ወደ ክርስቶስ የሚመራ መንገድ

2/27

ምዕራፍ 1 - የእግዚአብሔር ፍቅርለሰዎች

ተፈጥሮ እና እራሱን ለፍጡራኑ የገለጠበት መለኮታዊ መንገድ የእግዚአብሔርን ፍቅር ይመሰክራሉ፡፡ በሰማይ ያለው አባታችን የህይወት፣ የጥበብና የደስታ ምንጭ ነው.እስቲ አስደናቂና ውብ ወደሆነው ተፈጥሮ ይመልከቱ፡፡ ይኸው ወደር የማይገኝለት ተፈጥሮ ለሰብዓዊው ፍጡር ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ ህይወት ላላቸው ፍጡራን እጅግ የተስማማና የደስታ ምንጭም መሆኑን ያስቡ፡፡ ምድርን ደስ የሚያሰኘው የፀሐይ ብርሃን እና መሬቱን የሚያረሰርሰው ዝናብ፣ ኮረብታው፣ ባሕሩናመስኩ ሁሉም በአንድነት ስለ ፈጣሪ ፍቅር ይናገራሉ፡፡ ለፍጡራኑ የሚያስፈልገውን ሁሉ በየዕለቱ የሚያሟላው እግዚአብሔር ነው፡፡ባለመዝሙሩ ባማሩ ቃላት እንዲህ ይላል፡- ክየመ 7.1

«የሁሉ ዓይን አንተን በተስፋ ይጠብቃል፤
አንተም ምግባቸውን በወቅቱ ትሰጣቸዋለህ፡፡
አንተ እጅህን ትዘረጋለህ፤ የሕያዋን
ፍጥረታትንም ሁሉ ፍላጎት ታረካለህ፡፡»
ክየመ 7.2

(መዝ. 145: 15-16)

እግዚአብሔር ሰውን ፍጹም፣ ቅዱስ እና ደስተኛ አድርጎ ነበር የፈጠረው፡፡ምድር በፈጣሪዋ እጅ በተሰራችበት ጊዜ ውብ ከመሆኗ ባሻገር የመበስበስ፣ የእንከንም ሆነ የእርግማን ጥላ አላጠላባትም ነበር፡፡ ነገር ግን የፍቅር ሕግ የሆነውን አምላካዊ ሕግ መተላለፍ በምድር ላይ ዋይታንና ሞትን አመጣ፡፡ሆኖም ግን የኃጢአትን ውጤት ተከትሎ በመጣው ሥቃይ መሃል እንኳ የእግዚአብሔር ፍቅር ተገልጾአል፡፡ በርግጥ እግዚአብሔር በሰው ምክንያት ምድርን እንደረገማት እናነባለን (ዘፍ. 3:17)፡፡ እሾህና አሜኬላ፤ ችግርና ፈተና የሰብዓዊውን ህይወት አድካሚና ጥንቃቄ የበዛበት ይሆን ዘንድ መንስዔ ቢሆንም ነገር ግን ይህ የሆነው ለበጎ ነው ምክንያቱም እግዚአብሔር ይህን ዕቅድ የዘረጋው ሰብዓዊው ፍጡር ካወደቀሰት ኣባቅትወጥቶ ኃኣት ካጎበጠው ማንነት ቀና የሚልበት አንዱ ሥልጠና ይሆንለት ዘንድ በማሶብ ነው። ምንም እንኳ ምድር በኃጢአት ብትወድቅም ሁሉም ነገር በሐዛንና ምስቅልቅል ብቻ አልተዋጠም በራሷ በተፈጥሮ ውስጥ የተስፋ መልእክቶችንና መጽናናትን እናገኛለን። አሚካላው በአበባ እንዲሁም እሾሁ በጽጌረዳ ተሸፍኗል። ክየመ 7.3

