አእምሮ፣ባሕርይና ማንነት፣ክፍል 1
ምዕራፍ 10—መረዳት
ነገሮችን መረዳትንና ለይቶ ማወቅን የሚሻ ሥራ።-- ከአእምሮ ጋር የሚሰራ ሥራ ለሟች ሰዎች ተሰጥቶ ከሚያውቅ ሥራ ሁሉ እጅግ ጥሩና ወሳኝ ሥራ ነው። በዚህ ሥራ የሚሳተፉ ሰዎች የጠራ መረዳትና ጥሩ የሆኑ ነገሮችን ለይቶ የማወቅ ኃይል ይኖራቸዋል።-- {1MCP 78.1} 1MCPAmh 66.1
እውነተኛ የሆነ የአእምሮ ጥገኛ አለመሆን ነገሮችን በጥድፊያ ከማድረግ ሙሉ በሙሉ የተለየ ነው። ወደ ጥንቃቄ፣ ወደ መጸለይና ሆን ተብሎ ታስቦበት ወደሚደረግ አመለካካት የሚመራ ጥገኛ ያለመሆን ሁኔታ ስህተት መሆናችንን የሚያረጋግጥ ጠንካራ የሆነ ማስረጃ እስከሌለ ድረስ በቀላሉ መተው የለበትም። ይህ ጥገኛ አለመሆን እየታዩ ባሉ ቁጥር ስፍር በሌላቸው ስህተቶች ውስጥ አእምሮን የተረጋጋና የማይለዋወጥ ያደርጋል፤ እንዲሁም በሀላፊነት ቦታ ላይ የተቀመጡትን በሁሉም ወገን ያለውን መረጃ በጥንቃቄ እንዲመለከቱ እንጂ ባለማስተዋልና ለሁሉም ሁኔታዎች በቂ ግንዛቤ ሳይኖር ወደ ድምዳሜ ላይ በመድረስ በሌሎች ተጽእኖ ወይም በዙሪያቸው ባሉ ነገሮች ተጽእኖ ወዲያና ወዲህ እንዳይዋልሉ ያደርጋል። --3T 104, 105 (1872). {1MCP 78.2} 1MCPAmh 66.2
ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚሻ ሥራ።--ሰው የእግዚአብሔርን የከበረ ልጅ ዋጋ እስከማስከፈል ሰማይን ከፍተኛ ወጪ እስከጠየቀ ድረስ አገልጋዮች፣ መምህራንና ወላጆች በእኛ ተጽእኖ ሥር ያሉ ነፍሳትን ምን ያህል በጥንቃቄ መያዝ እንዳለብን ማወቅ አለብን። ከአእምሮዎች ጋር መሥራት ጥሩ ነገር ሲሆን ወደ ሥራው መገባት ያለበት በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ ነው። {1MCP 78.3} 1MCPAmh 66.3
የወጣቶች መምህራን ፍጹም የሆነ ራስን መቆጣጠር ሊኖራቸው ይገባል።--ትዕግስት ከማጣት የተነሣ ወይም ያልተገባ ስብዕናና የበላይነትን ለማስጠበቅ ሲባል በሰብአዊ ነፍስ ላይ ያለውን ተጽእኖ ማጥፋት ለክርስቶስ ሊሆን የሚችለውን ያን ነፍስ ማጣት ስለሚሆን አስከፊ ስህተት ነው። ጥበብ ከጎደለው አያያዝ የተነሣ የተከሰተውን ጉዳት በፍጹም ሙሉ በሙሉ ማሸነፍ እስከማይቻል ድረስ የወጣቶች አእምሮ ሊጣመም ይችላል። በወጣቶች ትምህርትና ስልጠና ላይ የክርስቶስ ኃይማኖት የመቆጣጠር ተጽእኖ ሊኖረው ይገባል።--{1MCP 79.1} 1MCPAmh 66.4
