የተሟላ ኑሮ

120/201

ሀብታሞችን የመቅረብ ዘዴ

ክርስቶስ ድሆችን ሲያስተምር ሀብታሞችንም የሚቀርብበት ዘዴ ከመፈለግ አልቦዘነም፡፡ ሀብታሞቹንና የተማሩትን ፈሪሳውያን፤ የአይሁድ ባላባቶች፤ የሮማን ገዥዎች ሊተዋወቅ ፈለገ፡፡ ግብዣቸውን ተቀበለ፤ በድግሳቸው ላይ ተገኘ፤ ልባቸውን አግኝቶ የማይጠፋውን ሀብት ሊገልጥላቸው ስለፈለገ ፍላጎታቸውንና የሥራቸውን ዓይነት አወቀ፡፡ CLAmh 128.2

ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም የመጣው አንድ ሰው ከላይ ኃይል ከተቀበለ ነውር የሌለበት ኑሮ መኖር እንደሚችል ለማሳየት ነው፡፡ በፍጹም ትዕግሥትና በደግነት ሰዎችን እንደየፍላጎታቸው ይሸኛቸው ነበር፡፡ በቸርነቱ ከሰዎች ልብ ኃዘንና ጥርጥርን አስወገደ፡፡ ጥላቻን ወደ ፍቅር፤ አለማመንን ወደ ማመን ይለውጣል፡፡ CLAmh 128.3

ያስደሰተውን “ተከተለኝ” ሲለው የተጠራው ተነሥቶ ይከተለዋል፡፡ የዓለም ቀንበር ተሰበረ፡፡ የእርሱን ድምፅ የሰማ ሁሉ መስገብገብና ጉጉት ከልቡ ውስጥ ይጠፋል፡፡ ሰዎቹ ነፃ ወጡና መድኅንን ተከተሉ፡፡ CLAmh 128.4