ሥነ - ትምህርት

47/56

ምዕራፍ 27—ግብረገብ

«ፍቅር ራሷን አትወድም፡፡» EDA 269.1

የደግነት ዋጋ ቀላለ ግምት የሚሰጠው አይደለም፡፡ብዙ ከልባቸው የዋህ የሆኑ ሰዎች ፀባይ ይጐድላቸዋል፡፡ ልባዊና ትክክለኛ በመሆናቸው ክብር የሚሰጣቸው ብዙ ሰዎች በሚያሳዝን ሁኔታ ትህትናና መግባባት ይጐድላቸዋል፡፡ ይህ ጉድለት የራሳቸውን ደስታ የሚያበላሽና ለሌሎች የሚሰጡትን አገልግሎትም ይቀንስባቸዋል፡፡ በሕይወት ውስጥ ካሉት ብዙ ጣፋጭና ጠቀሚ ልምዶች ደግ ባልሆነው ሰው ለሐሳቡ ፍላጐት ብቻ በመስዋዕትነት ይለወጣሉ፡፡ EDA 269.2

ተጫዋችነትና ደግነት በወላጆችና መምህራን ዘንድ ልዩ እንክብካቤ ሊደረግበት ይገባል፡ ሁሉም ፏፏቴ የሆነ ገጽታ የተገራ ለስላሳ ድምጽ የመግባባት ችሎታ ያላቸው ይሆኑ ይሆናል፡፡ እናም እነዚህ ሁሉ የኃይል ንጥረ ቅመሞች ናቸው፡፡ ልጆች ፊቱ ፈታ ባለ ሁኔታ ብርሃን የተሞላበት ጨዋታ ሲያዩ ይማረካሉ፡፡ የዋህነትና ደግነት አሳዩአቸው፡፡ እነሱም ለእናንተና ለእርስ በራሳቸውም ያንኑ መንፈስ መልሰው ይገልፃሉ፡፡ EDA 269.3

እውነተኛ ደግነትን ማኅበራዊ የሆኑ የአብሮ መኖር ደንቦችንና ሥርዓቶችን በመለማመድ ብቻ መማር አይቻልም፡፡ የአቋቋምና አረማመድ ሥርዓት ሁልጊዜ በሚገባ ክትትልና ቁጥጥር ሊደረግበት ይገባል፡፡ መርህ ለድርድር በማይቀርብበት ቦታ ሁሉ ስለሌሎች ነገሮች ማሰብና ማመዛዘን በታወቀ ወግና ልማድ ወደመርካት ያመራል፡፡ ነገር ግን እውነተኛ ደግነት መርህን ለማንኛውም ዓይነት ደንብ መስዋዕት የሚከፍል አይደለም፡፡ ማግለልን ውድቅ ያደርጋል፡፡ የራስን ከብር ያስተምራል፡፡ ሰውን እንደሰውነቱ ማክበር ያስተምራል፡፡ በታላቁ ሰብዓዊ የወንድማማችነት ማኅበር ውስጥ አባል ለሆነ ሰው ሁሉ ከበሬታን ይሰጣል፡፡ EDA 269.4

ለግብረገብና ለአሰራሩ ደንብ ብቻ ዋጋ መስጠት በነዚህ መስመሮች ብቻ ትምህርት በመለገስ ብዙ ጊዜ ማጥፋት አደጋ አለበት፡፡ ከእያንዳንዱ ወጣት የሚፈለገው ታላቅ ኃይል የሚጠይቅ ጥረት ያለበት ሕይወት አስቸጋሪና ከባድ ዘወትር በሕይወት ውስጥ ለሚያጋጥሙ የተለመዱ ተግባራት እንኳ ከዚያም በላይ የዓለምን ከባድ የድንቁርናና ሸክምን ለማቃለልና ተገባቢዎች የሚሰጡት ትንሽ ቦታ ብቻ ነው፡፡ EDA 270.1

በወግና በደንብ ላይ አጥብቀው የሚያተኩሩ ብዙ ሰዎች የፈለገውን ያክል ድንቅ ነገር ቢሆንም እንኳ እነሱ ከመደቡለት ደረጃ ጋር የሚስማማ ካልመሰላቸው ለማንኛው ነገር የሚያሳዩት ከበሬታ ትንሽ ነው፡፡ ይህ ደግሞ የተሳሳተ ትምህርት ነው፡፡ ይህ ዓይነት ባህሪይ አሳሳቢ የሆነ ኩራትንና እጅግ ጠባብ የሆነ ገለልተኝነትን ያበረታተል፡፡ EDA 270.2