አዳኙ ያሳየው ራስን የመካድ፣ ለሁሉም ደግ የመሆን እና ትዕግስተኛ ፍቅርን የማሳየት ምሳሌ ትዕግሥት ለሌላቸው አገልጋዮችና መምህራን ተግሳጽ ነው። እነዚህን ስሜታዊ መምህራን እንዲህ ብሎ ይጠይቃቸዋል፡- ‹‹እኔ ሕይወቴን አሳልፌ የሰጠኋቸውን ሰዎች የምትይዙት በዚህ ሁኔታ ነውን? ለእነርሱ ድነት ለከፈልኩት ዘላለማዊ ዋጋ ትልቅ አድናቆት የላችሁምን?›› --4T 419 (1880). {1MCP 79.2} 1MCPAmh 66.5
ሐኪም ከሁሉም የአእምሮ አይነቶች ጋር ግንኙነት ያደርጋል።--ዶክተር በየቀኑ በእውቀት ክምችቱ ላይ ለመጨመርና ትህትናንና የተሞረደ ባሕርይን ለማሳደግ መሻት አለበት።…ከሁሉም የአእምሮ ዓይነቶች ጋር ግንኙነት ስለሚፈጥር እርሱ የሚያሳርፋቸው አሻራዎች ወደ ሌሎች ግዛቶችም ስለሚዛመት ውጤቱ በተቋሙ ላይ ይንጸባረቃል [የባትል ክሪክ ጤና ማሰልጠኛ ማዕከል]። --3T 183, 184 (1872). {1MCP 79.3} 1MCPAmh 67.1
ትዕግስትና ጥበብ ያስፈልጋል።--አገልጋዮች ገና በስህተት ጨለማ ውስጥ እየዳከሩ (በዳበሳ እየሄዱ) ካሉት ሰዎች ብዙ ከመጠበቅ መጠንቀቅ አለባቸው። ያለ መንፈስ ቅዱስ ተጽእኖ ልፋታቸው እንደማይሳካ በማወቅ፣ ለሚጠይቁት አእምሮዎች ምስጢራዊና የሚያንቀሳቅሰውን የእርሱን መንፈስ ተጽእኖ እንዲሰጥ በእግዚአብሔር በመደገፍ ሥራቸውን በደንብ መሥራት አለባቸው። ከአእምሮዎች ጋር በሚሰሩበት ጊዜ በግለሰቦች ውስጥ ያሉትን እነዚህን የተለያዩ ዓይነት ባሕርያት ያሳደጉ ሁኔታዎች ብዙ መሆናቸውን በማሰብ ታጋሾችና ጠቢባን መሆን አለባቸው። ራስ የበላይነትን አግኝቶ ኢየሱስ ከጥያቄ ውጭ እንዳይሆን ራሳቸውን በጥብቅ መጠበቅ አለባቸው። --GW 381 (1915). {1MCP 79.4} 1MCPAmh 67.2
የክርስቶስ ፍቅር ያሸንፋል።--ልብን የሚያነብ እርሱ ብቻ ሰዎችን እንዴት ወደ ንስሃ እንደሚያመጣ ያውቃል። የጠፉትን በመድረስ ሂደት የእርሱ ጥበብ ብቻ ስኬትን ይሰጠናል። ‹‹እኔ ከአንተ ይልቅ ጻድቅ ነኝ›› የሚል ስሜት ስላለህ ቀጥ ብለህ ልትቆም ትችላለህ፤ የምታቀርበው ምክንያት ምን ያህል ትክክል መሆኑ ወይም ቃላትህ ምን ያህል እውነት መሆናቸው ልዩነት አያመጣም፤ በፍጹም ልቦችን አይነኩም። መመሪያዎችን ደጋግሞ መናገር ወይም ክርክር ምንም ነገር ማድረግ ሲያቅተው በቃልና በተግባር የተገለጠ የክርስቶስ ፍቅር አሸንፎ ወደ ነፍስ ይደርሳል። --MH 163 (1905). {1MCP 79.5} 1MCPAmh 67.3
