አእምሮ፣ባሕርይና ማንነት፣ክፍል 1

17/45

ምዕራፍ 15—ስሜትን የሚቀሰቅሱ (የሚነኩ) ነገሮች

እግዚአብሔርን መታዘዝ ጥልቅ ከሆነ ስሜትና ምኞት ነጻ ያወጣል።--እግዚአብሔርን መታዘዝ ከኃጢአት ባርነት፣ ከሰብአዊ ጥልቅ ስሜትና ምኞት ነጻ መውጣት ነው። ሰው ራሱን ሊያሸንፍ ይችላል፣ የራሱን ዝንባሌዎች ሊያሸንፍ ይችላል፣ ሥልጣናትንና ኃይላትን፣ ‹‹በዚህ ዓለም ጨለማ የሚገዙ ገዥዎችን›› እና ‹‹ከፍ ባለ ስፍራ ያለውን መንፈሳዊ ክፋት›› ማሸነፍ ይችላል። --MH 131 (1905). {1MCP 123.1} 1MCPAmh 102.1

ስሜቶች በፈቃድ ቁጥጥር ሥር መሆን አለባቸው። [‹‹ውሳኔና ፈቃድ›› በሚለው መጽሐፍ ገጽ 76ን ይመልከቱ]--የአንተ ድርሻ ፈቃድህን በክርስቶስ ወገን ማድረግ ነው። ፈቃድህን ለፈቃዱ ስታስገዛ እርሱ ወዲያውኑ ይቆጣጠርህና የእርሱን መልካም ደስታ ለመፈጸም ፈቃደኛ እንድትሆን በውስጥህ ይሰራል። ሀሳብህ ሳይቀር ለእርሱ ይገዛል። {1MCP 123.2} 1MCPAmh 102.2

ውስጣዊ ግፊቶቻችሁንና ስሜቶቻችሁን እንደምትፈልጉት መቆጣጠር ከቻላችሁ፣ ፈቃድን መቆጣጠር ስለምትችሉ በሕይወታችሁ ሙሉ ለውጥ ይፈጸማል። ፈቃዳችሁን ለክርስቶስ ስታስገዙ ሕይወታችሁ ከክርስቶስ ጋር በእግዚአብሔር ውስጥ ይሰወራል። ከኃይላትና ሥልጣናት ሁሉ በላይ ከሆነው ኃይል ጋር ወዳጅነት ይፈጥራል። ከእርሱ ብርታት ጋር የሚያገናኝ ብርታት ከእግዚአብሔር ያገኛል፤ አዲስ ሕይወት፣ ያውም የእምነት ሕይወት፣ የሚቻላችሁ ይሆናል።--CTBH 148 (ML 318.) {1MCP 123.3} 1MCPAmh 102.3

ስሜቶች በግንዛቤና በህሊና ቁጥጥር ሥር ሲሆኑ።--በእያንዳንዱ ችግር ውስጥ ለማቆየትና ለማጽናናት የእውነት ኃይል በቂ መሆን አለበት። የክርስቶስ ኃይማኖት ትክክለኛ ዋጋውን የሚያሳየው ባለቤቱ በመከራ ላይ አሸናፊ እንዲሆን በማስቻል ነው። የምግብ ፍላጎቶችንና ኃይለኛ ስሜቶችን በግንዛቤና በህሊና ቁጥጥር ሥር በማድረግ ሀሳብ ጤናማ በሆነ መስመር እንዲፈስ ሥነ-ሥርዓት ያስይዛል። ከዚያም ምላስ ኃጢአተኛ በሆነ የብስጭት አገላለጾች እግዚአብሔርን እንዲያዋርድ አይተውም። --5T 314 (1885). {1MCP 124.1} 1MCPAmh 102.4