«እግዚኣብሔር ፍቅር ነው» የተሰኘው ቃል በእያንዳንዱ እንቡጥ ኣበባና አረጓዴው መስክ ላይ ይነበባል» በአስደሳች ድምፃቸው ልዩ ዝማራ የሚያሰሙት ተወዳጅ አዕዋፍ፣ ፍጹም በሆነው መዓዛቸው አየሩን የሚያውዱ ውብ አበቦችና አረንጓዴ ቀለማትኝ የተላበሱ ግዙፎቹ የዱር ዛፎች፣ አፍቃሪና ጥንቃቄ የተሞላው አባት ልጆቹ ደስ ይሰኙ ዘንድ ያለውን ምኞት ይመሰክራሉ። ክየመ 8.1

አሜኬላው በአበባ አንዲሁም እሾሁ በጽጌረዳ ተሸፍኗል።

የእግዚአብሔር ቃል አምላካዊውን ባህሪ ይገልጻል፡ ወሰን ስለሌለው ፍቅሩና ሀዘኔታው ያወጀው እራሱ ይኸው አምላክ ነው» ሙሴ ክብርህን አሳየኝ» ብሎ በጸለየ ጊዜ «መልካምነቴ ሁሉ በፊትህ እንዲያልፍ አደርጋለሁ። (ዘፀ. 33፡18-19) በማለት ነበር እግዚአብሔር የመለሰለት። ይህ የእርሱ ክብር ነው። ጌታ በሙሴ ፊት እያለፈ እንዲህ ሲል አወጀ፡- «እግዚአብሔር ርኅሩኅ ቸር አምላክ፣እግዚአብሔር ለቁጣ የዘገየ፣ ፍቅሩና ታማኝነቱ የበዛ፣ ፍቅርን ለሺህዎች የሚጠብቅ፣ ክፋትኝ ዐመጽንና ኃጢአትን ይቅር የሚል» (ዘፀ. 34 6-7)። እርሱ ቸርና ርኅሩኅ፣ ከቁጣ የራቀ» «ምህረት በማድረግ ደስ የሚለው ነው (ዮናስ 420 ሚልክ. 7፡8)። ክየመ 8.2

እግዚአብሄር ሊያተውለው በሚችለው በተፈጥcና ጥልቀት ባሳቸው ሰርሳሪጎ በተሞሉ ምድራዊ ትስስሮች አማካኝነት እራሱን ይገልጽልን ዘንድ ሽቶአል። ቢሆንም ግን አነrህ ነገርች የአርሶኝ ፍቅር የጨካሉት ፍጽምና በጎደለው መልኩ ነው። ምንም እንኳ እነዚህ ሁሉ ማiረጃዎች ቢሰጡም የመልካም ጠላት የሆነ ኃይል የሰዎች አእምሮ እንዲታሠር አደረገ። በዚህ ሁሉም እግዚኣብሄርን በፍርሃትና በመርበድበድ ከመመልከታቸው በተጨማሪ እርሱን እንደ ጨካኝና ይቅር እንደማይል አድርገው አሰቡት። እግዚኣብሔር አለልክ ጥብቅ ፣ ከባድ ፍርድ የሚሰጥ፡ እንዲሁም ጨካኝ ፈራጅና ርህሪሄ ቢስ ዓይነተኛ ባህሪይው እንደሆነ አድርጎ ሰይጣን በአእምሮአቸው ውስጥ በመሳል አሳታቸው። እግዚኣብሄር በሰዎች ሳይ መፍረድ ሲል በቅናት ዓይነት ስህተታቸውን ብቻ የሚፈልግ አምሳክ ተደርጎ ተሳለ። ይህን ጽልመት የተሞላ ጥሳ ለመግፈፍ እና ዘላለማዊውን አምላካዊ ፍቅር ለማሳየት ሲል ኢየሱሰ ከሰዎች ጋር ሊኖር ወደዚህ ምድር መጣ። ክየመ 9.1

