የተሟላ ኑሮ

189/201

ያልታዩት ተጨባጭ ነገሮች

ኀዘንና ትካዜ ቢሰማህ ስለ ስሜትህ ብዙ አትናገር፡፡ የሌሎችን ኑሮ በአንተ የትካዜ ወሬ አታጨልም፡፡ ቀዝቃዛና እንደ ደመና የከበደ ሃይማኖት ነፍሳትን ወደ ከርስቶስ አይመልስም፡፡ የባዘኑትን ለማጥመድ ሰይጣን ወደ ጣለው አሽከላ(ወጥመድ) ይነዳቸዋል፡፡ CLAmh 202.7

በጉድለትህ ከመተከዝ ይልቅ በክርስቶስ አማካይነት የምታገኘውን ኃይል አስታውስ፡፡ በአሳብህ ያልታዪትን ነገሮች ተመልከት፡፡ ዝንባሌህ እግዚአብሔር ወዳሳየህ ታላቅ ፍቅር ይራመድ፡፡ እምነት ፈተናን ይታገሳል፤ ችግርን ይቋቋማል፤ በኀዘን ጊዜም መጽናናትን ያስገኛል፡፡ ክርስቶስ አማላጃችን ነው፡፡ በአማላጅነት ሥልጣኑ ሁሉን ይሰጠናል፡፡ CLAmh 202.8

ለእርሱ የሚኖሩትን ክርስቶስ ከፍተኛ ግምት የሚሰጣቸው አይመስላችሁም? እንደ ተወደደው ዮሐንስ በግዞት ሆነው በጭንቅና በችግር ስለእርሱ የሚንገላቱትን የሚረሳቸው መሰላችሁ? CLAmh 203.1

እግዚአብሔር በሙሉ ልብ የሚያለግሉትን ሁሉ ድል እንዲሆኑ ለመከራ አጋልጦ አይተዋቸውም፡፡ በክርስቶስ አማካይነት ወደ እርሱ የቀረበችም ነፍስ ሁሉ እንደ ዕንቁ የከበረች ነች፡፡ እንደነዚህ ያሉትን ነፍሳት “መርጨሃለሁና እንደ ቀለበት ማተሚያ አደርግሃለሁ” ይላቸዋል፡፡ CLAmh 203.2