የእውነተኛ ትህትና ውስጣዊ መሠረት ለሌሎች መልካም አሳቡ መሆን መቻል ነው፡፡ ዋናው አስፈላጊ ዘላቂ ትምህርት ርህራሄን የሚያስፋፋና አጠቃላይ የዋህነትን የሚያበረታታ ሲሆን ነው፡፡ አንድን ወጣት ለወላጆቹ ልዩ እንዲሆን፤ ይህተታቸውን በትዕግስት የማይቀበል ለሚያስፈልጋቸው ነገርም ረዳት የማይሆንላቸው ከሆነ አመዛዛኝ አሳቢና ገር የማያደርገው ከሆነ ለወጣቶች ለአረጋዊያንና እድላቸው ለተሰናከለባቸው ለጋስና ጠቃሚ ረዳት ለሁሉም ሰው ደግ እንዲሆን የማያደርገው ከሆነ ባህል የሚባለው ነገር ዋጋ የሌለው ውድቅ ነው፡፡ EDA 270.3

ትክክለኛውን የሐሳብና የሥነ-ምግባር ጥራት ለማግኘት በሌላ መልክ ተደንግገው የተቀመጡ ደንቦችን ከማክበር ይልቅ መለኮታዊው መምህር ባለበት ትምህርት ቤት መማር የበለጠ ጠቃሚ ይሆናል፡፡ የርሱ ፍቅር ልብ ውስጥ ሲገባ የርሱን ተምሳሌት እንዲይዙ አድርገው የሚቀርጹ እነኛ ዳበሳዎች ለባህሪ ማጣሪያ ያደርጉለታል፡፡ ይህ ትምህርት ሰማይ ወለድ የሆነ ክብርና ፀባይን ከፍሎ ይሰጣል፡፡ ወረተኛ በሆነ ኅብረተሰብ ውስጥ ላይ ላዩን የሚታይ ብልጭልጭ ፈጽሞ ሊስተካከለው የማይችል የተፈጥሮ ችሎታና የምግባር ታላቅነት ይሰጣል፡፡ EDA 271.1

መጽሐፍ ቅዱስ ደግነትን ያዝዛል፡፡ ራስን ወዳድ ስላልሆነው መንፈስ ስለታላቁ ፀጋ እውነተኛ ትህትናን ስለሚቀርፀው አሸናፊ ስለሆነው ትዕግሥት ብዙ መግለጫዎች ያቀርባል፡፡ እነኝህ የክርስቶስ ባሕሪይ ነፀብራቆች ናቸው፡፡ በዓለም ላይ ያለው እውነተኛ ገርነትና ደግነት ሁሉ ስሙን በማያውቁ ሰዎች ውስጥ ዘንድ እንኳ ያለው ሁሉ ከርሱ የመጣ ነው፡፡ እርሱም እነዚህ ባህሪያት በልጆቹ ሁሉ ውስጥ ፍፁም ትክክለኛ በሆነ መንገድ እንዲንፀባረቁ ይፈልጋል፡፡ በእኛ በሰዎች ውስጥ የርሱ ውበት ይኖር ዘንድ የርሱ ዓላማና ፍላጐት ነው፡ EDA 271.2

ስለ ሥነ-ምግባር ከተፃፉት ትምህርቶች ሁሉ እጅግ ከፍተኛ ዋጋ ያለው በመድህናችን የተሰጠው ክቡር መማሪያ ሲሆን በመንፈስ ቅዱስ ቃል ተመርቶ በሐዋርያው ጳውሎስ የተነገረው በእያንዳንዱ ሰብዓዊ ፍጡር በወጣቱም ሆነ በሽማግሌ አእምሮ ውስጥ መቀመጥ ያለባቸው ቃላት ናቸው፡፡ በሐዋሪያው ጳውሎስ የተነገረው በእያንዳንዱ ሰብዓዊ ፍጡር በወጣቱም ሆነ በሽማግሌ አእምሮ ውስጥ መቀመጥ ያለባቸው ቃላት ናቸው፡፡ EDA 271.3

«እኔ እንደ ወድኋችሁ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ፡፡» ዮሐ 13፡34 EDA 271.4

«ፍቅር ይታገሳል ቸርነትም ያደርጋል፡፡
ፍቅር አይቀናም ፍቅር አይመካም አይታበይም፡፡
ፍቅር የይገባውን አያደርግም የራሱንም አይፈልግም፡፡
በደልን አይቆጥርም ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ
ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፤ ሁሉን ይታገሳል፤
ሁሉን ያምናል ሁሉን ይታገሳል፤
ሁሉን ያምናል፤ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፤
በሁሉ ይፀናል፡፡ ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም፡፡» 1ኛ ቆሮ 13፡4-8
EDA 272.1