የእግዚኣብሔር ልጅ ኣባቱን ሊገልጥ ከሶማይ ወረደ «ከቶንም እግዚኣብሔርን ያየ ማንም የለም፥ ነገር ግጎ በአብ እቅፍ ያለው ኣንድያ ልጁ የሆነ አምላክ አርሶ ገለጠው (ዮሐ 1:18):: «ከአብ ሌላ ወልድን የሚያውቅ የለም ከወልድና ወልድ ራሱ ፈቅዶ ካሚገልጥላቸው ሌላ ኣብ የሚያውቅ የለም» (ማቲ l:17)። ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ አብን አሳየን ብሎ ኢየሱሰኝ በጠየቀ ጊዜ «አንተ ፊልጶስ! ይህን ያህል ጊዜ ከኣንታ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቶአል፤ አንዲት አብን አሳየኝ ትሳለህ?» (ዮሐ. 14:8-9) በማለት ነበር የመሰሶሰት። ክየመ 9.2

ኢየሱሰ ስለምድራዊ አገልግሎቱ ሲገልጽ እንዲህ ነበር ያለው “የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድሆች ወንጌልን እንድሰብክ፣ እርሱ ሰቶኛልና፤ ለታሰሩት መፈታት፡ ለታወሩትም ማየት፥ እንዳውጅ፡ የተጨቆኑትን ነጻ አንዳወጣ፡ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እንዲወጅ ልኮኛል። (ሉቃ 4፡18)። ይህ እንግዲህ የእርሱ ስራ ነበር። እርሱ መልካም እያደረገና በሰይጣን ግዞት ስር ወድቀው የነበሩትን እየፈወሰ በየስፍራው ተንቀሳቀሰ። እርሱ በመሃላቸው እየፈወሰ ያልፍ ስለነበረ፡ የህመምና የማቃሰት ድምጽ የሚሰማበት አንድም መንደር አልተገኘም ነበር፡፡ ሥራዎቹ በመለኮት ለመቀባቱ ማረጋገጫ በመሆን ፍቅር፣ ምህረትና ርኅራኄ በእያንዳንዱ የህይወቱ እንቅስቃሴ ተገልጾ ይታይ ነበር፡፡ ልቡ ለሰዎች ልጆች በፍቅርና በርኅራኄ ይፈስ ነበር፡፡ እርሱ የሰዎችን ፍላጎት ለመድረስ ይችል ዘንድሰብዓዊውን ተፈጥሮ ወሰደ:: እጅግ ድኾችና እራሳቸውን ዝቅ ያደረጉ እርሱን ቀርቦ ለማናገር ፍርሃት አልነበራቸውም፡፡ እንዲያውም ትናንሽ ብላቴናዎች ሳይቀሩ በእርሱ ተስበው ነበር፡፡ ህጻናት እንኳን ሳይቀሩ በጭኖቹ ላይ በመውጣት፣ በፍቅር የተሞላ ቸርና ርኅሩኅ እንዲሁም አስተዋይ የሆነውን የፊቱን ገጽታ ለመመልከት ችለው ነበር፡፡ ክየመ 9.3

ኢየሱስ የእውነትን ቃል ሁልጊዜ በፍቅር ይናገር ነበር:: እርሱ ከሰዎች ጋር ለሚኖረው ግንኙነት ትኩረት የሚሰጥ፣ ደግ፣ አሳቢና አስተዋይ ነበር፡፡ኢየሱስ ግትር አልነበረም፣ ለሆደ ባሻው አላስፈላጊ ጠንካራ ቃላትን በመሰንዘር እንዲታወክ አድርጎ አያውቅም፣ ሰብዓዊውን ደካማነትም አልተቸም፡፡ እውነትን በግልጽ ይናገር ነበር፤ ይህንን ያደርግ የነበረው ግን ሁልጊዜ በፍቅር ነበር፡፡ ግብዝነትን፣ አለማመንን እንዲሁም ታማኝ አለመሆንን ቢያወግዝም፣ ግሳጼ ሲያደርግ ሳለ ግን በድምፁ ላይ ሳግ ይሰማ ነበር፡፡ መንገድ፣ እውነትና ህይወት የሆነውን ኢየሱስ ለመቀበል አሻፈረኝ ላለችው ለሚወዳት ከተማ ኢየሩሳሌም አልቅሶአል፡፡ ሕዝቡ አዳኙን ቢቃወምም እርሱ ይመለከት የነበረው በሀዘኔታና በፍቅር ዓይን ነበር፡፡የእርሱ ህይወት እራስን በመካድና ለሌሎች ደግ በማሰብ የተሞላ ነበር፡፡እያንዳንዱ ነፍስ በእርሱ ዘንድ የከበረ ነበር፡፡ መለኮታዊውን ክብር ከምንም ሳይቆጥር ነገር ግን ከፍ ባለ ፍቅር እራሱን ለእያንዳንዱ የእግዚአብሔር ቤተሰብ ዝቅ ያደረገው አዳኝ፤ እያንዳንዱን ሰው ሊያድነው ዓላማው የሆነውን የወደቀ ነፍስ በመመልከት ነበር፡፡ ክየመ 10.1

