የተሟላ ኑሮ
የሕይወት ምግቦች
እግዚአብሔር የመረጠልን ምግቦች ጥራጥሬ እህል፣ ፍራፍሬ፣ ሥራ-ሥርና ቅጠላቅጠል (አትክልት) ናቸው፡፡ የተፈጥሮ ጣእማቸው ሳይጠፋና ብዙ ነገር ሳይጨመርባቸው ከተዘጋጁ እነዚህ ምግቦች የምግብ ፍላጐትን ለማሟላትና ሙሉ ጤንነትን ለመስጠት ይችላሉ፡፡ ብዙ ነገር ከተቀላቀለባቸውና በጣም ከሚጣፍጡ ምግቦች የበለጠ ኃይልና ጥንካሬ ይገኝባቸዋል፡፡ CLAmh 53.4
አንዳንድ ምግብ ምንም እንኳን ጥሩ ቢሆን በማንኛውም ጊዜ ፍላጎታችንን የሚያሟላ ላይሆን ይችላል፡፡ ስለ ምግብ አመራረጥ በጣም መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ምግባችን ለወቅቱ፣ ለአየሩ ሀኔታና ለሥራችን ተስማሚ መሆን አለበት፡፡ ከዓመቱ ለተወሰኑ ጊዜና ለተወሰኑ የአየር ሁናቴ የሚስማ ምግብ ለሌላ ጊዜና ሁናቴ የማይስማማ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ልዩ ልዩ ሥራ ለሚሠሩ ሰዎች የሚስማማቸው ምግብ አንድ ዓይነት አይደለም፡፡ ጠንካራ ሥራ ለሚሠሩ ሰዎች የሚስማማ ምግብ በቅምጥ ለሚሠሩ ወይም የአእምሮ ሥራ ለሚበዛባቸው አይስማማም፡፡ እግዚአብሔር ለጤናችን የሚስማሙ ልዩ ልዩ ዓይነት ምግቦች በብዛት ሰጥቶናል፤ እያንዳንዱ ሰው የሚጠቅመውን አስቦ መምረጥ አለበት፡፡ CLAmh 53.5
ከሥነ ፍጥረት የምናገኛቸው ፍራፍሬዎች፣ ሥራሥሮችና (የኦቾሎኒ ቤተሰብ) ጥራጥሬዎች በጣም ብዙ ናቸው፤ በያመቱ ለመጓጓዣ በሚደረገው መሻሻል ምክንያት እነዚህን የምግብ ዓይነቶች ከአንዱ ቦታ ወደ ሌላው ለማድረስ ተችሏል፡፡ በዚህም ምክንያት ከጥቂት ዓመታት በፊት በጣም ውድ የነበሩ ምግቦች ዛሬ ማንኛውም ሰው በየዕለቱ ፍለጎቱ ሊያገኛቸው ይችላል፡፡ ለዚህ ምሳሌ የሚሆን የደረቅና በቆርቆሮ የታሸገ ምግብ ነው፡፡ ነትና (ኦቾሎኒና) ከነት የሚሠሩ ምግቦች በሥጋ ምትክ እየገቡ ናቸው፡፡ ጤና የሚሰጡና የተሟሉ ለማድረግ ከነትስ ጋር ጥራጥሬ እህል፣ ፍራፍሬና አንዳንድ ሥራሥሮች ሊጨመርባቸው ይገባል፡፡ ብዙ ነትስ ላለመብላት መጠንቀቅ ያሻል፡፡ ነት በመብላት ሕመም የሚሰማቸው ሁሉ የተጠቀሰውን ጥንቃቄ በማድረግ ሕመማቸውን ለማስወገድ ይችላሉ፡፡ አንዳንድ ነት (ኦቾሎኒ) እንደሌላው ተስማሚ አለመሆኑን ማወቅ ተገቢ ነው፡፡ አልመንድ የሚባለው ነት ከፒነት የተሻለ ነው፤ ይሁን እንጂ ፒነትም በመጠኑና ከጥራጥሬ እህል ጋር ቢበሉት በጣም ጠቃሚና በቀላሉ የሚፈጭ ምግብ ነው፡፡ CLAmh 54.1
በደንብ ከተዘጋጀ የወይራ ፍሬ እንደነት በቅቤና በሥጋ ምትክ ሊበላ ይችላል፡፡ ከወይራ ፍሬ የሚገኘው ቅባት ከእንሰሳት ከሚገኘው ቅባት የበለጠ ጠቃሚ ነው፡፡ አንጀትን ያለሰለልሳል፡፡ የሳባ ነቀርሳ ለያዛቸው በሽተኞች ይጠቅማል፤ ለታወከና ለቆሰለ ጨጓራም መድኃኒት ነው፡፡ CLAmh 54.2