የእግዚአብሔርን ፈቃድ መፈጸም ከስሜትና ከውስጣዊ ስሜቶቻችን ጋር ሲነጻጸር።--የእግዚአብሔር ልጅ የሚያደርጉህ የሚሰሙህ ነገሮች ወይም ውስጣዊ ጥልቅ ስሜቶችህ ሳይሆኑ የእግዚአብሔርን ፈቃድ መፈጸምህ ነው። ፈቃድህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ከሆነ ጠቃሚ የመሆን ሕይወት ከፊትህ ነው። ያኔ እግዚአብሔር በሰጠህ ማንነትህ፣ የመልካም ሥራዎች ምሳሌ ሆነህ ትቆማለህ። {1MCP 124.2} 1MCPAmh 102.5

ያኔ የድስፕሊን ደንቦች እንዲጣሱ ከመርዳት ይልቅ እንዲጠበቁ ትረዳለህ። በራስህ ድርጊት ሥርዓትን ከመናቅና ሕገ ወጥነትን ከማነሳሳት ይልቅ እንዲጠበቅ ትረዳለህ። {1MCP 124.3} 1MCPAmh 103.1

በእግዚአብሔር ፍርሃት እነግራችኋለሁ፡- ፈቃዳችሁ በእግዚአብሔር ወገን ቢሆን ምን እንደምትሆኑ አውቃለሁ። ‹‹ከእግዚአብሔር ጋር አብረን ሠራተኞች ነን›› (1 ቆሮ. 3፡ 9)። ሥራችሁ የፍርድ ፈተናን ማለፍ በሚችልበት ሁኔታ ለአሁንና ለዘላለም እየሰራችሁ ሊሆን ይችላል። ትሞክሩታላችሁን? አሁኑኑ ወደ ኋላ ትመለሳላችሁን? የክርስቶስ ፍቅርና ምልጃ ግብ እናንተ ናችሁ። የእግዚአብሔርን ሥራ ለመጠበቅ እንደ ዘብ ሆነው የተቀመጡትን ከማሳዘንና ተስፋ ከማስቆረጥ ይልቅ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አሳልፋችሁ ሰጥታችሁ እነዚያን የእግዚአብሔር ሥራ ጠባቂዎች ትረዳላችሁን? --5T 515, 516 (1889). {1MCP 124.4} 1MCPAmh 103.2

መቅበጥበጥና አለመርካት ተለወጠ (በሚዛን ላይ ላለ ሰው የተሰጠ መተማመኛ)።-ክርስቶስን እንደ ግል አዳኝህ አድርገህ ለመቀበል ስትመጣ በአንተ ውስጥ የሚታይ ለውጥ ይከሰታል፤ ትለወጣለህ፣ ጌታ ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ከጎንህ ይቆማል። ከዚህ በፊት የነበረህ እረፍት የለሽ ምቾት ማጣትና አለመርካት አይኖሩም። {1MCP 124.5} 1MCPAmh 103.3

መናገር ትወዳለህ። ቃላቶችህ እግዚአብሔርን የሚያስከብሩ ዓይነት ቢሆኑ ኖሮ ኃጢአት አይኖርብህም ነበር። ነገር ግን በእግዚአብሔር አገልግሎት ውስጥ ሰላምን፣ እረፍትንና ደስታን አትገነዘብም። በእርግጠኝነት የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማድረግ የተለወጥክ ሰው አይደለህም፤ ስለዚህ ደስታ የሚሰጠውና የሚያደምቀው የእርሱ መንፈስ ቅዱስ ተጽእኖ ሊሰማህ አይችልም። {1MCP 125.1} 1MCPAmh 103.4

ክርስቲያን መሆን እንደማትችልና አሁንም ደስ ያለህን ነገር ለማድረግ ስትወስን፣ ፈቃድህን ለእግዚአብሔር ፈቃድ ማስገዛት እንዳለብህ ስትገነዘብ፣ ያኔ ከክርስቶስ ግብዣ ጋር ትስማማለህ፣ ‹‹እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፣ ወደ እኔ ኑ፣ እኔም እረፍት እሰጣችኋለሁ። ቀንበሬን በለያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፤ እኔ የዋህ በልቤም ትሁት ነኝና፣ ለነፍሳችሁም እረፍት ታገኛላችሁ። ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና›› (ማቴ. 11፡ 28-30)።--MS 13, 1897. {1MCP 125.2} 1MCPAmh 103.5

