የተሟላ ኑሮ
26—ከተፈጥሮና ከእግዚአብሔር ጋር
ክርስቶስ በዚህ ምድር ሲኖር ከእግዚአብሔርና ከተፈጥሮ ጋር ጥብቅ ግንኙነት ነበረው፡፡ በዚህ ግንኙነት የሕይወትን ኃይል ምሥጢር ገለጠልን፡፡ CLAmh 141.3
ክርስቶስ ትጉህን የማይቦዝን ሠራተኛ ነበር፡፡ ከሰዎች መካከል የኃላፊነቱን ክብደት ጠንቅቆ የተረዳ እንደ እርሱ አልተገኘም፡፡ የዓለምን ኀዘንና ኃጢአትም እንደ እርሱ የተሸከመ የለም፡፡ ለሰዎች ደኅንነት ሲል ላቡን አንጠፍጥፎ ከልቡ የሠራ እንደ እርሱ ማንም የለም፡፡ ግን ጤናው የተሟላ ነበር፡፡ በአካልም በመንፈስም እንደሚሠዋው ጥቦት “ያለነውር ነበር” ፡፡ (1ኛ ጴጥሮስ 1፡19) ፡፡ በአካሉም፣ በመንፈሱም የተሟላ በመሆኑ የእግዚአብሔርን ሕግ አሟልቶ ለመገኘት ለሰብዓዊ ፍጡር ሁሉ አርኣያ ነው፡፡ CLAmh 141.4
ሰዎች የክርስቶስን ገጽ ሲመለከቱ መለኮታዊነት ያንዣበበበት ሆኖ አገኙት፡፡ በጠባዩ ጨዋነትና በትሕትናው የተደበቀ ኃይል እንዳለው ቢያውቁም ያ ኃይል አልተሠወረባቸውም፡፡ በሥራው ዘመን ሁሉ ግብዞችና ተመጻዳቂዎች ሕይወቱን ለማጥፋት ይከታተሉት ነበር፡፡ በንግግሩ ሊያጠምዱት የሚሞክሩ ሰላዮች ሁል ጊዜ ይከታተሉት ነበር፡፡ በጣም የተማሩና የተመራመሩት ሰዎች በክርክር ሊያጠቁት ይጥሩ ነበር፡፡ CLAmh 141.5
ግን በምንም በኩል አልተሳካላቸውም፡፡ ትሁቱ የገሊላ መምህር በትምህርት ከእነርሱ ልቆ ስላገኙት አፍረው ዝም አሉ፡፡ የክርስቶስ ትምህርት ከዚያ በፊት ሰው ያላወቀው ጣፋጭነትና ኃይል አለው፡፡ ጠላቶቹ ሳይቀሩ “እንደዚህ ሰው ማንም ተናግሮ አያውቅም” አሉ፡፡ (ዮሐንስ 7፡46) ፡፡ CLAmh 142.1