በርኅራኄና በፍቅር።--የተሳሳቱትን ለማረም ሁሉም ገጣሚዎች አይደሉም። ምህረትን በመውደድ በፍትሃዊነት ለመስራት ጥበብ የላቸውም። ፍቅርንና ደግነት ያለበትን ርኅራኄ ታማኝነት ካለበት ተግሳጽ ጋር የመቀላቀልን አስፈላጊነት ለማየት ያዘነበሉ አይደሉም። አንዳንዶች ሁልጊዜም ከሚያስፈልገው በላይ ጥብቅ ስለሆኑ ሐዋርያው የሰጠው የጽሁፍ ምክር አስፈላጊነት አይሰማቸውም፡- ‹‹አንዳንዶቻችሁ ልዩነት ለማምጣት ርኅራኄ ይኑራችሁ፡- ሌሎቻችሁ ደግሞ ከእሳት ነጥቃችሁ በማውጣት በፍርሃት አድኑ›› (ይሁዳ 22፣ 23)። --3T 269, 270 (1873). {1MCP 80.1} 1MCPAmh 67.4
በጠንካራ ስሜት በቀላሉ የሚጠቃ ሰው ከአእምሮዎች ጋር መስራት የለበትም።--ጽኑ እምነት ማጣትና የተቀደሱ ነገሮችን የመገንዘብ እጦት ማንኛውንም ሰው ከእግዚአብሔር ሥራ ጋር ግንኙነት እንዳይኖረው ለመከልከል በቂ እንደሆኑ ተደርገው መወሰድ አለባቸው። ግልፍተኛ፣ አስቸጋሪ፣ የሌሎችን ሀሳብ የሚንቅ ባሕርይን መለማመድ የዚህ ባሕርይ ባለቤት የእግዚአብሔርን ቅርስ የሚነኩ ክብደት ያላቸው ጥያቄዎች ላይ ውሳኔ እንዲሰጥ በሚጠራበት ቦታ መቀመጥ የለበትም። {1MCP 80.2} 1MCPAmh 68.1
በጠንካራ ስሜት በቀላሉ የሚጠቃ ሰው ከሰብአዊ አእምሮዎች ጋር በሚሰራ ሥራ ላይ ምንም ድርሻ ሊኖረው አይገባም። ክርስቶስ በዘላለማዊ ዋጋ ከገዛቸው ሰዎች ጋር ግንኙነት ያላቸውን ነገሮች መልክ እንዲያስይዝ ሊታመን አይችልም። ሰዎችን የማስተዳደር ሥራ ቢሰጠው ይጎዳቸዋል፣ ነፍሶቻቸውንም ያቆስላል፤ ይህ የሚሆነው የክርስቶስ ጸጋ የሚያጋራው ትክክለኛ ንካትና ጥሩ ስሜት ስለሌለው ነው። የራሱ ልብ ለእግዚአብሔር መንፈስ ተገዝቶ መለስለስ አለበት፤ የድንጋይ ልብ የሥጋ ልብ አልሆነም። --SpT Series A, No. 5, p 18, 1896. (TM 261.) {1MCP 80.3} 1MCPAmh 68.2
አእምሮዎችን ለመረዳት የሚያስፈልጉ ችሎታዎች (ለጽሁፍ ወንጌላዊ የተሰጠ ምክር)።--ከሌሎች የሥራ ዘርፎች ይልቅ በዚህ ሥራ ውስጥ ብዙ ችግሮች አሉ፤ ነገር ግን በዚህ ሥራ ውስጥ የተማርካቸው ትምህርቶች፣ ያገኘሃቸው ስልቶችና ሥነ-ሥርዓቶች፣ ነፍሳትን ማገልገል ለምትችልባቸው ለሌሎች ጠቃሚ የሥራ መስኮች ገጣሚ ያደርጉሃል። ጥሩ ባልሆነ መንገድ ትምህርታቸውን የሚማሩና ወደ ግለሰቦች ሲቀርቡ ግድየለሾችና ግልፍተኞች የሆኑ ሰዎች ወደ አገልግሎት ቢገቡ ከአእምሮዎች ጋር ለመሥራት ስልትና ብልሃት ይጎድላቸዋል። --Manual for Canvassers, pp. 41, 42, 1902. (CM 34.) {1MCP 80.4} 1MCPAmh 68.3
