የተሟላ ኑሮ
የተሻለውን ዓለም ማስታወሻ
ተፈጥሮን በመመልከት በሽተኞች ስለራሳቸው ማሰብን ሊተዉ ይችላሉ፡፡ ባስገራሚው ሥራው ሲከበቡ አስተሳሰባቸው ከሚታየው ዓለም ወደማይታየው ዓለም ይራመዳል፡፡ የተፈጥሮ ውበት መልካሙን ነገር የሚያበላሽ፤ ሞትና በሽታ የሌለበትን የሰማይን ቤት ያሳስባቸዋል፡፡ CLAmh 118.1
በእንዲህ ያለ አካባቢ ከሆኑ ብዙ ሥቃይ ያለባቸው ሰዎች ወደ ሕይወት መንገድ ይጓዛሉ፡፡ የታመሙትንና የሚሰቃዩትን በሽተኞች ለመርዳትና በሚሰቃዩት ልቦች ውስጥ ድፍረትን፣ ደስታን፣ ተስፋንና ሰላምን ለማብቀል የሰማይ መላእክት ከምድራውያን ሰዎች ጋር በኅብረት ይሠራሉ፡፡ ነገሩ እንዲህ ከሆነ በሽተኞች ዕጽፍ ድርብ በረከት ይቀበሉና ይፈወሳሉ፡፡ የሚብረከረከው ጉልበታቸው ይጠነክራል፤ የፈዘዘው ዓይናቸው ይጠራል፤ ያለ ተስፋ የነበሩት ባለተስፋ ይሆናሉ፡፡ ፊታቸው ጨልሞ የነበረው ብሩህ ገጽ ይታይባቸዋል፡፡ የማጉረምረም ቃላት ተወግደው የደስታና የምስጋና ቃላት ይተካሉ፡፡ CLAmh 118.2
የአካል ጤንነታቸው የተሟላ ሲሆን ሰዎች መንፈሳዊ ጤና የሚያስገኘውን እምነታቸውን ያጠነክራሉ፡፡ የኃጢአት ይቅርታ ሲገኝ በቃላት ሊገለጥ የማይችል ሰላም ደስታና የመንፈስ እረፍት ይሰማል፡፡ እምነት በንግግር ይገለጣል፡፡ “አምላካችን መጠጊያችንና ኃይላችን ባገኘን በታላቅ መከራ ረዳታችን ነው፡፡” መዝሙር 46፡1 CLAmh 118.3
“በሞት ጥላ መካከል እንኳን ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፡፡ በትርህና ምርኩዝህ እነርሱ ያጽናኑኛል፡፡” መዝሙር 23፡4፡፡ “ለደካማ ኃይልን ይሰጣል፤ ጉልበት ለሌለውም ብርታትን ይጨምራል፡፡” ኢሣይያስ 40፡29 CLAmh 118.4