የተሟላ ኑሮ
ጋኔንን ማውጣት
በቅፍርናሆም ቤተ ጸሎት የሱስ የኃጢአትን ተገዥዎች ነፃ ስለማውጣት ተግባሩ ይናገር ነበር፡፡ በአንድ አስደንጋጭ ጩኸት ምክንያት ንግግሩ ተቋረጠ፡፡ አንድ ዕብድ “ተው የናዝሬቱ የሱስ ሆይ፤ ከአንተ ጋር ምን አለን? ልታጠፋን መጣህን?” እያለ በሕዝቡ መካከል ይወራጭ ነበር፡፡ ንግግሩን በመቀጠል “ማን እንደሆን አውቄአለሁ አንተ የእግዚአብሔር ቅዱስ” አለ፡፡ የሱስም “ዝም በል ከእርሱም ውጣ ብሎ ገሰጸው፡፡ ጋኔኑም በመካከላቸው ጥሎት ሳይጎዳው ከእርሱ ወጣ፡፡” (ሉቃስ 4፡34፣35) ፡፡ CLAmh 161.7
የዚህ ሰውም የሥቃዩ ጠንቅ የኑሮው ይዞታ ነበር፡፡ የኃጢአትን ጊዜያዊ ደስታ በመቅመስ በምቾት ለመኖር አስቦ ነበር፡፡ የተፈጥሮ ጨዋነቱን ራስን አለመቆጣጠርና ንዝህላልነት በዘበዘበት፡፡ ጸጸት ወደኋላ ሆነ፡፡ CLAmh 162.1
የሰውነት ደረጃውን ለመመለስ ሀብታና ደስታን ገለል ማድረግ ሲገባው በዲያቢሎስ እጅ ውስጥ እንዳይወጣ ሆኖ ገባ፡፡ CLAmh 162.2
በጌታ ፊት ሲቀርብ ነጻነትን ሽቶ ነበር፤ ዲያብሎስ ግን የመድኅንን ኃይል ሲቋቋም ሞከረ፡፡ ሰውየው ከየሱስ ዘንድ ርዳታ በመጠየቅ አቤት ሊል ሲሞክር ሠይጣን የራሱን ፍላጎት አናገረው፡፡ ሰውየውም በፍርሃትና በጭንቀት ጮኸ፡፡ ጋኔን ያደረበት ሰው ነፃ ሊያወጣው በሚችል ሰው ፊት መቅረቡን በሞላ ጎደል አውቋል፡፡ ግን ወደዚያ ኃያል ፈዋሽ ለመቅረብ ሲሞክር ከፈቃዱ ውጭ የሆነ ሌላ ኃይል ወደኋላ ያዘው፡፡ የሌላ ተናጋሪ ቃላት በእርሱ አማካይነት ተሰሙ፡፡ CLAmh 162.3
በሰይጣን ኃይልና በእርሱ የመዳን ፍላጎት መካከል የተደረገው ትግል ብርቱ ነበር፡፡ CLAmh 162.4
ከሰውነት ተራ ካወጣው ጠላቱ ጋር በሚታገልበት ጊዜ የሰውየው ሕይወት ወዲያው የሚያልፍ መስሎ ነበር፡፡ ጌታ ግን በኃይልና በሥልጣን ተናግሮ ምርኮኛውን አስለቀቀው፡፡ በጋኔን ተይዞ የነበረው ሰው ራሱን የመቆጣጠር ነፃነቱ ተመልሶለት በአድናቆት በሚመለከተው ጉባዔ ፊት ቆመ፡፡ CLAmh 162.5
እግዚአብሔር ስላዳነው በደስታ አመሰገነው፡፡ በዕብደት ሲቀበዘበዝ የነበረው ዓይኑ በአስተዋይነት ብሩህ ከመሆኑም በላይ የደስታ እንባ አቅርሮ ይታይ ነበር፡፡ ሰዎቹ ከአድናቆት የተነሣ መናገር አቃታቸው፡፡ እንደገና ልብ አድርገው መናገር ሲችሉ እርስ በርሳቸው “ይህ ምንድነው? በሥላጣን ርኩሳን መናፍትን ያዝዛል፤ ይህ አዲስ ትምህርት ምንድን ነው?” በመባባል አደነቁ፡፡ CLAmh 162.6