ይህ በክርስቶስ ህይወት የተገለጠው ባሕርይ የራሱ ባህሪይ ነው።ደግሞም የእግዚአብሔር ባህሪይ ነው። ከአብ ልብ በመመንጨት በክርስቶስ የተገለጠው መለኮታዊው ርኅራኄ ወደ ሰው ልጆች ይፈሳል፡፡ አፍቃሪና ርኅሩኅ የሆነው አዳኝ «በሥጋ የተገለጠ» (1ኛ ጢሞቴ. 3:16) እግዚአብሔር ነበር፡፡ ክየመ 10.2

ኢየሱስ እኛን ለመዋጀት ሲል በዚህ ምድር ላይ ኖረ፣ ሥቃይ ተቀበለ፤እንዲሁም ሞተ፡፡ እኛ የዘላለማዊው ደስታ ተካፋዮች እንሆን ዘንድ እርሱ «የሐዘን ሰው» ሆነ፡፡ በጸጋና በእውነት የተሞላው የተወደደ ልጁ ቃላት ሊገልጹት ከማይችል ክብር ወጥቶ በኃጢአት ወደ ረከሰው፣ በሞት ጥላ ሸለቆና በእርግማን ጽልመት ወደ ተዋዋጠው ወደዚህ ምድር ይመጣዘንድ እግዚአብሔር ፈቀደ።የእግዚአብሔርን የፍቅር እቅፍ፣የመላእክትን ክብርና አምልኮ ትቶ ሥቃይ፣ ሐፍረት፣ ስድብ፣ ውርደት፣ጥላቻና ሞት ወደ መቀበል ያመራ ዘንድ የአባቱ ፈቃድ ሆነ፡፡ «በእርሱ ላይ የወደቀው ቅጣት ለእኛ ሰላም አመጣልን፤ በእርሱም ቁስል እኛ ተፈወስን» (ኢሳ. 53:5)፡፡ እነሆ እርሱን በምድረበዳ፣ በጌተሰማኔ፣ በመስቀል ላይ ተመልከቱት! እንከን የሌለበት የእግዚአብሔር ልጅ የኃጢአትን ቀንበር እርሱ ራሱ ወሰደ፡ ኃጢአት በእግዚአብሔርና በሰው መካከል የሚያደርገው አስፈሪ መለያየት ከእግዚአብሔር ጋር አንድ በሆነው በእርሱ ነፍስ ውስጥ ዘልቆ ተሰማው።ይህን ተከትሎ «አምላኬ፣ አምላኬ፣ ለምን ተውኸኝ» (ማቴ. 27፡46) የሚል ታላቅ የሕማም ጩኸት ከአንደበቱ ወጣ፡፡ ይህ እንግዲህ የእግዚአብሔርን ልጅ ልብ የሰበረውና አስፈሪ ተፈጥሮ የተላበሰው፣ ነፍስን ከእግዚአብሔር የሚነጥለው የኃጢአት ሸክም ነበር፡፡ ክየመ 11.1

