የተሟላ ኑሮ

183/201

ከፍተኛው ክብር

ከሰማይ ስጦታዎች ሁሉ የክርስቶስ ሥቃይ መካፈል ከከሁሉም የበለጠ ከባድ አደራና ከፍተኛ ክብር ነው፡፡ ወደ ሰማይ ያረገው ሄኖክ ወይም በእሳት ሰረገላ ያረገው ኤልያስ በክብር በግዞት ውስጥ ከሞቱ ከዮሐንስ መጥመቁ አይበልጡም፡፡ “ይህ ስለክርስቶስ ተሰጥቶአችኃልና ስለእርሱ መከራ ደግሞ ልትቀበሉ እንጂ በእርሱ ልታምኑ ብቻ አይደለም፡፡ “(ፊልጵስዩስ 1፡29) CLAmh 195.7

ብዙዎች ሰዎች ለወደፊቱ ቁርጥ ሀሳብ ለማድረግ ያቅታቸዋል፡፡ ኑሮአቸው ያልተደላደለ ነው፡፡ በኋላ የሚከተለውን ስለማያውቁ መቅበጥበጥና ሥጋት ያድርባቸዋል፡፡ CLAmh 195.8

የእግዚአብሔር ልጆች በዚህች ምድር መናኝ መሆናቸውን አንርሳ፡፡ የራሳቸውን ኑሮ ለመወሰን ጥበብና ብልሃት የለንም፡፡ CLAmh 196.1

የወደፊቱን መተንበይ አንችልም፡፡ “አብርሃም የተባለው ርስት አድርጎ ሊቀበለው ወዳለው ስፍራ ለመውጣት በእምነት ታዘዘ፡፡ ወዴትም እንደሚሄድ ሳያውቅ ወጣ፡፡” (ዕብ 11፡8) ፡፡ CLAmh 196.2

ክርስቶስም ቢሆን በዚህች ምድር ሳለ ለወደፊት አልተጨነቀም ነበር፡፡ የአብን ዕቅድ ለመከተል ስለወሰነ አብ በየዕለቱ የሚሰራውን ይገልጥለት ነበረ፡፡ እኛም ኑሮአችንን እንደፈቃዱ እንድናካሄድ በእግዚአብሔር ማመን አለብን፡፡ አንተ ምራን ብለን ካመንንበት መንገዶቻችንን ያቀናልናል፡፡ CLAmh 196.3

ብዙ ሰዎች የወደፊቱን በማሰብ በደስታ ህልም ሲዋኙ ሳይሳካላቸው ይቀራል፡፡ እግዚአብሔር ያስብላችሁ ዘንድ ሁሉንም ለእርሱ ተውለት፡፡ “የቅዱሳንን እግር በሚጠብቀው” በእርሱ መሪነት እንደትንሽ ልጅ እመኑ፡፡ (1ኛ ሳሙኤል 2፡9) ፡፡ የእግዚአብሔር ልጆች ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ የመመልከት ችሎታ ቢኖራቸው ኖሮ የእግዚአብሔርን አመራር በወደዱት ነበረ፡፡ CLAmh 196.4

የእርሱ የሥራ ባልደረባ የሚሆን ክብር ሲቀዳጁ በተደሰቱ ነበረ፡፡ CLAmh 196.5

ክርስቶስ ደቀመዛሙርቱን ሲመርጥ በዚህ ምድር ይመቻቸኋዋል ብሎ አላጓጓቸውም፡፡ በዓለም ክብር እንደሚያገኙ ተስፋ አልሰጣቸውም፡እነርሱም ይህንን ማግኘት ይገባናል የሚሉት ነገር አልነበራቸውም፡፡ CLAmh 196.6

ማቴዎስን ከቀረጥ መሰብሰቢያው ሥፍራ ተቀምጦ ሲያየው” ተከተለኝ አለው ፤ ሁሉንም ተወ፤ ተነስቶም ተከተለው፡፡” (ሉቃስ 5፡27፣28) CLAmh 196.7

ማቴዎስ ለሥራ ከመሰለፉ በፊት ከቀረጥ የሚገኘውን ገንዘብ ያህል በደቀመዛሙርትነት ሲሰራ ለመቀበል አልጠየቀም፡፡ ሳይጠይቅ ወይም ሳያመነታ ተከተለው፡፡ ከጌታ ጋር ሆኖ ቃሉን መስማትና ከእርሱ ጋር መሥራት በቂ ነበረ፡፡ CLAmh 196.8

ከዚያም በፊት የተጠሩት ደቀመዛሙርት ሁሉ እንደዚሁ ነበሩ፡፡ ክርስቶስ ጴጥሮስና ጓደኞቹ ተከተሉኝ ሲሏቸው ጀልባቸውንና መረባቸውን ትተው ተከተሉት፡፡ CLAmh 196.9

ከደቀመዛሙርቱ መካከል አንዳንዶች የእነርሱን እጅ የሚጠባበቁ ዘመድ ወዳጅ ነበራቸው፡፡ግ ን መድኃኒታችን ሲጋብዛቸው ዘመዶቼ ምን ይበጃችኃል? እኔስ እንዴት ልኑር? ብለው አላወላወሉም፡፡ CLAmh 197.1

ጥሪውን አክብረው ተከተሉት፤ ክርስቶስ በኋላ ፤ “ያለኮረጆና ያለከረጢት፤ ያለጫማም በላክኋችሁ ጊዜ አንዳች ጎደለባችሁን?” ባላቸው ጊዜ “ምንም አልጎደለብንም “አሉ፡፡ (ሉቃስ 22፡25) CLAmh 197.2