እግዚአብሄር ቃል ገብቷል

2/16

ብርታት ያስፈልጋችኋል?

እግዚአብሔር ለህዝቡ ብርታትን ይሰጣል።
መዝ 29፡11

አታውቅምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም
አምላክ፣ የሰማይና የምድር ዳርቻ ፈጣሪ ነው፡፡
አይደክምም! አይታክትም! ማስተዋሉም በማንም
አይመረመርም፡፡ ለደከመው ብርታት ይሰጣል፤ ለዛለው
ጉልበት ይጨምራል፡፡ ወጣቶች እንኳ ይደክማሉ!
ይታክታሉም፣ ጎበዛዝትም ተሰናክለው ይወድቃሉ።
እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ ግን፣ኃይላቸውን
ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፤
ምአይታክቱም፤ ይሄዳሉ፤ አይደክሙም፡፡
ኢሳ 40፡28-31

በፊታችን ያለውን ስራ በራሳችን ብርታት እንሰራው ዘንድ እግዚአብሔር አይጠይቀንም፡፡ የእኛ ሰብአዊ አቅም የማይወዳደራቸውን ድንገተኛ መጠይቆች ሁሉ ልናሚላ የምንችልበትን መለኮታዊ እገዛ አበርክቶልናል። እቃገ 11.1

በማለዳ ከእንቅልፋችሁ ስትነቁ፣ ረዳተቢስ መሆናችሁና ከእግዚአብሔርም ዘንድ ብርታት እንደሚያስፈልጋችሁ ይሰማችኋል? ለሰማያዊ አባታችሁስ መሻታችሁን በትህትናና ከልብ በሆነ መጠይቅ ታሳውቃላችሁ? እንዲህ የምታደርጉ ከሆነ መላእክት ጸሎታችሁን ይመዘገባሉ፤ ያለማስተዋል ስህተት ለመስራትና ሌሎችን ወደ ስህተት የሚመራን ነገር ለማድረግ በሚያስችል አደጋ ውስጥ ስትወድቁ፣ ጠባቂ መላእክቶቻችሁ ከጎናችሁ ሰመሆን ወደ ተሻለ መንገድ እንድታመሩ ይረዷችኋል፤የምትናገሩትን ቃል ይመርጡላችኋል፤ በድርጊቶቻችሁም ላይ በጎ ተጽእኖን ያሳድራሉ፡፡ እቃገ 11.2

እግዚአብሔርን እንደ ቃሉ የሚቀበል ሰው የሚቀዳጀውን ሰላምና ደስታ ቃላት ሊገልጹት አይችሉም፡፡ በመከራዎች አይናወጥም፡፡ እኔነት ተሰቅሏል፡፡ ዕለት በዕለት ስራው እየጠነከረሰት ሊሄድ ይችላል፤ ፈተናዎቹም ሊሰረቱ ይችላሉ፤መከራውም ሌከር ይችላል፡፡ ነገር ግን አይበረጎጎም፤ ምክንያቱም ለሚያስፈልገው ነገር የሚሰቃ ብርታት ይቀበላልና፡፡ እቃገ 12.1

ፈጽሞ ማየት በማይቻልባቸው በጽልመት በተዋጡ ቀናት ውስጥ ስታልፍ ሰእግዚአብሔር ላይ እምነት ይኑርህ፡፡ እርሱ ፈቃዱን እያከናወነና፣ ስለ ህዝቡም ነገሮችን ሁሉ ለበጎ እየለወጠ ነው፡፡ እርሱን የሚወዱና የሚያገለግሉ ሁሉ ብርታታቸው ሰየዕለቱ ይታደሳል። እቃገ 12.2

ያጋጠሙንን ችግሮች በክርስቶስ ብርታት ካሸነፍናቸው፣ጠላቶች ተነስተውብን ለክርስቶስ ብርታት ካባረርናቸው ፣ሃላፊነቶችን ተቀብለን በክርስቶስ ብርታት በታማኝነት ከተወጣናቸው፣ እጅግ የከበረ ልምድ በህይወታችን እያካበትን ነው፡፡ በሌላ በምንም አይነት መንገድ ልንማር የማንችለውን ትምህርት፣ ይኼውም፡- አዳኛችን በችግር ጊዜ የቅርብ ረዳታችን እንደሆነ እንማራለን፡፡ እቃገ 12.3

በራሳችሁ ብርታት ምንም ማድረግ አትችሉም፤ ነገር ግን ሰኢየሱስ ብርታት ሁሉን ማድረግ ትችላላችሁ፡፡ የእግዚአብሔር የተስፋ ቃሎች የተሟሉና የተትረፈረፉ ናቸው፡፡ ከዚህም የተነሳ ማንም ሰው በሰብአዊ ብርታት ላይ ለመደገፍ ምንም ምክንያት የለውም።ለሚጠሩት ሁሉ ሊረዳቸውና ሊያጽናናቸው እርሱ ቅርብ ነው:: እቃገ 12.4

ብርታትና ጸጋ ለምትለምን ነፍስ ሁሉ በመላእክቱ አማካኝነት ይታደሉ ዘንድ በክርስቶስ ተሰርክተዋል። እቃገ 13.1

ሰዎችን ጠንካራ የሚያደርጓቸው መሰናክሎች ናቸው:: ችግሮችና ግጭቶች የሰዎችን የሞሪል ጡንቻዎች ያዳብራሉ።ኀላፊነትን መሸሽና ድሎት የበዛበትን ህይወት መፈለግ የጠንካራ መንፈሳዊ ጡንቻና የሞራል ኀይል ባለቤት መሆን ይችሉ የነበሩትን ሰዎች ልፍስፍስና ድንክዬ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። እቃገ 13.2