ግብታዊነትን፣ ትዕግሥት የለሽነትን፣ ኩራትን እና ለራስ ከፍተኛ ግምት መስጠትን መጋፈጥ።--ከሰብአዊ አእምሮ ጋር መስራት ሟች ለሆነ ሰው ከተሰጡት ሥራዎች ሁሉ እጅግ ጥንቃቄ የሚፈልግ ስለሆነ መምህራን ሥራቸውን በትክክል መስራት እንዲችሉ ሁልጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። በትምህርት ቤት በሚማሩ ወጣቶች መካከል ትልቅ የባሕርይና የትምህርት ልዩነት ይኖራል። መምህር ግብታዊ፣ ትዕግስት የለሽ፣ ኩሩ፣ ራስ ወዳድና ለራስ ከፍተኛ ግምት ያላቸውን ተማሪዎች ሊገናኝ ይችላል። ከወጣቶቹ መካከል አንዳንዶቹ በውስጣቸው የግትርነትና የተቃውሞ መንፈስ እንዲጎለብት ባደረገ ጭፍን እቀባና ጭካኔ ውስጥ የኖሩ ናቸው። ሌሎቹ ደግሞ ከመጠን በላይ ፍቅር በሚያሳዩ ወላጆች እንደ ለማዳ አጫዋች እንስሳ (ብርቅዬ እንስሳ) ታይተው የራሳቸውን ዝንባሌ እንዲከተሉ የተፈቀደላቸው ናቸው። ባሕርይ እስኪጣመም ድረስ ስህተቶች ሳይታረሙ አልፈዋል። --CT 264 (1913). {1MCP 81.1} 1MCPAmh 68.4
ትዕግስት፣ ብልሃትና ጥበብ ያስፈልጋል።--መምህር ከእነዚህ የተለያዩ ዓይነት አእምሮዎች ጋር በተሳካ ሁኔታ ለመስራት ከፍተኛ የሆነ ብልሃትና ጥንቃቄ የተሞላ አያያዝ፣ እንዲሁም የአስተዳደር ጽናት ያስፈልገዋል። ብዙ ጊዜ ተገቢ ለሆኑ ቁጥጥሮች ጥላቻና ንቀት ሊገለጽ ይችላል። አንዳንዶች ቅጣትን ለማምለጥ የራሳቸውን ቅልጥፍና ሲጠቀሙ ሌሎች ደግሞ የህግ ጥሰት ለሚያስከትላቸው መዘዞች ግድየለሽነትን ያሳያሉ። ይህ ሁሉ እነዚህን ወጣቶች የማስተማር ሀላፊነት የተሰጣቸው ሰዎች ትዕግስት፣ መቻልና ጥበብ እንዲኖራቸው ይጠይቃል።--CT 264 (1913). {1MCP 81.2} 1MCPAmh 69.1
ሊድኑ የማይችሉ ጠባሳዎችንና ሰንበሮችን ትቶ የሚያልፍ አካሄድ።--መምህር በሚያስተምራቸው ሳይንሶች ላይ በቂ ትምህርትና እውቀት ሊኖረው ይችላል፣ ነገር ግን ከሰብአዊ አእምሮዎች ጋር ለመስራት ብልሃትና ጥበብ እንዳለው ተረጋግጦአልን? መምህራን የክርስቶስ ፍቅር በልባቸው ውስጥ ከሌለ፣ ወጣቶችን በሚያስተምሩ መምህራን ላይ የተጣለውን ከባድ ሀላፊነት ለመሸከም ገጣሚዎች አይደሉም። ለራሳቸው ከፍተኛ ትምህርት ስለሚጎላቸው ከሰብአዊ አእምሮ ጋር እንዴት እንደሚሰሩ አያውቁም። የራሳቸው ያልተገዙ ልቦች የበላይነትን ለመያዝ ጥረት እያደረጉ ናቸው፤ በቀላሉ ቅርጽ መያዝ የሚችሉ የልጆችን አእምሮዎችና ባሕርያት እንደዚህ ላለው ዲሲፕሊን ማስገዛት በአእምሮ ውስጥ ሊፋቁ የማይችሉ ጠባሳዎችንና ሰንበሮችን መተው ነው። --CT 193 (1913). {1MCP 81.3} 1MCPAmh 69.2
