ሥነ - ትምህርት

49/56

ምዕራፍ 29—የሰንበት ቀን

«በእናንተና በእኔ መካከል ምልክት ትሆን
ዘንድ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ታውቁ ዘንድ፡፡»
EDA 281.1

እንደ አንድ የትምህርት መሣሪያ ሲታይ የሰንበት ጥቅም እጅግ በጣም ከልክ በላይ ነው፡፡ እግዚአብሔር ከእኛ ምንም ነገር ቢጠብቅብን እንኳ ከራሱ ክብር ከፍሎ በእጥፍ ግሩም ድንቅ አድርጐ ይመልስልናል ይለውጠናልም፡፡ ከእሥራኤላዊያን ላይ ይፈልግባቸው የነበረው አሥራት ከሙሉ ክብርና ውበት ጋር በሰማይ ያለውን የርሱን መቅደስ የሚመስል ተምሳሌ እርሱ በምድር ላይ የመኖሩ ምልክት በሆነው ቤተ መቅደስ ለሚያገለግሉ ሰዎች ተጠብቆ እንዲቀመጥ ተመደበ፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ካለን ጊዜ ከፍለን የርሱ ለሚፈልግብን ጉዳይ የምናውለው ሰዓት ተሰጥቶናል፡፡ የርሱ ስምና ማኅተም «ምልክት ናት» ይላል፡፡»በእኔና በእናንተ መካከል... እኔ ጌታ እንደሆንሁ ታውቁ ዘንድ» ምክንያቱም «በስድስት ቀን ጌታ ሰማይንና ምድርን ባህርንና በነርሱም ውስጥ ያለውን ሁሉ ፈጠረ፡፡ በሰባተኛውም ቀን አረፈ፡፡ ስለዙህም ጌታ የሰንበትን ቀን ባረከው ቀደሰውም፡፡» ዘፀ 31፡13 ምዕ 20፡11 ሰንበት የፈጠራና የቤዛነት ኃይል መልክት ናት፡፡ እግዚአብሔር የሕይወትና የዕውቀት ምንጭ መሆኑን ታመለክታለች፡፡ የሰውን ልጅ ጥንታዊ ክብር ታስታውሰናለች፡፡ እናም እግዚአብሔር እኛን እንደገና መልሶ በርሱ አምሳል ሊፈጥረን ማሰቡን ትመሰክራለች፡፡ EDA 281.2

ሰንበትና ቤተሰብ በኤደን በአንድ ላይ የተመሠረቱ ናቸው፡፡ እናም በእግዚአብሔር ሐሳብ ውሰጥም በአንድ ላይ የተያያዙና የማይነጣጠሉ ናቸው፡፡ ከሌሎች ቀኖች በበለጠ በዚች ቀን የኤደንን ሕይወት መኖር እንችላለን፡፡ የቤተሰቡ አባላት በመሉ በሥራ በጥናት በስግደትና በመዝናኛ ሰዓት አባትየው የቤተሰቡ ካህን በመሆን አባትና እናት ደግሞ በአንድ ላይ የልጆቻቸው መምህራንና ጉደኞች በመሆን በሕብረት እንዲኖሩ የእግዚአብሔር እቅድ ነበረ፡፡ ነገር ግን የኃጢአት ውጤቶች የሕይወት አኳኋኖችን ስለለወጡት ይኸንን ሕብረት በጣም አሻከረው፡፡ አባትየው የልጆቹን ፊት በሳምንት ውስጥ አንድ ጊዜ እንኳ ለማየት የማይችልበት ውጥረት ነበረበት፡፡ የዝምድና ፍቅሩን ወይም ትምህርት ለመስጠት የሚያስችለው ዕድል ማግኘት አልቻለም፡፡ የእግዚአብሔር እቅድ ግን የሥራው ጠባይ ለሚያቀርበው ጥያቄ ገደብ አበጅቶለት ነበር፡፡ በሰንበት ላይ በምህረት የተሞላ እጁን አሳረፈባት፡፡ በዚች የራሱ በሆነች ዕለት ከርሱ ጋር ከተፈጥሮና እርስ በራሳቸውም ለቤተሰቡ ሁሉ የመገናኛ ዕድል አበጀላቸው፡፡ EDA 281.3

