የተሟላ ኑሮ

60/201

ማመዛዘንና ራስን መቆጣጠር መልመድ

የጉለበት ሥራ የሚያከናውኑ ብርቱ ሰዎች የምግባቸውን ዓይነት ሆነ መጠን በመወሰን ረገድ የቅምጥና የአእምሮ ሥራ የሚሠሩትን ያህል መጠበብና መጨነቅ አያስፈልጋቸውም፡፡ ግን እነርሱም ቢሆኑ በምግብና በመጠጣቸው በኩል ቢጠነቀቁ ይበጃቸዋል እንጂ አይጎዳቸውም፡፡ CLAmh 61.3

አንዳንድ ሰዎች ስለ አመጋገብ የማያዳግም ደንብ ቢደነገግ ይወዳሉ፡፡ ከመጠን በላይ ይበሉና ቆይተው ይጸጸታሉ፤ ስለ ምግብና መጠጣቸው ሲያወጡና ሲያወርዱ ይኖራሉ፡፡ አንዱ ሰው ለሌላው የአመጋገብ ደንብ ሊያወጣለት አይችልም፡፡ ሁሉም አመዛዝኖና ራሱን ተቆጣጥሮ በሥርዓት መኖር ያሻዋል፡፡ CLAmh 61.4

አካላታችንን ክርስቶስ ገዝቶ የግሉ አድርጓቸዋል፡፡ ስለዚህ የፈለግነው ልንፈጽምባቸው መብትና ነፃነት የለንም፡፤ የጤናን ሕግ የሚያስተውሉ ሁሉ እነዚህን ደንቦች የማክበር ግዴታ እንዳለባቸውና ሕጉን ደንጋጊውም እግዚአብሔር መሆኑን መገንዘብ ያሻል፡፡ ሕግን ስንተላለፍ ቅጣቱን የምንቀበል ራሳችን ነን፡፡ በልምዳችንና በሥራችን እግዚአብሔር በኃላፊነት ሲጠይቀን መልስ አቅራቢዎቹ ራሳችን ነን፡፡ ስለዚህ ራሳችን መጠየቅ ያለብን “የዓለም ሥራ እንዴት ነው?” ብለን ሳይሆን “እኔ ራሴ ለግሌ እግዚአብሔር የሰጠኝን የመኖር ግዴታ እንዴት አካሂደዋለሁ?” ብለን ነው፡፡ CLAmh 61.5