ሌላው በከፍተኛ ጥንቃቄ መያዝ ያለበት እጅግ ድንቅ ፀጋ ደግሞ ቅን አገልጋይነት ነው፡፡ ለእግዚአብሔር ቀና አገልጋይ መሆን በርሱ ዘለዓለማዊ ታላቅነትና እርሱም እዚህ በመካከላችን ያለ መሆኑን በመገንዘብ መንፈስ የሚመጣ ነው፡፡ በዚህ በማይታየው ስሜት የእያንዳንዱ ልጅ ልብ በጥልቀት ሊሳብ ይገባዋል፡፡ ልጅ የፀሎት ሰዓት ቦታና ምዕመናን የሚገኙበት የተቀደሱ ሰዓታት ናቸውና በሚገባ እንዲያከብራቸው መማር አለበት፡፡ አገልግሎቱ ልባዊ ዝንባሌና በሥነ-ሥርዓት በሚከናወንበት ጊዜ ይኸንን የሚያነቃቃው ስሜት ይበልጥ ጥልቀት እያገኘ ይሄዳል፡፡ EDA 272.2

እግዚአብሔር የሚገኝበት ልዩ ሥፍራ በመሆኑ ምን ያክል መክበር እንዳለበት በቅዱስ መጽሐፍት ውስጥ ያሉ ቃላት ላይ ሐሳብን አሰባስቦ ማተኮርና ዘወትርም እነሱኑ መደጋገም ለወጣቱም ሆነ ለአረጋዊው መልካም ነው፡፡ EDA 272.3

«የቆምክበት ሥፍራ የተቀደሰች መሬት ናትና ጫማህን ከእግርህ አውጣ፡፡» /ዘፀ 3፡5/ በማለት በሚቃጠለው ቁጥቋጦ አጠገብ እግዚአብሔር ሙሴን አዘዘው፡፡ EDA 272.4

ያዕቆብ መላዕክት ሲመላለሱ ያየበትን ራዕይ እንደጨረሰ ጮኸ፡፡ «በእውነት እግዚአብሔር በዚህ ሥፍራ» ነው፡፡ ይህ ሥፍራ የእግዚአብሔር ቤት ነው እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ ይህም የሰማይ ደጅ ነው፡፡» ዘፍ 28፡16፣17 EDA 272.5

«እግዚአብሔር ግን በተቀደሰ መቅደሱ አለ ምድርም ሁሉ በፊቱ ዝም ትበል፡፡» እንባ 2፡20 EDA 273.1

«እግዚአብሔር ታላቅ አምላክ ነውና
በአማልክትም ሁሉ ላይ ታላቅ ንጉሥ ነውና
እግዚአብሔር ሕዝቡን አይጥላቸውም የምድር
ዳርቻቸውም በእጁ ውስጥ ናቸው፡፡ የተራሮች
ከፍታዎች የርሱ ናቸው፡፡ ባህር የርሱ ናት
የእርሱም አደረጋት የብስንም እጆቹ ሠሩአት
ኑ እንስገድ ለእሱ እንገዛ፡፡
በርሱ ባደረገን በእግዚአብሔር ፊት እንንበርከክ፡፡
እግዚአብሔር እርሱ አምላክ አንደሆነ እውቁ
እርሱ ሠራን እኛም አይደለንም
እኛስ ሕዝቡ የማሰማሪያውም በጐች ነን
ወደ ደጆቹ በመገዛት ወደ አበባባዮቹም በምስጋና ግቡ
አመስግኑት ስምንም ባርኩ፡፡» መዝ 95፡3-6 ምዕ 100፡3-4
EDA 273.2

ከበሬታ የተሞላበት አገልግሎት የእግዚአብሔርን ስም በመጥራት ላይም ሊታይ ይገባል፡፡ የርሱ ስም በቀላሉና በዘፈቀደ በፍፁም ሊነሳ አይገባውም፡፡ በፀሎት ላይ እንኳ ብዙ ጊዜ ስሙን ማንሳት ወይም አስፈላጊ ያለሆነ ድግግሞሽ መወገድ አለበት፡፡ «ስሙም የተቀደሰና የተፈራ ነው» መዝ 119፡9 መላዕክትም እንኳ ስሙን ሲጠሩ ፊታቸውን ሸፍነው ነው፡፡ ታዲያ እኛ የወደቅንና በኃጢአት የትሞላን ሆነን እያለን ስሙን በከንፈሮቻችን ለመጥራት የምንችለው በምን ዓይነት አክብሮትና ትሕትና ነው፡፡ EDA 273.3

