛ ሥልጣኑን ተወ፣ የሰማይ ሁሉ ዋና አዛዥ ከሆነበት ከክብር ዙፋኑ ወረደና ሰብአዊነት ሰብአዊነትን መንካት እንዲችል መለኮታዊነቱን ሰብአዊነትን አለበሰው። ወደዚህ የመጣበት ምክንያት ይህ ነበር። ቀጥታ ወደ ምድራችን የወረደው በራሱ ላይ የሰው ተፈጥሮን ለመቀበል፣ በችግሮች ሁሉ ውስጥ ለማለፍ፣ ሰውን በሚገጥሙ ሥቃዮችና ፈተናዎች ውስጥ በማለፍ አሳፋሪ የሆነውን የአዳምን አለመቻልና ውድቀት ለመዋጀት ስለነበር በዚህ አዳም በወደቀበት ቦታ በማለፍ ከእነዚህ ፈተናዎች ጋር ታገለ። {1MCP 184.4} 1MCPAmh 151.5
በሰብአዊ ተፈጥሮ፣ እንደ ምትካችን፣ እንደ ዋስ ጠበቃችን፣ እኛ እንድንጨብጠው ዕድሉ የተሰጠንን ተስፋ ጨበጠ፣ ያም የተለሌ ኃይል ነው። በዚህ አማካይነት አዳኛችን የጠላትን ፈተናዎች በማሸነፍ ድልን ተቀዳጀ። ለማን ብሎ? ለምን በእኛ ፋንታ፣ ለምን? ወደ ዘላለም ሕይወት በሚመራው መንገድ ላይ ከሰብአዊ ቤተሰብ አባላት መካከል አንድ ሰው እንኳን እንዳይደናቀፍ ነው። በዚህ መንገድ ላይ እርሱ ከፊታችን ስለተጓዘበት እያንዳንዱን እንቅፋት ያውቃል፣ በምድር ፊት ላይ ያለ እያንዳንዱ ነፍስ ሊጋፈጥ ያለውን እያንዳንዱን ችግር ያውቃል። ይህን ስለሚያውቅ በጥምቀቱ ጊዜ፣ ልመናውን ወደ ሰማይ ባቀረበ ጊዜ፣ ያ ጸሎት በአንተ መንገድ ላይ፣ በእኔ መንገድ ላይ፣ ተዘርግቶ የነበረውን የሰይጣንን ገሃነማዊ ጥላ ሰነጠቀውና እምነት ‹‹በመጋረጃው ውስጥ ወዳለው›› ገባ (ዕብራውያን 6፡ 19)።--MS 12, 1895. {1MCP 185.1} 1MCPAmh 152.1
ፈላጊውን እምነቱን እንዲለማመድ ይረዳል።--ክርስቶስ እያንዳንዱን የአእምሮዋን ሀሳብ ስላወቀ [ልብሱን የነከችውን ሴት] እርሷ ወደ ቆመችበት እያመራ ነበር። ትልቁን ፍላጎቷን ስለተገነዘበ እምነቷን እንድትለማመድ እየረዳት ነበር። --MH 60 (1905). {1MCP 185.2} 1MCPAmh 152.2
መለኮታዊ እውቀት ሰብአዊ እውቀት ሊሆን ይችላል።--እያንዳንዱ አገልጋይ የክርስቶስን ትምህርት ባሕርይ በቅርበት ማጥናት አለበት። የእርሱን ትምህርቶች መቀበል አለባቸው። የክርስቶስን አገልግሎት ውበት፣ እርግጠኛ የሆነውን ዓላማ የሚያስተውሉ ከሃያ ሰዎች አንድ እንኳን አይሆኑም። ፈልገው ማግኘት አለባቸው። ያኔ የእርሱ ትምህርቶች መልካም ፍሬ ተካፋዮች ይሆናሉ። ከራሳቸው ሕይወት ጋር ሙሉ በሙሉ ይሸምኑአቸውና ክርስቶስ በትምህርቶቹ ውስጥ ያመጣቸው ሀሳቦችና መርሆዎች እነርሱ በሚያስተምሩት ትምህርት ውስጥ እንዲመጣ ይለማመዱታል። እውነት ያብብና የከበረውን ዓይነት ፍሬ ያፈራል። የሰራተኛው ልብ ይሞቃል፤ በሌሎች ሰዎች አእምሮ ውስጥ በሚያሰርጹት ሕይወት ሰጭ በሆነ መንፈሳዊ ሕይወት ይቀጣጠላል። --MS 104, 1898. {1MCP 185.3} 1MCPAmh 152.3
የተለያዩ አእምሮዎችን ለመገናኘት።--የእግዚአብሔር ልጆች ነን የሚሉ ሁሉ እንደ ሚስዮናውያን ከሁሉም የአእምሮ ክፍሎች ጋር ግንኙነት እንደሚፈጥሩ ማወቅ አለባቸው። የተሞረዱና ሸካራ የሆኑ፣ ትሁታንና ትዕቢተኞች፣ ኃይማኖታውያንና ተጠራጣሪዎች፣ የተማሩና ያልተማሩ፣ ድሆችና ሀብታሞች አሉ። እነዚህ የተለያዩ አእምሮዎች በተመሳሳይ ሁኔታ አይያዙም፤ ሆኖም ሁሉም ደግነትንና ርኅራኄን ይሻሉ። በጋራ ግንኙነት የእኛ አእምሮዎች መወልወልና መሞረድ አለባቸው። በሰብአዊ ወንድማማችነት በቅርበት የተሳሰርን ስለሆንን አንዳችን በሌላችን ላይ እንደገፋለን። --MH 495, 496 (1905). {1MCP 186.1} 1MCPAmh 153.1
አእምሮ ከእርሱ አእምሮ ጋር አንድ እንዲሆን።--ራሳችንን ለክርስቶስ ስናስገዛ፣ ልብ ከእርሱ ልብ ጋር አንድነት ይፈጥራል፣ ፈቃድ ከእርሱ ፈቃድ ጋር ይዋሃዳል፣ አእምሮ ከእርሱ አእምሮ ጋር አንድ ይሆናል፣ ሀሳቦች ለእርሱ ምርኮኛ ይሆናሉ፤ የእርሱን ሕይወት እንኖራለን። በእርሱ የጽድቅ ልብስ መሸፈን ማለት ይህ ነው። ያኔ ጌታ እኛን ሲመለከት የሚያየው የበለስን-ቅጠል-ልብስ ሳይሆን፣ የኃጢአትን እራቁትነትና ቅርጸ-ቢስነትን ሳይሆን፣ ለያህዌህ ሕግ ፍጹም መታዘዝ የሆነውን የራሱን የጽድቅ ልብስ ነው። --COL 312 (1900). {1MCP 186.2} 1MCPAmh 153.2