የውስጥ ስሜቶችን መቆጣጠር።--ሀሳቦቻችሁን እንኳን ለክርስቶስ ፈቃድ ብታስገዙ ኖሮ ደስተኛ መሆን ትችሉ ነበር። ሳትዘገዩ ልባችሁን በቅርበት በመመርመር ለራስ በየቀኑ ሙቱ። {1MCP 125.3} 1MCPAmh 104.1

እንዲህ ብላችሁ ትጠይቁ ይሆናል፡- እንዴት አድርጌ ነው ድርጊቴን ማሸነፍ የምችለውና የውስጥ ስሜቶችን መቆጣጠር የምችለው? {1MCP 125.4} 1MCPAmh 104.2

የእግዚአብሔር ፍቅር የሌላቸው ብዙዎች ልዩ የሆነ የእግዚአብሔር ፀጋ እርዳታ ሳይኖራቸው በከፍተኛ ደረጃ መንፈሳቸውን ይቆጣጠራሉ። ራስን መቆጣጠርን ያሳድጋሉ። ይህ ከእግዚአብሔር ብርታትንና ጸጋን እንደሚያገኙ ለሚያውቁና የመንፈስን ጸጋዎች ለማያሳዩ ተግሳጽ ነው። ክርስቶስ ምሳሌያችን ነው። እርሱ የዋህና ትሁት ነው። ከእርሱ ተማሩ፣ የእርሱን ምሳሌ ቅዱ። የእግዚአብሔር ልጅ ስህተት የለሽ ነበር። ከእርሱ በቀኝ በኩል መቀመጥ ከፈለግን ወደዚህ ፍጽምና ማነጣጠርና እርሱ እንዳሸነፈ ማሸነፍ አለብን።--3T 336 (1873). {1MCP 125.5} 1MCPAmh 104.3

ስሜቶች እንደ ደመና ተለዋዋጭ ናቸው።--እንደ ነጻን እስኪሰማን ድረስ መጠበቅ አለብን ወይ? አይደለም፤ ክርስቶስ እንዲህ በማለት ቃል ገብቶልናል፡- ‹‹በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከአመጻም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው›› (1 ዮሐ. 1፡ 9)። እግዚአብሔር የሚፈትናችሁ በቃሉ አማካይነት ነው። እግዚአብሔር እንደ ሰማችሁ ከማመናችሁ በፊት አስደናቂ የሆኑ ስሜቶች እንዲፈጠሩ አትጠብቁ፤ ስሜቶች እንደ ደመና ተለዋዋጭ ስለሆኑ ስሜት መስፈርታችሁ መሆን የለበትም። ለእምነታችሁ መሰረት እንዲሆን የሆነ ጽኑ ነገር ሊኖራችሁ ይገባል። የእግዚአብሔር ቃል ልትተማመኑበት የምትችሉበት ዘላለማዊ ኃይል ያለው ቃል ነው፣ እርሱ ራሱ ‹‹ጠይቁ ይሰጣችኋል›› ብሎአል። ወደ ቀራኒዮ ተመልከቱ። ኢየሱስ ጠበቃችሁ ነኝ አላለምን? ምንም ነገር በስሙ ብትጠይቁ ትቀበላላችሁ አላለምን? በራሳችሁ መልካምነት ወይም መልካም ሥራ መደገፍ የለባችሁም። በጽድቅ ፀሐይ በመደገፍ፣ ክርስቶስ ኃጢአታችሁን እንዳስወገደላችሁና የራሱን ጽድቅ እንደሰጣችሁ በማመን መምጣት አለባችሁ።--ST, Dec. 12, 1892. (1SM 328.) {1MCP 126.1} 1MCPAmh 104.4