ነገሮችን ጥርት ባለ ሁኔታ ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል።--እግዚአብሔር በብዙ መንገዶችና በተለያዩ ጊዜያቶች ወጣቶችን እንዴት በጥንቃቄ መያዝ እንዳለብን፣ ከአእምሮዎች ጋር ለመሥራት ጥርት ባለ ሁኔታ ልዩነትን ማወቅ እንደሚያስፈልግ አሳይቶኛል። ከወጣቶች ትምህርትና ስልጠና ጋር የሚሰራ እያንዳንዱ ግለሰብ የእርሱን የሥራ መንፈስና ሁኔታ ለመያዝ ወደ ታላቁ መምህር ቀርቦ መኖር አለበት። ባሕርያቸውንና የሕይወት ስራቸውን የሚነኩ ትምህርቶች መሰጠት አለባቸው። --GW 333 (1915). {1MCP 82.1} 1MCPAmh 69.3
ግላዊ ማንነት አስፈላጊ ነው።--በሁሉም እውነተኛ ትምህርት ውስጥ ግላዊ ማንነት አስፈላጊ ነው። ክርስቶስ በትምህርቶቹ ውስጥ ከሰዎች ጋር የሰራው በግላቸው ነበር። አሥራ ሁለቱን ያሰለጠናቸው በግላዊ ግንኙነትና ሕብረት በመፍጠር ነበር። ከአንድ አድማጭ በስተቀር አብዛኛውን ጊዜ የእርሱን እጅግ የከበረ መመሪያ የሰጠው በግል ነበር። በደብረዘይት ተራራ ላይ ከአንድ የከበረ መምህር ጋር በማታ ውይይት እና በሲካር ጉድጓድ ለአንዲት የተናቀች ሴት እጅግ የከበሩ ሀብቶቹን ከፈተላቸው፤ ይህን ያደረገው በእነዚህ አድማጮች ውስጥ ሊነካ የሚችል ልብ፣ ክፍት አእምሮ፣ ተቀባይ የሆነ መንፈስ ስላየ ነበር። የእርሱን ዱካ ተከትሎ ይተም የነበረው ሕዝብም ቢሆን ለክርስቲያን ተለይቶ ሊታወቅ የማይችል የሰብአዊ ፍጡራን ክምችት አልነበረም። ለእያንዳንዱ አእምሮ በቀጥታ እየተናገረ ለእያንዳንዱ ልብ ተማጽኖ አቀረበ። እውነት ለነፍሳት እንደደረሰ የነበሩትን የአድማጮቹን ፊቶች ተመለከተ፣ የፊታቸውን መብራትና ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ እይታቸውን ተገነዘበ። በዚያ ቦታ፣ ምላሽ እንዲሆን ርኅራኄ ያለበት የደስታ ምት በልቡ ውስጥ አስተጋባ።--Ed 231 (1903). {1MCP 82.2} 1MCPAmh 69.4
ከመጠን በላይ መሥራት ከሌሎች ጋር ለመሥራት ገጣሚ እንዳትሆኑ ያደርጋል።--መምህራን የራሳቸውን ኃይሎች በተሻለ ሁኔታ ለመጠበቅና በቃልም ሆነ በሥራ በተማሪዎቻቸው ላይ ትክክለኛ ተጽእኖ ማሳደር እንዲችሉ ለጤና ሕጎች ተገቢ የሆነ ትኩረት መስጠት አለባቸው። የአካል ኃይሎቹ በበሽታ ወይም ከመጠን በላይ በመስራት የደከሙበት መምህር ለሕይወት ሕጎች የተለየ ትኩረት መስጠት አለበት። ለመዝናናት ጊዜ መውሰድ አለበት። ከትምህርት ቤት ሥራው ሌላ የነርቭ ስርዓት ሚዛን እስኪያጣ ድረስ አካልና አእምሮ በሥራ እንዲጠመድ የሚያደርግ ሀላፊነት መውሰድ የለበትም፤ በዚህ ሁኔታ ከአእምሮዎች ጋር ለመስራት የማይገጥም ስለሚሆን ለራሱም ሆነ ለተማሪዎቹ ተገቢ የሆነ ሥራ ሳይሰራ ይቀራል። --CTBH 83, 1890. (FE 147.) {1MCP 82.3} 1MCPAmh 70.1
