እግዚአብሄር ቃል ገብቷል

13/16

ምሪት ያስፈልጋችኋል?

ከእናንተ ማንም ጥበብ ቢጎድለው!
ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉም የሚሰጠውን
እግዚአብሔርን ይለምን፤ ለእርሱም ይሰጠዋል።
ያዕ 1፡5

አስተምርሃለሁ፤ በምትሄድበትም መንገድ እመራሃለሁ!
እመክርሃለሁ በአይኔም እከታተልሃለሁ፡፡
መዝ 32፡8

ፈቃዳችንን ለእግዚአብሔር እስካስረከብንና በብርታቱና በጥበቡም እስከታመንን ድረስ፣ በእርሱ ትልቅ እቅድ ውስጥ የተዘጋጀልንን ዓላማ ለመፈጸም ሰደህንነት መንገድ ይመራናል፡፡ እቃገ 45.1

እግዚአብሔርን የሚያሳዝን ነገር በምንም መንገድ ላለማድረግ የወሰኑ ሰዎች፣ ጉዳያቸውን ሰእግዚብአብሔር ፊት ካቀረቡ በኋላ የትኛውን መንገድ መከተል እንዳለባቸው እርሱ ያሳውቃቸዋል፡፡እናም ጥበብን ብቻ ሳይሆን ብርታትንም ይቀበላሉ፡፡ እቃገ 45.2

ራሳችንን ለጠቢቡ ጌታ አሳልፈን ስንሰጥ፣ ለእርሱ ክብር የሚሆነውን የህይወት አቅጣጫና ባህሪይ እንድንይዝ ያደርገናል፡፡ግድየለሽ በሆነ አካሄድ ራሳችንን መከራ ውስጥ እንዳንጨምር፣በእያንዳንዱ የህይወት ውሳኔ ውስጥ ሰጥሰብ ልንመላለስ ይገባል፡፡እግዚአብሔር የሰጠንን ነገር ሰመርሳት፣ ወይም ስጦታዎቹን ያለአግባብ በመጠቀም ራሳችንን ችግር ውስጥ ልንዘፍቅ አይገባም፡፡ የክርስቶስ ሰራተኛች የሆንን የእርሱን መመሪያ መታዘዝ ይገባናል።ስራው የእግዚአብሔር ነው፤ ሌሎችን መባረክ ከፈልገን የእርሱን ዕቅድ መከተል ያስፈልገናል፡፡ እኔነት ማዕከላዊውን ስፍራ መያዝ የለበትም፤ ክብርም ሊቀበል አይገባም፡፡ በራሳችን አሳብ መሰረት ካቀድን፣ እግዚአብሔር ደግሞ ለስህተቶቻችን አሳልፎ ይሰጠናል። ነገር ግን የእርሱን ምሪት ከተከተልን ከአስቸጋሪ ጎዳናዎች ነጻ ያወጣናል፡፡ እቃገ 45.3

ለራሳችን ሕይወት ዕቅድ ለማውጣት ጥበቡ የለንም፡፡የወደፊቱን ህይወታችንን መልክ ማስያዝ የእኛ ድርሻ አይደለም፡፡... ሕይወታችን የእግዚአብሔር ፈቃድ ውጤት እንዲሆን በእርሱ ላይ መደገፍ ያስፈልገናል፡፡ መንገዳችንን ለእርሱ ስናስረክብ፣እርሱ ደግሞ እርምጃችንን ይመራል፡፡ እቃገ 46.1

ሕይወታችንን ለእርሱ አገልግሎት ካስረከብን፣ እግዚአብሔር ሊረዳን ሰማይችል ሁኔታ ውስጥ ልንሆን አንችልም፡፡ ሁኔታችንምንም ቢሆን ምን፣ መንገዱን የሚያሳየን መሪ አላን፡፡ ጎራ ያጋባን ነገር ምንም ቢሆን ምን አማካሪ አላን፡፡ ሰቆቃችን፣ሃዘናችን ወይም ብቸኝነታችን ምንም ያህል ቢገዝፍ የሚራራልን ወዳጅ አላን፡፡ ባለማወቅ እግራችን ሲደናቀፍ እንኳ፣ ክርስቶስ አይተወንም፡፡ ድምጹ ጥርት ብሎ እንዲህ ሲል ይደመጣል “እኔ መንገድ ፣ እውነትና ህይወት ነኝ፡፡” እቃገ 46.2

በእኛ ላይ ባለው ትኩረትና የፍቅር እንክብካቤ እኛ ራሳችንን ከምናስተውለው በላይ የሚያስተውለን ጌታ፣ በራስ ወዳድነት የራሳችንን መንገድ እንዳንከተል ሊከላክላን ይችላል፡፡ ... ብዙ ጊዜ የእኛ እቅዶች የሚፈርሱት የእግዚአብሔር እቅድ እንዲሳካ ነው፡፡በየዕለቱ የጌታን ፊት ብትፈልጉና ብትላወጡ፣ መንፈሳዊ ምርጫችሁም ነጻ ቢሆንና በእግዚአብሔም ሃሴት ብታደርጉ፣ የመታዘዝና የአገልገሎት ቀንበር የሆነውን የክርስቶስን ቀንበር ለመሸከም ሰደስታ ከሙሉ ልባችሁ ብትስማሙ ፣ማጉረምረማቸሁ ሁሉ ጸጥ ባለ፣ ችግሮቻችሁ ሁሉ በተፈቱ፣አሁን ያስጨነቃችሁ ነገሮች ሁሉ መፍትሔ ባገኙ ነበር። እቃገ 46.3

በእግዚአብሔር የተነደፈውን የህይወት እቅድ በጥንቃቄ ልንከተል ይገባል፡፡ አንድን ስራ በመምረጥ ረገድ ልንከተለው የሚገባን አስተማማኝ ምሪት፣በቅርባችን የምናገኘውን ስራምርጥ አድርገን መስራት፣ መንገዳችንን ለእግዚአብሔር ማስረከብ፣ እርሱም የሚከፍትልንን በር ማጤን ነው፡፡ እቃገ 47.1