የተሟላ ኑሮ

100/201

20—አስታማሚነት በቤት ውስጥ

ሕመምተኞችን የሚያገለግሉ የጤናን ደንብ ጠንቅቀው ማወቅ ይገባቸዋል፡፡ ይህ ሕግ መከበር ያለበት ከማንኛውም ቦታ በበለጠ በበሽተኛው ክፍል ነው፡፡ አስታማሚዎች በሽተኛውን ሲረዱ በጥቃቅን ነገሮች ሁሉ ታማኝ መሆን ያስፈልጋቸዋል፡፡ በሽተኛው በጥብቅ ከታመመ ትንሽ ቸልተኛነት፤ የበሽተኛውን ፍላጎት እንደዋዛ መቁጠር ፍርሃት፤ ድንጋጤ፤ አለማዘን፤ በሽተኛውን ከሞት ሊያደርሰው ይችላል፡፡ በትጋት ተረድቶ ቢሆን ሕይወቱ ሊተርፍ ይችል የነበረው በሽተኛ በአጭር ይቀጫል፡፡ CLAmh 103.1

የአስታማሚዋ የሥራ ውጤት ሊለካ የሚችለው ራሷ ብርቱ የአካል አቋም የኖራት እንደሆን ነው፡፡ የተሟላ ጤና ካላት ለበሽተኛው ልታበረክት የሚገባትን አገልግሎት በሚገባ ትፈጽማለች፡፡ ተግባሯም የተሳካ ውጤት ይኖረዋል፡፡ አስታማሚዎች አመጋገብን፣ ንጽሕናን፣ ንጹህ አየርንና የአካል ማጠንከሪያ ልምምድን አተኩረው መመልከት አለባቸው፡፡ CLAmh 103.2

የበሽተኛው ቤተሰቦች በነገሩ ተባባሪ ቢሆኑ አስታማሚዎቹን በኃላፊነታቸው ረዷቸው ማለት ነው፡፡ እንዳይታመሙም ይረዷቸዋል፡፡ CLAmh 103.3

ሕመሙ ጥብቅ ሆኖ ሌሊትና ቀን አስታማሚ የማይለየው በሽተኛ ከሆነ ሲያንስ ሁለት ጎበዝ አስታማሚዎች ያስፈልጋሉ፡፡ እንዲህ ከሆነ ዕረፍትና ንጹህ አየር የማገኘት እድል ይኖራቸዋል፡፡ CLAmh 103.4

በተለይ በበሽተኛው ክፍል ውስጥ በቂ አየር ከሌለ ነገሩ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ የንጹህ አየርን ጥቅም ባለማወቅ በክፍሉ ውስጥ ብዙ ጊዜ አየር እንደልብ እንዲገኝ አይደረግም፡፡ ስለዚህ የበሽተኛው ሆነ የአስታማሚዎቹ ሕይወት ከሥጋት ላይ ይወድቃል፡፡ CLAmh 103.5

የሚገባ ጥንቃቄ ቢደረግ ኖሮ ተላላፊ ያልሆኑ የበሽታ ዓይነቶች ወደ ሌላ ሰው ባልተጋቡም ነበር፡፡ ይህ ዓይነት ልማድ ይታረም፤ በቂ አየር በማግኘትና በንጽህና አማካይነት በሽተኛው ከሕመምና ከሚመርዙ ነገሮች ነፃ ይሁን፡፡ CLAmh 104.1

በዚህ ዓይነት ይዞታ በሽተኛው የመዳን ተስፋው የተሟላ ከመሆኑም በላይ አስታማሚዎቹ ሆኑ ቤተሰቦቹ በሽታው አይጋባባቸውም፡፡ CLAmh 104.2

በሽተኛው በቶሎ እንዲገግም ከተፈለገ የተኛበት ክፍል ሰፊ፣ ብርሃን ያለበት፣ ንጹህ አየር የሚገኝበት መሆን አለበት፡፡ በቤት ውስጥ እነዚህን ግዴታዎች አሟልቶ የያዘው ክፍል ለበሽተኛው መኝታ እንዲሆን ይመደብ፡፡ CLAmh 104.3