ስሜቶች እርግጠኛ የሆኑ ከአደጋ ጠባቂዎቻችን አይደሉም። ስሜቶች ብዙ ጊዜ አሳሳች ናቸው፣ ስሜቶች የተለያዩና ለውጫዊ ሁኔታዎች ተገዥ ስለሆኑ እርግጠኛ የሆኑ ከአደጋ ጠባቂዎች አይደሉም። ብዙዎች ስሜትን በሚያነሳሱ አስተያየቶች ከመደገፋቸው የተነሣ ተታለዋል። መፈተኛው፡- ለክርስቶስ ምን እያደረግክለት ነው? የሚለው ነው። ምን መስዋዕትነቶች እየከፈላችሁ ናችሁ? ምን ድሎችን እያገኛችሁ ናችሁ? ያሸነፍከው የራስ ወዳድነት መንፈስ፣ የተቋቋምከው ተግባርን ችላ የማለት ፈተና፣ ያሸነፍከው ስሜት፣ ለክርስቶስ ፈቃድ በፈቃደኝነትና በደስታ ያቀረብከው መታዘዝ፣ አልፎ አልፎ ከሚታይ አምልኮና ከስሜታዊ ኃይማኖት ይልቅ የእግዚአብሔር ልጅ ለመሆንህ እጅግ የሚበልጡ ማስረጃዎች ናቸው። --4T 188 (1876). {1MCP 126.2} 1MCPAmh 104.5

ክርስቲያን የስሜቶች ተገዥ መሆን የለበትም።--የእግዚአብሔር ልጆች ለስሜቶች ተገዥ መሆን የለባቸውም። በተስፋና በፍርሃት መካከል በሚዋዥቁበት ጊዜ የክርስቶስ ልብ ያዝናል፤ ይህ የሚሆነው ሊሳሳት የማይችል የፍቅሩን ማረጋገጫ ስለሰጣቸው ነው።…እርሱ የሰጣቸውን ሥራ እንዲሰሩ ይፈልግባቸዋል፤ ያኔ ልባቸው የዓለምን ኃጢአት እንዲያስወግድ በእግዚአብሔር ለተላከው ውዳሴንና ምስጋናን ለማፍለቅ በእጁ ላይ እንዳሉ ቅዱስ በገናዎች ይሆናሉ።--Lt 2, 1914. (TM 518, 519.) {1MCP 126.3} 1MCPAmh 105.1

ክርስቶስ የተፈጥሮ ዝንባሌዎችን እንድናሸንፍ (እንድንቆጣጠር) ኃይል ይሰጠናል።--ሰው ነፍስን የሚያበላሹ የተፈጥሮ ዝንባሌዎችን ፍጹም ማሸነፍ እንዲችል ለማድረግ ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም መጥቶ የእግዚአብሔርን ሕግ በመታዘዝ ኖረ። የነፍስና የአካል ሐኪም በሚዋጉን ፍትወቶች ላይ ድልን ይሰጠናል። ሰው የባሕርይ ፍጽምናን ያገኝ ዘንድ የሚያስፈልገውን እያንዳንዱን ነገር ሰጥቷል። --MH 130, 131 (1905). {1MCP 127.1} 1MCPAmh 105.2

ጥልቅ የሆነ የደስታ ስሜት የመለወጥ ማስረጃ አይሆንም።--ጥልቅ የሆነ የደስታ ስሜት ስለ ተሰማቸው ተለውጠናል ብለው እንዲያስቡ ሰይጣን ሰዎችን ይመራል። ነገር ግን ልምምዳቸው አይለወጥም። የሚያደርጉአቸው ነገሮች ከዚህ በፊት ከነበረው ጋር ተመሳሳይ ናቸው። ሕይወታቸው መልካም ፍሬ አያሳይም። ብዙ ጊዜ እና ለረዥም ሰዓት ስለሚጸልዩ በዚህ ሰዓት ከዚህ በፊት የነበራቸውን ስሜት ያለማቋረጥ ይጠቅሳሉ። ነገር ግን አዲስ ሕይወት አይኖሩም። ተታለዋል። ልምምዳቸው ከስሜት ያለፈ ጥልቀት የለውም። በአሸዋ ላይ እየገነቡ ስለሆነ ክፉ ንፋስ ሲመጣ ቤታቸው ተጠራርጎ ይወሰዳል። --YI, Sept. 26, 1901. (4BC 1164.) {1MCP 127.2} 1MCPAmh 105.3