ሰንበት የመፍጠር ኃይል መታሰቢያ ስለሆነች ከሌሎች ቀኖች በተለየ በሥራው አማካይነት ከእግዚአብሔር ጋር የምንተዋወቅበት ዕለት ነች፡፡ በልጆች አእምሮ ውስጥ ስለ ሰንበት የሚኖረው ሐሳብ ራሱ ከተፈጥሮ ነገሮች ውበት ጋር የተሳሳረ መሆን አለበት፡፡ በሰነበት ቀን የፀሎት ስብከት ወደሚደረግበት ቦታ የሚሄድ ቤተሰብ ልክ የሱስና ደቀመዛሙርቱ ወደ ሲናጐግ እንደሄዱ በስክ በባህር ዳርቻ ወይም ወደ ቁጥቋጦና ጥቂት ዛፎች ወዳሉበት ጫካ የሚሄድ ቤተሰብ ደስተኛ ነው፡፡ ከተከፈተው የተፈጥሮ መጽሐፍ ማብራራያዎች ያሉት የተፃፈውን የእግዚአብሔር ቃል በአረንጓዴ ዛፍ ሥር ፍፁም ንፁህ የሆነ አየር እየተመገቡ ቃሉን ለማጥናትና ለላይኛው አባት የምስጋና መዝሙር እየዘመሩ ልጆቻቸውን ማስተማር የሚችሉ አባትና እናት ደስተኞች ናቸው፡፡ EDA 282.1

በዚህ ዓይነት ሕብረት ወላጆች ልጆቻቸውን ከልባቸው ጋርና ከእግዚአብሔር ጋር ሊፈታ በማይችል ትስስር እንዲገናኙ ያደርጋሉ፡፡ EDA 282.2

እንደ አንድ የአዕምሮ ማሰልጠኛ የማስተማሪያ መንገድ የሰንበት ዕድሎች ዋጋ ያላቸው ናቸው፡፡ የሰንበት ትምህርቶች ሁልጊዜ በሰንበት ጧት በሚሰጡበት ጊዜ በትምህርቶቹ ላይ በጥድፊያ ወረር ወረር ማድረግ ሳይሆን ጥንቃቄ በተሞላበት ጥናት እስከሚቀጥለው ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ ድረስ በየቁኑ መክለሳ ወይም በማብራሪያ ሳምንቱን በሙሉ ይጠኑ በመሆኑም ትምህርቱ በአእምሮ ውስጥ ይቀረፃል፡፡ ለዘላለም የማይጠፋ መዝገብም ይሆናል፡፡ EDA 283.1

ስብከት በምናዳምጥበት ጊዜ ወላጆችና ልጆች ለስብከቱ የተመረጡትን ጥቅሶች በማስታወሻ መዝግበው ይያዙ፡፡ እናም በተቻለ መጠን በዚያው የሃሳብ መስመር እቤት ውስጥም እርስ በራስ መደጋገም ይቻላል፡፡ ልጆች በዚህ ዓይነት መንገድ ስብከትን ማዳመጥና መከታተል ሊመጣባቸው የሚችለውን ድካምና መሰላቸት አስወግዶ የተያያዘ ተከታታይ ሃሳብን በትኩረት የመከታተል ልምድ ያዳብርላቸዋል፡፡ EDA 283.2

ልቦናን አሰባስቦ በተመስጦ በቀረቡ ሐባቦች ላይ ማተኮር ለተማሪው በሕልሙ አይቷቸው የማያውቀውን መዝገቦች ይከፍትለታል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጠውን ሕይወት በራሱ ውስጥ ማግኘቱን ያረጋግጣል፡፡ EDA 283.3

«ቃልህ ተገኝቷል እኔም በልቸዋለሁ ቃልህ ሐሴትና የልብ ደስታ ሆነኝ፡፡» ኤር 15፡16 EDA 283.4

«ሥርዓትህን አስባለሁ፡፡» «ከወርቅና ከክቡር እንቁ ይልቅ ይወደዳል፡፡ ባሪያህ ደግሞ ይጠብቀዋል፤ በጠበቁም እጅግ ይጠቀማል፡፡» መዝ 119፡48 ምዕ 19፡10፣11 EDA 283.5