የተሟላ ኑሮ

109/201

ዘምሩ

ምስጋናን ደስታን በመዝሙር አማካይነት መግለጥ ነው፡፡ ፈተና ሲመጣብን በአሳብ ከመዋለል ይልቅ በሃይማኖት የምሥጋና መዝሙር ለአምላክ እናቅርብ፡፡ CLAmh 114.2

ተስፋ ስንቆርጥ የሚረዳን መሣሪያ መዝሙር ነው፡፡ ልባችን ለመድኃኒታችን ብርሃን ስንከፍትለት ያን ጊዜ ጤናና በረከት እናገኛለን፡፡ CLAmh 114.3

“ቸር ነውና ምህረቱም ለዘለዓለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑት፤ እግዚአብሔር ያዳናቸው ከጠላት እጅ ያዳናቸው ይናገሩ፡፡ መዝሙር 107፡1፣2 CLAmh 114.4

“በሁሉ አመስግኑ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ የሱስ ወደ እናንተ ነውና” 1ኛ ተሰሎንቄ 5፡18፡፡ ይህ ትእዛዝ እኛን የሚጎዳን የሚመስለው ነገር ሳይቀር ለእኛ ጥቅም እንደሚውል ያመለክታል፡፡ በሽተኞች እንዳይሻላቸው ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ ስለራሳቸው አጥብቆ ማሰብ ነው፡፡ ብዙ ድውያን ሰው ሁሉ እንዲያዝንላቸው እንዲረዳቸው ይፈልጋሉ፡፡ ግን የሚጠቅማቸው ስለራሳቸው አጥብቆ አለማሰቡ ነው፡፡ ስለሌሎች ማሰብና ሌሎችን መርዳት የእነርሱን ችግር ያቃልልላቸዋል፡፡ CLAmh 114.5

አብዛኛውን ጊዜ ችግር ለደረሰባቸው፤ ላዘኑትና ተስፋ ለቆረጡ ይጸለይላቸዋል፡፡ ይህም የሚደግፍ ነው፡፡ ያዘኑትን ልቦች እንዲጽናና፤ የጨለመው አእምሮ እንዲያበራ መጸለይ ያስፈልጋል፡፡ እግዚአብሔር እንዲባርካቸው ለሚፈቅዱ ጸሎታቸውን ይመልስላቸዋል፡፡ CLAmh 114.6

ላዘኑት ስንጸልይላቸው ከእነርሱ የባሱትን እንዲረዱ ማደፋፈር አለብን፡፡ ሌሎችን መርዳት ሲሞክሩ በእነርሱ ላይ ያንዣበበው ጨለማ ይወገዳል፡፡ እኛ በተጽናናንበት ተስፋ ለሎችን ማጽናናት ስንሞክር በረከቱ በእኛ ተመልሶ ይውላል፡፡ CLAmh 114.7

የኢሳይያስ 58ኛው ምዕራፍ ለሥጋና ለነፍስ በሽታ መድኃኒት ነው፡፡ CLAmh 114.8

“እንጀራህን ለተራቡት ትቈርስ ዘንድ፤ ስደተኞችንና ድሆችን ወደ ቤትህ ታገባ ዘንድ፤ የተራቈተውንስ ብታይ ታለብሰው ዘንድ፤ ከሥጋ ዘመድህ እንዳትሸሽግ አይደለም? የዚያ ጊዜ ብርሃንህ እንደንጋት ይበራል፡፡ ፈውስህም ፈጥኖ ይበቅላል፡፡ ጽድቅህም በፊትህ ይሄዳል፤ የእግዚአብሔርም ክብር በኋላህ ሆኖ ይጠብቅሃል፡፡” ኢሣይያስ 58፡7፣8 CLAmh 115.1

መልካም ሥራ ሁለት ጥቅም አለው፡፡ ሰጪውንም ተቀባይውንም ይጠቅማል፡፡ ለታመመ አካልና ለታወከ አእምሮ ቅን መሥራት ከሁሉ የበለጠ መድኃኒት ነው፡፡ CLAmh 115.2

አእምሮ ከሕሊና ወቀሳ ነፃ ሲሆንና በፈጸመው ተግባር ሲደሰት ያ ሌሎችን ስላስደሰተ የሚሰማው ደስታ ለአካሉ በሞላ በረከትን ያወርድለታል፡፡ CLAmh 115.3

የጤና ጉድለት ያለባቸው ሰዎች ስለራሳቸው ብቻ ማሰቡን ትተው ከእነርሱ የባሱትን መርዳት ቢሞክሩ ኖሮና የጌታን ትዕዛዝ ቢፈጽሙ “ብርሃንህ እንደ ንጋት ይበራል፤ ፈውስህም ፈጥኖ ይበቅላል” የሚለውን ተስፋ እርግጠኛነት ባወቁ ነበር፡፡ CLAmh 115.4