የእግዚአብሔርን ቃል ከልባችን በጥልቀት ልናከብረው ይገባል፡፡ ለታተመው መጽሐፍ ቅዱስ ታላቅ ከበሬታ ልናሳይ ይገባናል፡፡ ሥራ ላይ መዋል ያለበት በዘልማዳዊ ተራ አጠቃቀም አይደለም፡፡ ወይም የግዴለሽነት አያያዝ ተገቢ አይደለም፡፡ እናም መጽሐፍ ቅዱስ ለቀልድ ወይ ለአንዳንድ የሰዎች አባባሎች እንዲስማማ ሆኖ ተቀንጭቦ መጠቀስ ፈጽሞ የለበትም፡፡ «የእግዚአብሔር ቃል ሁሉ ተፈትናለች፡፡» «በምድር ላይ እንደተፈተነ ሰባት ጊዜም እንደ ተጣራ ብር» ነው፡፡ ምሳ 30፡5 መዝ 12፡6 EDA 273.4

ከሁሉም በላይ ልጆች እውነተኛ ልባዊ አገልግሎት በታዛዥነትም እንደሚገለጽ ይማሩ፡፡ እግዚአብሔር መሠረታዊ ላልሆነ ነገር ትዕዛዝ አይሰጥም፡፡ እርሱ እንደተናገረው እርሱን እንደመታዘዝ የሚያስደሰተው ሌላ የአገልግሎት መግለጫ ነገር የለም፡፡ EDA 274.1

የትህትና ከበሬታ ለእግዚአብሔር ወኩሎችም ለአገልጋዮቹ ለመምህራንና ለወላጆች እርሱን ተከተው ለሚናገሩና ለሚሠሩ ሁሉ ማሳየት አለብን፡፡ ለእነርሱ በምናሳየው ከበሬታ እርሱም ይከበራል፡፡ EDA 274.2

እግዚአብሔር ለአረጋዊያን ተገቢ ከበሬታ እንድንሰጥ ያዝዛል፡፡ እንዲህም ይላል፡፡ «የሸበተ ጠጉር የክብር ዘውድ ነው፡፡ እርሱም በጽድቅ መነገድ ይገኛል፡፡» ምሳ 16፡31 ስለ ተካሄዱ ጦርነቶችና ስለተገኙ ድሎች ሽክሞችን በትዕግሥት ስለመቻል ፈተናዎችን ስለመቋቋም ይናገራል፡፡ ለእረፍት ስለተቀረቡ የደከሙ እግሮች በቅርቡ ባዶ ስለሚሆን ስፍራዎች ይናገራል፡፡ ልጆች ስለዚህ ነገር እንዲያስቡ እርዷቸው፡፡ እናም በደግነታቸውና በአክብሮታቸው የአረጋዊያንን መንገድ ለስላሳ ያደርጋሉ፡፡ ለለጋው ሕይወታቸውም ፀጋና ውበትን ያገኙበታል፡፡ ትዕዛዙን በንቃት መጠበቅ ያስፈልጋል፡፡ «በሽበታሙ ፊት ተነሳ ሽማግሌውንም አከብሮ» ዘለ 19፡32 EDA 274.3

አባቶች እናቶችና መምህራንን ለልጆች የአምላክ ወኪሎች ስለ አደረጋቸው እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ የጣለባቸውን ኃላፊነት ልጆች ማክበር አለባቸው፡፡ በቀን ተቀን የሕይወት ግንኙነት የሚገለጠው ባህሪይ እነኛን የእግዚአብሔር ቃላት በክፉ ወይም በበጐ ጐን ለልጆች ይተረጉምላቸዋል፡፡ EDA 274.4

«አባት ለልጆቹ እንደሚራራ እንዲሁ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ይራራል፡፡» መዝ 103፡13 እናት ልጁዋን እንደመታጽናና እንዲሁ አጽናናችኋለሁ፡፡ እንደነዚህ ዓይነት ቃላትን የሚያገኝ ልጅ ደስተኛ ነው፡፡ የአባትን የእናትን የመምህርን ገርነትና ቅንነት ታጋሽነት የእግዚአብሔርን ፍቅር ቀና ፍርድ እና ታጋሽነቱን በማሳየት የማተረጉሙለት ልጅ ለምድራዊ ተንከባካቢዎቹ በእምነት ራስን ዝቅ በማድረግ የሚያገለግል ልጅ ለእግዚአብሔርም በመተማመን በመታመን በመታዘዝና ቀና ልባዊ አገልግሎት በመስጠት ደስተኛ ይሆናል፡፡ ለልጁ ወይም ለተማሪው እንዲህ ዓይነት ስጦታ የሚያካፍል ሰው በዘመናት ሁሉ ከሚታወቀው ሀብት ንብረት ሁሉ በላይ በእጅጉ የበለጠ መዝገብ ሰጠው ማለት ነው፡፡ ለዘለዓለም የማይጠፋ መዝገብ፡፡ EDA 274.5