ኢየሱስ የእውነትን ቃል ሁልጊዜ በፍቅር ይናገር ነበር።

ነገር ግን ይህ ታላቅ መስዋዕትነት የተከፈለበት ምክንያት በአብ ልብ ውስጥ ሰውን የመውደድ ስሜት በመፍጠር እኛን ለማዳን ፈቃደኛ ለማድረግ አልነበረም:: በጭራሽ! «እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና» (ዮሐ. 3:16)። አብ እኛን የወደደበት ምክንያት ቁጣውን ለማብረድ መስዋዕት በመከፈሉ አይደለም:: ነገር ግን እርሱ ራሱ ስለሚወደን የሚከፈለውን መስዋዕት አዘጋጀ:: ክርስቶስ አማላጅ በመሆን ዘላለማዊ ፍቅሩን በኃጢአት ለወደቀው ዓለም አፈሰሰ «እግዚአብሔር በክርስቶስ ዓለምን ከራሱ ጋር» አስታረቀ (2ኛ ቆሮ. 5:19)፡፡ እግዚአብሔር ከልጁ ጋር ሥቃይ ተቀበለ፡፡ በጌተሰማኔ ህማም እንዲሁም በቀራኒዮ መስቀል ሞት ዘላለማዊው አፍቃሪ ልብ የመዋጀታችንን ዋጋ ከፈለ፡፡ ክየመ 11.2

«መልሼ ለማንሳት ህይወቴን አሳልፌ ስለምሰጥ አባቴ ይወደኛል» ዮሐ.10፡17) በማለት ኢየሱስ ተናግሮአል፡፡ ይህ ማለት «አባቴ ይወዳችኋል፤ እኔ ደግሞ እናንተን ለመዋጀት ህይወቴን አሳልፌ በመስጠቴ አብልጦ ይወደኛል፡፡ በእናንተ ምትክ በመሞቴ፣ የደኅንነታችሁ ዋስትና በመሆኔ፤ ህይወቴን በመስጠቴ፣ ዕዳችሁንና መተላለፋችሁን በመውሰዴ በእርግጥም እኔ የአባቴ ነኝ:: በእኔ መስዋዕትነት እግዚአብሔር ጻድቅ ይሆናል፤ በእርግጥም እርሱ ክየመ 12.1

በኢየሱስ የሚያምነውን ሁሉ ያጸድቃል፡፡»ከእግዚአብሔር ልጅ በቀር ደኅንነት ሊያስገኝልን የሚችል አንዳችም ሌላ የለም፡፡ በአባቱ እቅፍ ያለው እርሱ ብቻ ነው እግዚአብሔርን መተረክ የሚችለው:: የእግዚአብሔርን ፍቅር ከፍታና ጥልቀት የሚያውቀው እርሱ ብቻ ነው ሊገልጽልን የሚችል፡፡ የአብን ፍቅር በክርስቶስ ከተፈጸመው ዘላለማዊ መስዋዕት ውጪ በኃጢአት ለወደቀውና ለጠፋው ሰብዓዊ ፍጡር ሌላ ማንም ሊገልጽ አይችልም፡፡ ክየመ 12.2

«እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና» እርሱ ልጁን የሰጠው ከሰዎች ጋር አብሮ እንዲኖር ብቻ ሳይሆን ኃጢአታቸውን እንዲሸከምና ለእነርሱ መስዋዕት ሆኖ እንዲሞት ጭምር ነው:: በዚህ መልኩ እግዚአብሔር ልጁን በኃጢአት ለወደቀው ሰብዓዊ ዘር መረጠ፡፡ ክርስቶስ እራሱን ከሰዎች ፍላጎትና አንገብጋቢ ችግራቸው ጋር አዛመደ:: ከአብ ጋር አንድ የነበረው አምላክ እራሱን በማይበጠስ ገመድ ከሰው ልጆች ጋር አስተሳሰረ:: ኢየሱስ «ወንድሞች ብሎ ሊጠራን አያፍርም» (ዕብ. 2:11)፡፡ መስዋዕታችን፣ ጠበቃችንና ወንድማችን የሆነው ኢየሱስ የእኛን ሰብዓዊ ተፈጥሮ በመጋራት በአባቱ ዙፋን ፊት የሚገኝ ሲሆን፤ በተጨማሪም እርሱ ፍጻሜ ለሌላቸው ዘመናት ከዋጀው የሰው ልጆች ዘር ጋር አንድ ነው:: ይህ ሁሉ የሆነው ሰብዓዊው ፍጡር ከውድቀት ተነስቶ እንዲሁም ከኃጢአት አዘቅት ወጥቶ፣ የእግዚአብሔርን ፍቅር ያንጸባርቅና የቅድስናን ክብር ይጋራ ዘንድ ነው፡፡ ክየመ 12.3

