የተሟላ ኑሮ

162/201

ሰው በእግዚአብሔር አምሳል ተፈጠረ

ሰው ሲፈጠር የእግዚአብሔር አቋም ተገለጠ፡፡ እግዚአብሔር ሰውን በአምሳሉ ሲፈጥረው ሰብአዊ ቅርጽ እንከን የሌለበት ፍጹም ነበር፡፡ ግን ሕይወት አልነበረበትም፡፡ እግዚአብሔር ራሱ በቅርጹ ላይ የሕይወት እስትንፋስ እፍ ቢልበት ሰው ሕያውና ጠቢብ ሆነ፡፡ CLAmh 172.6

የሰው አካል ልዩ ልዩ ክፍሎች የተመደበላቸውን ሞያ ማከናውን ጀመሩ፡፡ ልብ፤ደም መልስ ደም ቅዳ (አርቴሪስና ቬንስ) መላስ፤ እጆች፤እግሮች፤ሕዋሳት የአእምሮ ክፍሎች፤ሁሉም ተግባራቸውን ጀመሩ፡፡ በሕግና በሥርዓትም ተመሩ፡፡ በክርስቶስ በቃሉ አማካይነት እግዚአብሔር ራሱ ሰውን ፈጠረ፡፡ ኃይልና ማስተዋልንም አደለው፡፡የጠቢባን ጠቢብ ፍጥረትን ሁሉ እንደሚገዛ ተፈጥሮ ትመሰክራለች፡፡ CLAmh 172.7

በሚስጥር ስንፈጠር ከእግዚአብሔር አንሰወርም፡፡ ያልተሟላ ቢሆነም አቋማችን በእግዚአብሔር ዘንድ ግልጥ ሆኖ ይታያል፡፡ የአካል ክፍሎቻችን ገና ሳንፈጠር በእግዚአብሔር መጽሐፍ ተመዝግበዋል፡፡ ከሌላው ፍጥረት አብልጦ እግዚአብሔር ሰውን የሥራው መደምደሚያ አደረገው፡፡ አሳቡን እንዲያሟላለትና ክብሩን እንዲገልጥለት አድርጎ ፈጠረው፡፡ ግን ሰው ራሱን ከአምላክ ጋር ማስተካከል የለበትም፡፡ CLAmh 172.8

እግዚአብሔር የፈጠራቸውን ነገሮች መሣሪያ ያደርጋቸዋል፡፡ በጠፈጥሮ ሕግ አማካይነት ይሠራል፡፡ CLAmh 173.1

ራሳቸው በራሳቸው አይሰሩም፡፡ ተፈጥሮ ራሷ በሕግና በሥርዓት የሚያድተዳድራት አንድ ኃይል መኖሩን ትመሰክራለች፡፡ CLAmh 173.2

“በሰማይና በምድር በባሕርና በጥልቆች ሁሉ እግዚአብሔር የወደደውን ሁሉ አደረገ፡፡ እርሱ ብሎአል፤ሆኑም፤እርሱ አዞአል፤ተፈጠሩም፡፡ ለዘለዓለም አቈማቸው ትእዛዝን ሰጠ፤አያልፉም፡፡ (መዝሙር 135፡6፤ ምዕራፍ 145፡5-6) ፡፡ CLAmh 173.3

መሬት በየዓመቱ በረከት የምታሳፍሰንና በፀሐይ ዙሪያ የምትዞር እንዲሁ በልማድ አይደለም፡፡ መሬታችንን (ይህችን ፕላኔት) የኃያሉ እግዚአብሔር እጅ ይመራታል፤መሬት በዛቢያዋ ላይ እንድትሽከረከርና ከመንገዷ እንዳትወጣ የሚያደርጋት የእግዚአብሔር ኃይል ነው፡፡ ፀሐይ በሰማይ ላይ እንድታበራ የሚያደርጋትም እግዚአብሔር ነው፡፡ የሰማይን መስኮቶች ከፍቶ ጠልና ዝናብ ያወርዳል፡፡ CLAmh 173.4

“አመዳዩን እነደበዘቶ ይሰጣል፡፡ ጉሙን እንደ ዓመድ ይበትነዋል፡፡” (መዝሙር 146፡16) ፡፡ CLAmh 173.5

“ድምጹን ባሰማ ጊዜ ውሆች በሰማይ ይሰበሰባሉ፡፡ ከምድርም ዳር ደመናትን ከፍ ያደርጋል፡፡ ነፋስንም ከቤተ - መዛግብቱ ያወጣል፡፡ (ኤርሚያስ 10፡13) ፡፡ CLAmh 173.6

ቡቃያ የሚበቅለው፤ ቅጠሉ የሚለመልመው፤ አበባው የሚፈካው፤ ፍሬ የሚንዠረገገው በእርሱ ኃይል ነው፡፡ CLAmh 173.7