የተሟላ ኑሮ
ባልየው እንዴት ሊረዳ እንደሚችል
የእናቲቱ ጥንካሬ በጥንቃቄ መያዝ አለበት፡፡ በከባድ ሥራ ኃይልዋ እንዳይባክን ሥራዋ ሊቀነስላት ይገባል፡፡ ብዙውን ጊዜ ባልዮው የቤተሰቡ ጤንነት የሚጠበቅበትን የጤና ሕግ አያውቅም፡፡ ቤተሰቡ የሚተዳደርበትን ገንዘብ ለማግኘት ወይም ሐብት ለማጠራቀም እየተሳመጠ ወይም በችግር ማጥ ውስጥ ገብቶ እየዛገጠ ልትረዳ በሚገባት ጊዜ በባለቤቱ ላይ ኃይልዋን ሁሉ የሚሟጥጥ ሸክም ስለሚጥልባት ድካምና ሕመም ያጠቃታል፡፡ CLAmh 23.3
ብዙ ባሎች ወይም አባቶች ከታማኙ የበግ እረኛ ተጠንቃቂነት ጠቃሚ ትምህርት ለማግኘት ይችላሉ፡፡ ያዕቆብ አስቸጋሪ የሆነ የጥድፊያ ጉዞ እንዲጀምር በተጠየቀ ጊዜ የሚከተለውን መለሰ፤ CLAmh 23.4
“ልጆቹ ደካሞች እንደሆኑ ታውቃለህ፤ በጎችና ላሞችም ግልገሎቻቸውን ያጠባሉ፤ ሰዎችም በችኮላ አንድ ቀን የነዱአቸው እንደሆነ ከብቶቹ ሁሉ ይሞታሉ፡፡ እኔ እስክደርስ ድረስ ከፊቴ ባሉት በእንስሳቱ እርምጃና በህፃናቱ እርምጃ መጠን በዝግታ እከተላለሁ፡፡” ዘፍ 33፡13-14 CLAmh 23.5
በሕይወት አስቸጋሪ ጉዞ ላይ ባልዮው ወይም አባትዮው መንገደኞቹ በሚችሉት መጠን በዝግታ ይምራ፡፡ የሐብትና የኃይል እሽቅድድም በሞላበት ዓለም ባለቤትዮው እርምጃውን መመጠንና ጐን ለጐን እንድትራመድ የተሰጠችውንም (ባለቤቱን) ማጽናናትና መደገፍ አለበት፡፡ CLAmh 24.1