የደኅንነታችንን ዋጋ በመክፈል ዘላለማዊው አባት ልጁ ይሞት ዘንድ በመስጠት የከፈለው ዘላለማዊ መስዋዕት፤ እኛ በክርስቶስ ምን ልንሆን እንደምንችል ከፍ ያለ ግንዛቤ ሊያስጨብጠን ይገባል፡፡ በመንፈስ የተነካው ሐዋርያው ዮሐንስ እግዚአብሔር አብ ለጠፋው ዘር ያለውን ፍቅር ከፍታ፣ ጥልቀትና ስፋት ባስተዋለ ጊዜ፣ በታላቅ አምልኮና አክብሮት ተሞልቶ ነበር፡፡ የዚህን ፍቅር ታላቅነትና ርኅሩኅነት ያስተዋለው ዮሐንስ፣ ይህን እንዴት እንደሚገልጸው ተስማሚ የሆነ ቋንቋ በማጣት፡- ‹‹የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንድንጠራ አብ አትረፍርፎ ያፈሰሰልን ፍቅር ምንኛ ታላቅ ነው!» (1ኛ ዮሐ. 3:1) በማለት ይናገራል፡፡ ይህ ለሰዎች የተሰጠው ዋጋ እንዴት ያለ የከበረ ነው! የሰው ልጆች በመተላለፋቸው ጠንቅ የሰይጣን ተገዢዎች ለመሆን በቁ፡፡ በክርስቶስ መስዋዕትነት ላይ በሚኖር እምነት ግን የአዳም ልጆች የእግዚአብሔር ልጆች ለመሆን ቻሉ፡፡ ክርስቶስ ሰብዓዊውን ተፈጥሮ በመውሰድ በኃጢአት የወደቀውን ሰብዓዊ ፍጡር ከፍ ከፍ አደረገው:: ኃጢአተኞችም ከክርስቶስ ጋር ግንኙነት በመፍጠራቸው ምክንያት በእርግጥ «የእግዚአብሔር ልጆች» ለመባል የሚገባቸው ሆነ:: ክየመ 13.1

እንዲህ ያለው ፍቅር አቻ የለውም፡፡ የሰማያዊው ንጉሥ ልጆች! የከበረ ተስፋ! ይህ ሁልጊዜ ልናሰላስለው የሚገባን ተስፋ ነው! እርሱን ላልወደደው ዓለም የተበረከተ አቻ የሌለው ፍቅር! ይህ ሐቅ ነፍሳችንን በሐሴት የመሙላት ኃይል ያለው ሲሆን፤ ደግሞም ራሳችንን ለእግዚአብሔር ፈቃድ እንድናስገዛ የሚያደርግ ነው:: መለኮታዊውን ባህሪ በመስቀሉ ብርሃን ባጠናን ቁጥር፧ ምህረት፣ አፍቃሪነትና ይቅር ባይነት ከፍትሕና ከአድልዎ ነፃ ከመሆን ጋር ሕብረት ሲፈጥሩ እንመለከታለን፡፡ እንዲሁም እናት መንገዱን ለሳተው ልጇ ካላት ናፍቆትና ርኅራኄ ጋር ሲነጻጸር እጅግ የላቁትን ሊቆጠሩ የማይችሉትን ዘላለማዊ የፍቅሩን መረጃዎች አብልጠንና ለይተን እናያለን፡፡ ክየመ 13.2