የተሟላ ኑሮ
የፀሐይ ብርሃን በቤቱ ውስጥ
ከሁሉም በላይ ወላጆች ልጆቻቸው ደስተኞች፣ አክባሪዎችና አፍቃሪዎች እንዲሆኑ ማድረግ አለባቸው፡፡ ፍቅር በአስተያየት፣ በቃልና በሥራ በሚገለጽበት ቤት መላዕክት ለመገኘት ይፈቅዳሉ፡፡ CLAmh 31.4
ወላጆች ሆይ፤ የፍቅር፣ የደስታና የበቃኝ ማለት ብርሃን በልባችሁ ውስጥ ይብራ፤ በዚህም ምክንያት በቤታችሁ ውስጥ የደስታ ስሜት ይስፈን፡፡ የፍቅርና የትዕግስት መንፈስ ይታይባችሁ፤ ልጆቻችሁም ይህ ዓይነት ጠባይ እንዲኖራቸው አድርጉ፡፡ ጥሩ ጠባይን በመኮትኮት የቤተሰብን ሕይወት የሚያስደሰት አድርጉት፡፡ የፀሐይ ብርሃንና አየር ለዕፅዋት የሚያስፈልጉትን ያህል የዚህ ዓይነትም ኑሮ የልጆችን ጤንነት እያዳበረ አእምሯቸውንና አካላቸው ያጠነክርላቸዋል፡፡ CLAmh 32.1