የተሟላ ኑሮ
በአስካሪ መጠጥ ሱስ የተጠመዱ ሰዎች
“ወይስ ስጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተመቅደስ መሆኑ አታውቁምን በዋጋ ተገዝታችኋልና የራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ፡፡” (1ኛ ቆሮንቶስ 6፡19-20) CLAmh 77.5
“የወይን ጠጅ ፌዘኛ ያደርጋል፤ ብርቱ መጠጥም ጠበኛ ያደርጋል፡፡ በዚህም የሳተ ጠቢብ አይደለም፡፡ “ዋይታ ለማነው? ኀዘን ለማን ነው? ጩኸት ለማን ነው? ጠብ ለማን ነው? ያለምክንያት መቁሰል ለማን ነው? የዓይን ቅላት ለማን ነው? የወይን ጠጅ በመጠጣት ለሚዘገዩ አይደለምን? CLAmh 77.6
“ወደ ወይን ጠጅ አትመልከት በቀላ ጊዜ መልኩም በብርሌ ባንጸባረቀ ጊዜ እየጣፈጠ በገባ ጊዜ በኋላ እንደ እባብ ይነድፋል፤ እንደ እፉኝትም መርዙን ያፈስሳል፡፡” (ምሳሌ 20፡1፣ 23፣ 29-32) CLAmh 77.7
በመጠጥ ኃይል የተለከፈ ሰው ባርነትና ዝቅተኛነት ከዚህ በበለጠ ቅልብጭ ያለ አገላለጥ ሊዘረዝር አይችልም፡፡ ጉዳቱን ቢረዳውም እንኳን ኃይል ስለሌለው ከወጥመዱ ሊያመልጥ አይችልም፡፡ “ደግሞ ጨምሮ ይሻታል” (ምሳሌ 23፡35) CLAmh 78.1
ስካር በጠጪዎች ላይ የሚያመጣውን ጉዳት ለማስረዳት አከራካሪ ጉዳይ የለበትም፡፡ ክርስቶስ የሞተላቸው ብዙ ነፍሳት የትም እንዳልሆነ ሆነው ሲወድቁ መላዕክት ያለቅሱላቸዋል፡፡ የማንኛውም አገር ሃፍረት፣ ሸክምና መርገም ናቸው፡፡ የምንመካበት ሥልጣኔያችን ጥቁር ነቁጣ ናቸው፡፡ CLAmh 78.2
የሰካራም ቤት የቻለውን ችግር፤ ጭቅጭቅ፤ መንገላታትና ሥቃይ ማን ዘርዝሮ ይዘልቃል? ተቀማጥላ ያደገች፣ በሚገባ የተማረችና አዋቂና ብልህ ሴት ዲያብሎስ ከሆነ ባል ጋር መኖሯን አንዘንጋ፡፡ ልጆቹ ድሎት፣ ትምህርት፣ የሚገባ ሥልጣኔ ተነፍገው መመኪያቸውና መጠለያቸው ሊሆን በሚገባው ስህተት ሲመሩ፤ ሃፍረትንና አንገት መድፋትን ተጎናጽፈው ወደ ዓለም ሲሠማሩ ማየት፤ የአባታቸውን የስካር ዐመል እንደ ቅርስ ወርሰው ሲሰቃዩ ማየት በጣም ያሰቅቃል፡፡ CLAmh 78.3