ብዙ ቤቶች ምቹ የአየር ማስተላለፊያ አሠራር የላቸውም፡፡ ስለዚህ ለበሽተኛ ማስታመሚያ ለመሆን አይመቹም፡፡ ግን ሌሊትና ቀን በሽተኛው የአየር እጥረት እንዳይደርስበት ልዩ ቁጥጥር መደረግ አለበት፡፡ CLAmh 104.4

በበሽተኛው ክፍል ውስጥ ሊኖር የሚገባው የሙቀት ልክ እንደተቻለ መጠን በበሽተኛው ክፍል ውስጥ ሙቀቱ የተስተካከለ መሆን አለበት፡፡ በሙቀት መለኪያ መሣሪያ መለካት አለበት፡፡ አስታማሚዎች በተለይ ሌሊት ሲሠሩ ስለሚበርዳቸው በእጃቸው በመዳሰስ ወይም በአካላቸው ስሜት ሙቀቱን ሊወስኑ አይችሉም፡፡ CLAmh 104.5

የአስታማሚዋ አንዱ ዋና ተግባር የበሽተኛውን ምግብ መቈጣጠር ነው፡፡ CLAmh 104.6

በሽተኛው በምግብ እጥረት መዳከም የለበትም፡፡ ወይም ባለተመጠነ አመጋገብ የምግብ ማዋሃጃ ክፍሉ በሥራ መድከም የለበትም፡፡ ጣፋጭና ሊበላ የሚችል ምግብ ቢዘጋጅ መልካም ነው፤ ግን የበሽተኛው ምግብ ተቀባይነትም መታየት ይኖርበታል፡፡ ብዛቱም፤ ዓይነቱም ይታሰብበት፡፡ ሰውየው ሲያገግም እህል እህል ሰለሚያሰኘው የፈለገውን ያህል ቢበላ ላልበረታው የምግብ ማድቀቂያው ክፍል አደገኛ ይሆናል፡፡ CLAmh 104.7

በሽተኛውን የሚያስታምሙትም ሆነ ወደ በሽተኛው ክፍል የሚገቡ ፈገግታ የማይለያቸው፤ ረጋ ያሉና ራሳቸውን የቻሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ችኮላ፣ ግርግርና ድንግርግር መፈጠር የለበትም፡፡ በር ሲከፈትና ሲዘጋ በጥንቃቄ ሆኑ የቤቱ ጸጥታ ይከበር፡፡ በሽታው ትኩሳት ያለበት ከሆነ የተለየ ጥንቃቄ መደረግ ይገባዋል፡፡ ሳይዘነጉ መጠባበቅም ያሻል፡፡ ባለማወቅ በመርሳት፤ በቸልተኛነት ምክንያት ትጉህ አስታማሚ ቢያገኙ ሊድኑ ይችሉ የነበሩ በሽተኞች ይሞታሉ፡፡ CLAmh 104.8

ያላግባብ የሆነ ደግነት፣ የተሳሳተ የአክብሮት መንፈስ የበሽተኛው ጠያቂዎች እንዲበዙ ምክንያት ይሆናል፤ በጠና የታመሙ ሰዎች ጠያቂ አያስፈልጋቸውም፡፡ ጸጥታና ዕረፍት በሚያሻው ጊዜ ጠያቂዎችን ቢያስተናግድ ሕመሙ ይጠናበታል፡፡ CLAmh 105.1

ከሕመሙ ያገገመ ሰውና በማይድን በሽታ የተለከፈ ሰው ባይረሳ ደስ ይለዋል፡፡ ግን አለመረሳቱን ለመግለጥ ራስ እየሄዱ ከመጠየቅ ይልቅ በመልዕክትና በስጦታ አማካይነት ቢጠየቅ ይሻላል፡፡ ጉዳት ወይም አደጋ አያስከትልም፡፡ CLAmh 105.2