የተሟላ ኑሮ

102/201

የግል ኃላፊነት ደንብ

እግዚአብሔር ሰዎች ከእርሱ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እዲኖራቸው ይፈልጋል፡፡ ከሰዎች ጋር በሚያደርገው ግንኙነት ሁሉ የግል ኃላፊነትን ደንብ ችላ አይለውም፡፡ የግል እምነትና የግል መመሪያን ይደግፋል፡፡ ሰብአዊነትን ከመለኮታዊነት ጋር ሊያስተባብር ይፈልጋል፡፡ ሰብአዊነት ለመለኮታዊነት እንዲታዘዝ ፈቃዱ ነው፡፡ CLAmh 107.1

ሰይጣን ግን ይህን አሳብ ሊሠርዝ ይፈልጋል፡፡ ሰዎች በሰዎች ላይ እንዲያምኑ ያደፋፍራል፡፡ የሰዎች አስተሳሰብ ከእግዚአብሔር ከራቀ የሰይጣን ጭፍራዎች ሆኑ ማለት ነው፡፡ ያን ጊዜ ሰብአዊነት ይገዛል፡፡ አንዱ ሰው የሌላውን ሰው አስተሳሰብ እንዲገዛ ያደረገ ያው ሠይጣን ነው፡፡ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት ራሱን አለቃ አድርጎ ለመሰየም፤ በመለኮት ፈቃድ ቦታ የሰብዓዊን ፈቃድ ለመተካት ነው፡፡ በክርስትና ዓለም ውስጥ ካሉት ስህተቶች ሁሉ ከዚህ የበለጠ መከፋፈልን የሚፈጥርና አደገኛ ነገር የለም፡፡ CLAmh 107.2

በጽሞና ሲመለከቱት መልካም ቢመስልም በሽተኛን ያጠፋል እንጂ አያድንም፡፡ ሠይጣን ጣልቃ ገብቶ የሰባኪውንም ሆነ የተሰባኪውን ስሜት እጅ ያደርጋል፡፡ CLAmh 107.3

ክፉ አሳብ ያላቸው ሰዎች ኃይል አስጊ ነው፡፡ በሌሎች ድካምና ስህተት ተከልለው ለሚኖሩ በጣም አመች ነው! የሰዎችን አሳብ በመሳብና ሰዎችን በማታለል ዝናንና ትርፍን የሚያግበሰብሱ በጣም ብዙዎች ናቸው፡፡ CLAmh 107.4

ሰብአዊነትን ለሰብዓዊነት ተገዥ ከማድረግ የበለጠ የሥራ እድል ተዘርግቶልናል፡፡ ሐኪሙ ሰዎች ሰብዓዊ ፍጡርን ትተው በመለኮት አንዲያምኑ ያስተምራቸው፤ ለአካልና ለመንፈሳቸው ፈውስ እነዲሰጡአቸው ሰዎችን ደጅ የሚጠኑትን ሰዎች የዘለዓለም አዳኝ ወደሆነው ወደ እግዚአብሔር እንዲመለከቱ ያስተምሯቸው፡፡ የሰውን አእምሮ የፈጠረ አምላክ የሰውን ፍላጎት አጣርቶ ያውቃል፡፡ የፈዋሽነት ኃይል ያው እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ አካልና መንፈሳቸው የታመመባቸው ሁሉ ወደ ክርስቶስ በተስፋ ይመልከቱ፡፡ “እኔ ህያው ነኝና እናንተ ደግሞ ህያዋን ትሆናላችሁ” (ዮሐ 14፡19) CLAmh 107.5

ለበሽተኞች ሐይወትን ልናስገኝ የምንችል የሱስ ፈዋሽ መሆኑን እንዲያምኑ በመንገር፤ ከእርሱ ጋር እንዲተባበሩ፤ በፍርሃትና በአክብሮት እንዲታዘዙት፤ የጤናን ሕግ እንዲታዘዙና እንዲጠብቁ በማስረዳትና ይህን ካደረጉ ሕይወቱን እንደሚያድላቸው በማስገንዘብ ነው፡፡ CLAmh 107.6

ክርስቶስን በዚህ መንገድ ካስተዋወቅን ከላይ የተላከ ብርታት ማስተላለፋችን ነው፡፡ መንፈስንና አካልን ለመፈወስ እውነተኛው የሕክምና ሳይንስ ይህ ብቻ ነው፡፤ CLAmh 108.1