የተሟላ ኑሮ

160/201

የየሱስ አርኣያነት

ደቀመዛሙርቱ ለሦስት ዓመታት የየሱስ ድንቅ አርአያነት አልተለያቸውም ነበር፡፡ በየዕለቱ ከእርሱ ጋር ይራመዱና ይነጋገሩ ነበር፡፡ ያዘኑትንና የደከሙትን አይዟችሁ ሲል ይሰሙት ነበር፡፡ በታመሙትና በደዌያን ላይ የማዳን ኃይሉን ይገልጥ ነበር፡፡ የሚሄድበት ጊዜ ሲደርስ ስራውን በእርሱ ስም እንዲያካሂዱ ኃይልና ጸጋን አደላቸው፤የመዳንና የፍቅር ወንጌሉን ከጽንፍ እስከ አጽናፍ እንዲያዳርሱ አደራ ጣለባቸው፡፡ መድኃኒታችን ለዘለአለም እንደማይለያቸው ተስፋ ሰጣቸው፡፡ CLAmh 167.5

ሥጋ ለብሶ ከሰዎች ጋር ከነበረበት ጊዜ ይልቅ በመንፈስ እንደሚቀርባቸው ተስፋ ሰጣቸው፡፡ ደቀመዛሙርቱ የሰሩትን ሥራ እኛም መሥራት አለብን ፡፡ እያንዳንዱ ክርስቲያን የወንጌል መልክተኛ ነው፡፡ እርዳታን የሚሹትን በመታዘዘና በመራራት መርዳት ይገባናል ፡፡ CLAmh 167.6

ለራሳቸን ብቻ ማሰብን ገለል አድርገን በሰባዓዊ ዘር ላይ የወደቀውን መከራ ለማቃለል መሞክር አለብን፡፡ CLAmh 167.7

ማንም ሰው የየራሱ የሥራ ድርሻ አለለት ፡፡ ማንም ቢሆን ለክርስቶስ የሠራው ሥራ የሌለው አይምሰለው፡፡ ክርስቶስ ከእያንዳዱ ሰው ጋር ይተዋወቃል ፡፡ እኛን የሰማይ ቤተስብ አባል ለማድረግ እርሱ የምድራዊ ቤተስብ አባል ሆነ፡፡ CLAmh 168.1

የሰው ልጅ በመሆኑ የአዳም ልጆች ሁሉ ወንድም ነው ፡፡ ተከታዮቹ በዙሪያቸው ከሚጠፋው ዓለም የተገለሉ መሰሎ አይሰማቸው፡፡ ስብዓዊ ዘር ሁሉ አባል ናቸው፡፡ አምላክ የሚመለከታቸው የኃጢዓንም የቅዱሳንም ወንድሞች አደርጎ ነው፡፡ በሚሊዮን የሚቁጠሩ በሽተኞች፤ ማይማንና ኀጥአን የሱስ እንደሚወዳቸው አያውቁም፡፡ CLAmh 168.2

ሁኔታው ሁሉ ተለወጦ አኛ በእነርሱ ቦታ ብንሆን ምን እንዲያደርጉልን እንፈልጋለን? ችሎታችን የፈቀደልንን ያህል ልናደርግላቸው ይገባናል። ሊያስፈርድልን የሚችል ክርስቶስ ያቋቋመልን የኑሮ መመሪያ” ሰዎቸ ሊያደርጉላቸሁ የምትፈልጉትን እናንተ ደግሞ አድርጉላቸው “ይላል፡፡ (ማቴዎስ 7፡12) ፡፡ CLAmh 168.3

በትምህርትም ቢሆን በሥልጣኔ፣ በጠባይ፣ በክርስትና አስተዳድግ፣ በሃይማኖት ትምህርት በኩል ከሌሎች የተሻለ ዕድል ካጋጠመን ከእኛ በታች ላሉት ዕዳ አለብን፡፡ CLAmh 168.4

ብርቱዎች ከሆንን ደካሞቹን መደገፍ አለብን፡፡ CLAmh 168.5

ዘለዓለምም በሰማይ ባለው በእግዚአብሔር ፊት የሚቆሙ የክብር መላዕክት ታናናሾችን በማገልገላቸው ይደሰታሉ፡፡ መላዕክት እርዳታቸው በጣም በሚፈለግበት ቦታ ይገኛሉ፡፡ ከራሳቸው ጋር ከባድ ጦርነት ላለባቸው ነፍሳት፤አከባቢያቸው ተስፋ ላስቆረጣቸው ሰዎች ይደርሱላቸዋል፡፡ ጉድለት ላለባቸውና ጠባያቸው ላልተሟላ ሰዋች የተለየ ጥንቃቄ ያደርጉላቸዋል፡፡ CLAmh 168.6

ኃጢያት የሌለባቸው የሰማይ መላእክት አንዳንድ ኩሩዎች ወራዳ ሥራ አድርገው የሚገምቱትን ጎስቋሎችንና በማንኛውም ነገር ዝቅ ያሉትን ያገለግላሉ፡፡ እኛ ጠፍተን ሳለን የሱስ በሰማይ መንበሩ ለመኖር አልፈለገም የሰማይን አደባባይ ለቅቆ ለመሰደብና ለመናቅ የሀፍረት ሞት ለመሞት ወደ ምደር መጣ፡፡ የሰማይ ኃብት ሁሉ በእጁ እያለ ከበርቴ ሳለ በድኀነቱ ሊያበለጽገን ድሃ ሆነ፡፡ በተራመደበት ፈለግ መራመድ አለብን፡፡ CLAmh 168.7

የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ ሰው ሁሉ ሰውና እግዚአብሔርን በሚገኘው ሰንሰለት ውሰጥ እንደ አንድ ቀለበት መሆን አለበት፡፡ በክርስቶስ የምህረት አዋጅ ውሰጥ ተካፋይነት ሊኖር ይገባል፡፡ CLAmh 168.8

ዛሬ ብዙ ህዝብ ክርስቶስን ለማየትና ለመስማት ወደምድረ በዳ አይሄዱም፡፡ ድምጽ በመንገድ አይሰማም፡፡ CLAmh 169.1

“የናዝሬቱ የሱስ በዚህ አለፈ” የሚል ድምጽ ከመንገድ ዳር አይሰማም፡፡ (ሉቃስ 18፡37) ፡፡ ግን ዛሬም በየመንገዱ ዳር አለ፡፡ ክርስቶስ አይታይም እንጂ በየመንገዱ ይራመዳል፡፡ የምህረት መላእክት ይዞ ወደቤታችን ይመጣል፡፡ ብንቀበለው በመካከላችን ተገኝቶ ይባርከናል፤ይፈውሰናልም፡፡ CLAmh 169.2