አንዳንድ ጊዜ ያለማረፍ ስሜቶች ጥሩ ናቸው።--እረፍት የማጣትና ቤትን የመናፈቅ ወይም የብቸኝነት ስሜቶች ሊጠቅሙአችሁ ይችላሉ። ሰማያዊው አባታችሁ ይህ እንዲሆን የሚፈቅደው እጅግ ጥልቅ የሆኑ ተስፋዎቻችሁንና ፍላጎቶቻችሁን የሚያረካውን ጓደኝነት፣ ፍቅርና መጽናኛ በእርሱ እንድታገኙ ነው።…ደህንነትና ደስታ ሊገኝ የሚችልበት ብቸኛው መንገድ ክርስቶስን የሁልጊዜ አማካሪያችሁ ማድረግ ነው። በመላው ዓለም አንድ ጓደኛ እንኳን ባይኖራችሁ በእርሱ ደስተኛ መሆን ትችላላችሁ። --Lt 2b, 1874. (HC 259.) {1MCP 127.3} 1MCPAmh 105.4

እግዚአብሔር አእምሮዎችን መረበሽ ይፈልጋል።--ሰዎች በዓለማዊ ችግሮችና በንግድ ውዝግቦች እጅግ ከመመሰጣቸው የተነሣ ከእርሱ ጋር ለመተዋወቅ ጊዜ እንደሌላቸው ክርስቶስ ይመለከታል። ሰማይን ከግምታቸው ውስጥ ስላስወጡ ለእነርሱ ሰማይ እንግዳ ስፍራ ነው። ከሰማያዊ ነገሮች ጋር በደንብ ትውውቅ ስለሌላቸው ስለ እነርሱ መስማት ይሰለቻቸዋል። በጊዜያዊ መደሰቻዎች ላይ መጠመድን ስለሚመርጡ ድነት እንደሚያስፈልጋቸው በሚገልጹ ነገሮች አእምሮዎቻቸው ሲረበሹ ይጠላሉ። ነገር ግን ዘላለማዊ እውነቶችን እንዲጨብጡ ስለሚፈልግ እግዚአብሔር አእምሮዎቻቸውን መረበሽ ይፈልጋል። ከእርሱ ጋር ጽኑ ግንኙነት እንዲኖራቸው ይፈልጋል። እርሱን ለማወቅ ቢፈልጉም ባይፈልጉም በቅርቡ ሁሉም ያውቁታል።--MS 105, 1901. {1MCP 128.1} 1MCPAmh 106.1

ስሜቶችን በተመለከተ ራስን በማጥናት መመሰጥ የለብንም።--ወደ ራሳችን መመልከትና ስሜቶቻችንን ማጥናት ጠቢብነት አይደለም። ይህን ካደረግን ጠላት እምነትን የሚያደክሙና ድፍረትን የሚያጠፉ ችግሮችንና ፈተናዎችን ያቀርባል። ስሜቶቻችንን በቅርበት ማጥናትና ለሚሰሙን ነገሮች መንገድ መስጠት ጥርጣሬን ማስተናገድና ራሳችንን ግራ በመጋባት ገመድ ማጠላለፍ ነው። ዓይኖቻችንን ከራሳችን አንስተን ኢየሱስን መመልከት አለብን።--MH 249 (1905). {1MCP 128.2} 1MCPAmh 106.2