የተሟላ ኑሮ
35—ከሁሉ የበለጠ የህይወት አጋጣሚ
በየጊዜው ክርስቶስን የማወቅ ዕድል፤ ትእዛዙ ጋር የሚስማማ የዕለት ኑሮ ሊኖረን ይገባል፡፡ በራሳችን ጥረት ቅዱስና ከፍተኛ ሙያ ልንፈጽም አንችልም፡፡ በእውቀትና በጠባይ እንድንጎለምስ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፡፡ መለኮታዊ ድምፁን ያስተጋባል፡፡ ህጉ “እደጉ “የሚለውን መለኮታዊ ድምፁን ያስተጋባል፡፡ “የተቀደሱ” ይላል፡፡ በየቀኑ የክርስትና ጠባያችን መሻሻል አለበት፡፡ CLAmh 207.2
የእግዚአብሔር ሰፊ ቤተሰብ አባል የሆኑ ብዙ ሰዎች የክርስቶስን ክብር ማየትና ከክብር ወደ ክብር መሸጋገር ምን እንደሆነ አያውቁም፡፡ ብዙዎች ደግሞ ስለክርስቶስ ፍፁምና ጭላንጭል በማየታቸው ልባቸው በደስታ ይዘላል፡፡ የመድኃኒታችንን ፍቅር በበለጠ ለመረዳት ጉገት ያድርባቸዋል፡፡ CLAmh 207.3
እግዚአብሔርን የሚሻ ነፍስ ሁሉ በዚህ ይደሰት፡፡ መንፈስ ቅዱስ ለመመራት ፈቃደኛ የሆኑትን ይመራቸዋል፡፡ ለመገራት የሚፈልጉትን ይገራቸዋል ለመሰልጠን የሚሹትንም ያሰለጥናቸዋል፡፡ መንፈሳዊ አስተሳሰብና የተቀደሰ ግንኙነት ይኖራቸዋል፡፡ መንፈሳዊ ብርታት እንድንቀበል እኛም እንደ የሱስ ለጸሎት የተለየ ጊዜ መወሰን ያሻናል CLAmh 207.4
አሁን ያያችሁት የክብሩን ጎህ ብቻ ነው፡፡ አምላክን በበለጠ ለማወቅ እንደፈለጋችሁ መጠን “የጻድቃን መንገድ እንደ ንጋት ብርሃን መሆኑን” ትገነዘባላችሁ፡፡ (ምሳሌ 4፡18) ፡፡ CLAmh 208.1
ክርስቶስ ደግሞ “ደስታዬም በእናንተ እንዲሆን ደስታችሁም እንዲፈፀም ይህን ነግሬአችኋለሁ” ብሏል፡፡ (ዮሐንስ 15፡11) CLAmh 208.2