የተለያዩ ፍላጎቶችን መረዳት።--በተቋማችን ውስጥ ያሉ ሀኪሞች እምነትና መንፈሳዊነት ያላቸው ወንዶችና ሴቶች መሆን እንዳለባቸው አሳይቶኛል። እግዚአብሔርን መታመኛቸው ማድረግ አለባቸው። በኃጢአተኛ አጠቃቀማቸው በራሳቸው ላይ እያንዳንዱን የበሽታ ዓይነት በማምጣታቸው ወደ ጤና ተቋም የሚመጡ ብዙዎች አሉ። {1MCP 83.1} 1MCPAmh 70.2
እነዚህ በተደጋጋሚ የሚጠይቁት የቡድን አባላት ሀዘኔታ የሚገባቸው አይደሉም። በአካል፣ በአእምሮና በግብረገብ ለወረዱት ለነዚህ የቡድን አባላት ጊዜንና ብርታትን ለይቶ ማስቀመጥ ለሀኪሞች ምቾት የማይሰጥ ነው። {1MCP 83.2} 1MCPAmh 70.3
ነገር ግን ካለማወቅ የተነሣ የተፈጥሮ ሕጎችን እየጣሱ የኖሩ ክፍሎች አሉ። መሻትን ሳይገዙ መስራትና መብላት ባሕላቸው ስለሆነ ይህን አድርገዋል። አንዳንዶች ከብዙ ሀኪሞች ብዙ ነገሮችን ተቀብለዋል፣ ነገር ግን ከመሻል ይልቅ የበለጠውን ከፍቶባቸዋል። በጊዜ ብዛት ከሥራቸው፣ ከማህበረሱ እና ከቤተሰቦቻቸው ተለይተዋል፤ እንደ መጨረሻ አማራጭ እፎይታ አገኝ ይሆን በሚል የደበዘዘ ተስፋ ወደ ጤና ተቋም ይመጣሉ። {1MCP 83.3} 1MCPAmh 70.4
እነዚህ ሰዎች ሀዘኔታ ያስፈልጋቸዋል። እጅግ በጣም ከፍተኛ በሆነ ጥንቃቄ መያዝ አለባቸው፣ እንዲሁም የአካላቸውን ሕጎች እንዲረዱት ግልጽ ለማድረግ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል። እነዚህን ሕጎች ከመጣስ በመቆጠብ እና ራሳቸውን በመምራት የተጣሰው የተፈጥሮ ሕግ ቅጣት ከሆነው ስቃይና በሽታ ያመልጣሉ። --3T 178 (1872). {1MCP 83.4} 1MCPAmh 71.1
እውነት ሁል ጊዜ የሚነገር አይደለም።--ወደ ዓለም ሕብረት የገቡ፣ ነገሮችን ዓለማውያን ካላቸው አመለካከት በመነሳት የሚመለከቱ ጥቂት ሰዎች ስለ ራሳቸው በተመለከተ የእውነታዎች መግለጫ በፊታቸው ቀርቦ ለማየት ተዘጋጅተዋል። እውነት እንኳ ሁልጊዜ መነገር የለበትም። ለመናገር ገጣሚ የሆነ ጊዜና እድል አለ፣ ያውም ቃላት የማያስቀይሙበት ጊዜ ነው። ሀኪሞች ከመጠን በላይ በመስራት ነርቮቻቸው መዛል የለባቸውም፤ የዚህ ዓይነት የአካል ሁኔታ ለተረጋጉ አእምሮዎች፣ ቀስ ብለው ለሚሰሩ ነርቮችና ደስተኛ ለሆነ መንፈስ ምቹ አይደለም። --3T 182 (1872). {1MCP 84.1} 1MCPAmh 71.2
