የተሟላ ኑሮ

199/201

እግዚአብሔርን የማምለክ መብት

እግዚአብሔርን በጉባኤ ማምለክን ችላ ማለት ከባድ ስህተት ነው፡፡ እግዚአብሔርን የማገልገል መብት ቀላል ግምት ሊሰጠው አይገባም፡፡ በህክምና ሞያ የተሰማሩ ሰዎች ወደ ቤተ ፀሎት ለመሄድ ሥራ የሚበዛባቸው መስሎ ይሰማቸዋል፤ ግን በየምክንያቱ ወደ ፀሎት ቤት ከመሄድ መቅረት የለባቸውም፡፡ CLAmh 211.4

ኑሮአችን ሁለት መልክ የያዘ መሆን ይገባዋል፡፡ ማሰብና መሥራት፤ መፀለይና ከልብ ተግባርን ማከናወን አለብን፡፡ በፀሎትና በጥረት የተገኘ ኃይል በጭንቅ ጊዜም ቢሆን ፈተናን ለመቋቋም፤ የየዕለት ግዳጅን በሚገባ ለማከናወን፤ በሚገባ ማሰብና በሰላምና በደስታ ለመኖር ያስችላል፡፡ CLAmh 211.5

አንዳንድ ሰዎች ችግር ሲደርስባቸው ግራ ያጋባቸውን ነገር ለምድራዊ ወዳጅ በመዘርዘር መፍትሔ የሚያገኙ ይመስላቸዋል፡፡ ፈተና ሲደርስባቸው ይጠራጠራሉ፡፡ ቀኑ ይጨልምባቸዋል፡፡ ግን ሁል ጊዜ ኃያሉ አጽናኝ በአጠገባቸው ቆሞ እመኑኝ ይላቸዋል፡፡ የሱስ የሸክማችን አቅላይ “ወደ እኔ ኑ እኔም አሳርፋችኋለው’’ ይለናል፡፡ CLAmh 211.6

እርሱን ትተን እንደ እኛ የእግዚአብሔር እርዳታ ወደ ሚያስፈልጋቸው ሰዎች እርዱን እያልን እንሂድ? የሥራውን ታላቅነት ስትመለከቱ የጠባያችሁን ጉድለትና የችሎታችሁን ማነስ ተስፋ ያስቆረጣችሁ ይሆናል፡፡ CLAmh 211.7

ግን ከማንም ሰው የበለጠ የአእምሮ ችሎታ ቢኖራችሁም ለሥራችሁ ብቁ ልትሆኑ አትችሉም፡፡ ጌታችንና አዳኛችን “ያለ እኔ ምንም ማድረግ አትችሉም” ይለናል፡፡ (ዮሐንስ 15÷5) ፡፡ የምንሠራው ሥራ ሁሉ በአምላክ ርዳታ ነው፡፡ የሆነ ቢሆንም በአምላክ ላይ የዘወትር እምነት ይኑራችሁ፡፡ CLAmh 211.8

በሥራችሁ፤ በትርፍ ጊዚያችሁ በምታደርጉት መዝናናት፤ በኑሮ ትግላችሁ፤ ፀሎት አዘውትሩ፡፡ CLAmh 212.1

እንደዚህ ስታደርጉ እግዚአብሔርን ማክበራችሁ እርሱም እናንተን ማክበሩ ይታወቃል፡፡ ባዘናችሁ ጊዜ ፀልዩ፤ ሲከፋችሁ ለሰዎች አትናገሩ፡፡ የሌሎችን መንገድ አታሰናክሉ፡፡ CLAmh 212.2

ሁሉንም ለየሱስ ንገር፡፡ እጅህን ለርዳታ ዘርጋ (ሌሎችን እርዳ) ፡፡ ደካመነትህን አውቀህ ኃያሉን አምላክህን ተጠማጠም፡፡ የእግዚአብሔርን ብርሃን እንድትቀበልና በፍቅሩ እንድትደሰት ትሁት ትሆን ዘንድ፤ እምነትህ እንዲጎለምስ፤ ጥበብና ድፍረት እንድታገኝ ፀልይ፡፡ CLAmh 212.3