የተሟላ ኑሮ

66/201

ሲበሉ መዝናናት

አንዳንዶች ሰዎች ምግባቸው ቀላልና ለጤና ተስማሚ ቢሆንም ሁልጊዜ እታመም ይሆናል ብለው ይሰጋሉ፡፡ እንደዚህ ላሉት ሰዎች “ምግባችሁ አይጎዳችሁምና አትስጉ፤ እንዲያውም ስትበሉ ስለምግቡ አታስቡ፡፡ መልካም መስሎ የታያችሁን ብሉ፤ እግዚአብሔር ምግቡን ለጤናችሁ ተስማሚ እንደሚያደርገው ከጸለያችሁ ጸሎታችሁ እንደሚፈጸም እመኑ፤ በሰላም ተቀመጡ” እላቸዋለሁ፡፡ CLAmh 68.6

የጤና ሕግ ለሆድ የማይስማሙትንና ጤናን የሚጎዱትን የምግብ ዓይነቶች እንዳንበላ ስለሚከለክለን አሰስ ገሰስ መብላት በጤና መቀለድ መሆኑን አንዘንጋ፡፡ ለመዳን ከሚያስቸግሩት የሕመም ዓይነቶች መካከል ብዙዎች በዚሁ በምግብ ጠንቅ የሚመጡ ናቸው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የማይጠቅሙ ምግቦችን የሚበሉ ድሆች ብቻ አይደሉም፡፡ CLAmh 68.7

በችላ ባይነትና ባለማወቅ ይህንን የሚደርጉ አይታጡም፡፡ አንዳንዶችም የራሳቸውን ያመጋገብ ደንብ መከትል ሲፈልጉ ይህ ጉዳት ይደርስባቸዋል፡፡ CLAmh 69.1

አካላችንን በመጉዳት ከአገልግሎት ስናስተጓጉለው እግዚአብሔርን ማክበራችን አይደለም፡፤ የቤተሰብ አስተዳዳሪ ተቀዳሚ ተግባር ብርታትና ጥንካሬ የሚሰጥ ምግብ ለቤተሰቡ ማቅረብ ነው፡፡ ቤተሰብን በምግብ ከመበደል የልብስንና የቤት ዕቃን ወጭ መቀነስ ይሻላል፡፡ CLAmh 69.2

አንዳንድ የቤተሰብ አስተዳዳሪዎች እንግዶችን በሚገባ ለማስተናገድ ሲሉ የቤተሰቡን የምግብ ይዞታ ይበድላሉ፡፡ ይህ ቂልነት ነው፡፡ እንግዳ እንደነገሩ ሊሸኝ ይችላል፡፡ የቤተሰብ ጉዳይ የመጀመሪያውን ደረጃ ይያዝ፡፡ CLAmh 69.3

አጉል ልምድና ያልተስተካከለ የቤት አያያዝ መስተንግዶን በተፈለገ ጊዜና በረከት ሊሆን በሚችልበት ጊዜ ያስቀረዋል፡፡ የየእለቱ የቤት ዝግጅታችን ያልታሰበ እንግዳ ቢመጣ ለቤት እመቤቷ ሸክም እንዳይሆን ሆኖ መያዝ ያስፈልገዋል፡፡ CLAmh 69.4

ማንም የሚበላውን ማወቅና ማዘጋጀት መቻል አለበት፡፡ ወንድም ሆነ ሴት ቀላል የምግብ አዘገጃጀት ቢያውቅ አይጎዳውም፡፡ CLAmh 69.5

ምግባችሁን በሚገባ አስቡበት፡፡ መነሻውንና ውጤቱን ተቆጣጠሩ፡፡ ራስን የመግዛት ችሎታችሁን አዳብሩ፡፡ የምግብ ፍላጎታችሁን በቁጥጥራችሁ ሥር አድርጉት፡፡ በቁንጣን አትቸገሩ፡፡ በሌላም በኩል በችጋር ተሰቃይታችሁ ጤናችሁን አትበድሉ፡፡ CLAmh 69.6