ክርስቶስ ያስተውላል።--ሰብአዊነትን በራሱ ላይ የተቀበለው ለሰብአዊ ዘር ስቃይ እንዴት ሀዘኔታውን እንደሚገልጽ ያውቃል። ክርስቶስ እያንዳንዱን ነፍስ የሚያውቅ ብቻ ሳይሆን መንፈስን የሚያስጨንቁና ግራ የሚያጋቡ ሁኔታዎችን ሁሉ ያውቃል። የእርሱ እጅ ለእያንዳንዱ ለሚሰቃይ ልጅ ሀዘኔታ በተሞላበት ገርነት ተዘርግቷል። አብዝተው ለሚሰቃዩት እርሱ አብዝቶ ርኅራኄንና ሀዘኔታን ያሳያቸዋል። በእኛ ጉድለቶች ስሜት ስለተነካ ግራ መጋባታችንን እና ችግሮቻችንን በእግሮቹ ስር እንድንጥልና እዚያው እንድንተው ይፈልጋል። --MH 249 (1905). {1MCP 84.2} 1MCPAmh 71.3
መረዳት ከክርስቶስ ጋር የቀረበ ግንኙነት እንዲኖር ያደርጋል።--ጥሩ ሥራዎች ክርስቶስ እንድናፈራ የሚፈልግብን ፍሬዎች ናቸው፤ እነርሱም የገርነት ቃላት፤ የልግስና ሥራዎች፣ ለድሆች፣ ችግር ውስጥ ላሉትና ስቃይ ለደረሰባቸው ደግነትን ማሳየት ናቸው። ተስፋ መቁረጥና ሀዘን ለተጫናቸው ልቦች የሌሎች ሰዎች ልቦች ርኅራኄ ሲያሳዩ፣ እጅ ለችግረኞች ሲሰጥ፣ የተረቆቱት ሲለብሱ፣ መጻተኛ በሳሎናችሁ እንዲቀመጥ እንኳን ደህና መጣህ የሚል አቀባበል ሲያገኝና በልባችሁ ውስጥ ቦታ ሲያገኝ መላእክት እጅግ ቀርበው ስለሚመጡ ምላሹ ወደ ሰማይ ይሄዳል። {1MCP 84.3} 1MCPAmh 71.4
እያንዳንዱ የፍትህ፣ የምህረትና የልግስና ተግባር በሰማይ መልካም ቃና ያለው ዜማ ይፈጥራል። አብ ከዙፋኑ ሆኖ እነዚህን የምህረት ተግባራትን የሚፈጽሙትን ይመለከትና እጅግ ውድ ከሆኑ ሀብቶቹ ጋር ይቆጥራቸዋል። ‹‹እኔ ጌጦቼን በምሰራበት በዚያን ቀን የእኔ ይሆናሉ፣ ይላል የሰራዊት ጌታ›› (ሚልክያስ 3፡ 17)። ችግረኞች ለሆኑና ለሚሰቃዩት የሚደረግ እያንዳንዱ የምህረት ተግባር ለኢየሱስ እንደተደረገ ይቆጠራል። ድሆችን ስትረዱ፣ ስቃይ ለደረሰባቸውና ለተጨቆኑት ስታዝኑላቸው፣ ወላጅ የሌላቸውን ወዳጆቻችሁ ስታደርጉ፣ ራሳችሁን ከኢየሱስ ጋር የቀረበ ግንኙነት እንዲኖራችሁ እያደረጋችሁ ነው። --2T 25 (1868). {1MCP 84.4} 1MCPAmh 71.5
