የተሟላ ኑሮ

36/201

ከቤተሰብ ለመለየት መዘጋጀት

በእውነተኛ ቤተሰብ ውስጥ በፍቅርና በጥበብ ካደጉ ልጆች ደስታና ጓደኝነት ፍለጋ አይንከራተቱም፡፡ ብልግና አያታልላቸውም፡፡ በቤተሰብ ውስጥ የሚገኝ መንፈስ ጠባያቸውን ይገነባል፤ ከቤተሰብ ጥበቃ ወጥተው በዓለም ውስጥ ሥራቸውን በሚይዙበት ጊዜ ፈተናን ለመቋቋም የሚችል ጠባይና ደንብ ይኖራቸዋል፡፡ CLAmh 36.2

ልጆችም እንደ ወላጆቻቸው በቤተሰብ ውስጥ ሊያከናውኑት የሚገባ ዋና ተግባር አለ፡፡ ልጆች በቤተሰብ ውስጥ ዋና ክፍል እንዳላቸው መማር አለባቸው፡፡ ምግብ፣ ልብስና ፍቅር ያገኛሉ፤ ጥንቃቄም ይደረግላቸዋል፤ አባል ለሆኑበት ቤተሰብ ደስታን በማስገኘትና የሚሰጣቸውን ተግባር በመፈጸም ለሚደረግላቸው ነገር ሁሉ አመስጋኝ መሆናቸውን መግለጽ ይገባቸዋል፡፡ አንዳንድ ነገር እንዳያደርጉ በሚከለከሉበት ጊዜ ልጆ ይናደዳሉ፡፡ ይሁን እንጂ ባደጉ ጊዜ ተጠንቅቀው ስላሳደጓቸው ወላጆቻቸውን ሲያመሰግኑ ይኖራሉ፡፡ CLAmh 36.3