ክርስቶስ ገሮችና ርኁሩኆች እንድንሆን ይጠራናል።-- በሰውና በሰው መካከል እውነተኛ ርኅራኄ መኖር እግዚአብሔርን የሚወዱና የሚፈሩ ሰዎችን ለሕጉ ግድ ከሌላቸው ሰዎች የሚለይ ምልክት ነው። ክርስቶስ እየሞተ ለነበረው ዓለም ሕይወቱን መስዋዕት አድርጎ ለመስጠት ወደዚህ ዓለም በመምጣቱ የገለጠው ርኅራኄ ምንኛ ታላቅ ነው! የእርሱ ኃይማኖት ትክክለኛ የሆነ የሕክምና ሚስዮናዊ ሥራን ወደ መሥራት መራ። እርሱ ፈዋሽ ኃይል ነበር። ‹‹ምህረትን እወዳለሁ፣ መስዋዕትን አይደለም›› አለ። ታላቁ የእውነት ደራሲ በእነተኛና ሀሰተኛ ኃይማኖት መካከል ለመለየት የተጠቀመው መፈተኛ ይህ ነው። የህክምና ሚስዮናውያን ክርስቶስ በእኛ ዓለም ውስጥ ቢሆን ኖሮ የሚያሳየውን ዓይነት ገርነትና ርራኄ እንዲያሳዩ እግዚአብሔር ይፈልግባቸዋል። --SpT MM 8, 1893. (MM 251.) {1MCP 85.1} 1MCPAmh 72.1
የሕይወት ደስታ ድምር።--በደንብ ተኮትኩቶ ያደገ አእምሮ ታላቅ ሀብት ነው፤ ነገር ግን ልብን ገር ከሚያደርገው ርኅራኄና የተቀደሰ ፍቅር ተለይቶ ከፍተኛ ዋጋ አይኖረውም። ለሌሎች ግድ እንደሚለን የሚያሳዩ ቃላትና ተግባር ሊኖረን ይገባል። በእኛው ላይ ተመልሰው ሊንጸባረቁ በሚችሉ በወዳጅነት ቃላትና አስደሳች በሆኑ እይታዎች አንድ ሺህ የሚሆኑ ትናንሽ ትኩረቶችን ማሳየት እንችላለን። ሀሳብ የለሽ ክርስቲያኖች ሌሎችን ችላ ከማለታቸው የተነሣ ከክርስቶስ ጋር ሕብረት እንደሌላቸው ያሳያሉ። ከክርስቶስ ጋር አንድነት እያለ ለሌሎች አለመራራትና መብቶቻቸውን መርሳት አይቻልም። ብዙዎች ወዳጃዊ ርኅራኄን ለማግኘት በጥልቀት ይናፍቃሉ። {1MCP 85.2} 1MCPAmh 72.2
እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን ከሌላ ሰው ማንነት ጋር ሊደባለቅ የማይችል የራሳችንን ማንነት ሰጥቶናል፤ ነገር ግን እኛ በርግጠኝነት የክርስቶስ ከሆንን እና የእርሱ ፈቃድ የእኛ ከሆነ የእኛ የግል ባሕርዮቻችን ጎልተው አይታዩም። የአዳኛችን ሕይወት ለሌሎች ጥቅምና ደስታ የተቀደሰ እንደነበረ ሁሉ የእኛም ሕይወት ለሌሎች ጥቅምና ደስታ መቀደስ አለበት። የደግነትንና ትንንሽ የፍቅር ተግባራትን በመፈጸም፣ ሌሎች ላደረጉልን መልካም ነገሮች አመስጋኝነታችንን ለማሳየትና ሌሎችን ደስተኞች ለማድረግ፣ እንዲሁም ሀዘናቸውንና ሸክማቸውን ለማቅለልና ለማሳረፍ፣ በትንንሽ ነገሮች እንኳን ሳይቀር፣ አጋጣሚዎችን በመፈለግ ራሳችንን የረሳን መሆን አለብን። እነዚህ በቤተሰቦቻችን ውስጥ ጀምረው ከቤተሰብ ክበብ ወጥተው የሚስፋፉና ታስበው የሚደረጉ ደግነቶች የሕይወትን ደስታ ድምር የሚፈጥሩ ናቸው፤ እነዚህን ትንንሽ ነገሮች ችላ ማለት የሕይወት መራርነትንና የሀዘንን ድምር ይሰራሉ። --3T 539, 540 (1875). {1MCP 85.3} 1MCPAmh 72.3